ሐምሌ 19 - ቅዱስ ገብርኤል

ይህች ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣን እና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ቀን የሚታሰብበት ነው፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፡፡

ዘመነ ሰማዕታት አምልኮተ ጣዖት በተስፋፋበት፣ አምልኮተ እግዚአብሔር በጠፋበት ዘመን መምለኬ ጣዖት የነበረ የሀገሩ ገዥ እለ እስክንድሮስ በክርስቲያኖች ላይ ስደትን ስላወጀ፣ ቅድስት ኢየሉጣ የሦስት ዓመት ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ወደ ሌላ ሀገር ተሰደደች፡፡ ጌታ በወንጌል ‹‹በአንዲቱ ከተማ መከራ ሲያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ›› (ማቴ. 0፡፳3) ያለውን በማሰብ ተሰዳ ሳለች፣ የአላዊው መኰንን ወታደሮች ተከታትለው ደርሰው ለጣዖት ስገጂ ፈጣሪሽን ካጂ ቢሏት፣ የዚህን ምሥጢር የሚያውቅ የሦስት ዓመት ሕፃን አለ፤ እሱን ጠይቁት አለቻቸው፡፡

 ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› (መዝ. ፻፴305)፡፡ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ፈራች፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው፡፡ ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን ‹‹እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ›› አላት፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም ‹‹ልጄ የነፍስ አባት

Read more: ሐምሌ 19 - ቅዱስ ገብርኤል

ጴጥሮስ ወጳውሎስ (ሐምሌ 5


 ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ

ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19

ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣን ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ አንተ እንድመጣ አሰናብተኝ ብሎ በባሕር ላይ ሲሄድ በመሞከሩ ማቴ. 6፥45፣ ፈጣንነቱ ጌታ ደቀመዛሙርቱን በቂሣርያ ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ጠይቋቸው ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ፈጥኖ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ  ክርስቶስ ነህ ብሎ በመመለሱ ማቴ. 16፥16 ቁጡነቱም አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቶጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ በመቁረጡ ዮሐ. 18፥10 ላይ ያስረዳል፡፡ መዋዕለ ስብከቱ 50 ዓመት ነው፡፡ /ገድ ሐዋ፣ ዜና ሐዋ/

Read more: ጴጥሮስ ወጳውሎስ (ሐምሌ 5

ሕንጸተ ቤታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም

እመቤታችን በዐረገች በ4ዓመት ጳውሎስና በርናባስ ፊልጵስዩስ ገብተው አስተማሩ፤ ሕዝቡም አምነው ተጠመቁ እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሒዱ አሏቸው የለመድነውን ከከለከላችሁንማ መካነ ጸሎት ስጡን አሏቸው፡፡ እንዲህ ብንላቸው እንዲህ አሉን ብለው ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስ ላኩ አልቦ ‹‹ዘትገብሩ ወኢምንተኒ ዘእንበለ ትእዛዙ ወምክሩ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ›› ያለጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባም እናንተም ጸልዩ እኛም እንጸልያለን ብለው ላኩባቸው፡፡ ሱባዔ ሲጨርሱ በዚህ ዕለት ጌታ በሩቅም በቅርብም ያሉ ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ዮሐንስ ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን ብሎ ጠየቀ ጌታም በእናቴ ስም ጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው አለው፡፡

 

Read more: ሕንጸተ ቤታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም

ዘመነ ጰራቅሊጦስ

በበዓለ ሠዊት ካህናተ ኦሪት ዓሥራቱን' በኩራቱን' ቀዳምያቱን ይቀበሉበት ነበርና ይህ በዓል በዘመነ ኦሪት በዓለ ሠዊት ይባል ነበር፡፡ በዓለ ጰራቅሊጦስም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለውበታልና ከዘመነ ሐዋርያት ወዲህ በበዓለ ሠዊት በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል፡፡ ከዚሁ ዘመን በኋላም ተያይዘው ጾመ አስቴር' ጾመ ዮዲት የሚባሉ አጽዋማት ነበሩአቸው፤ በጾመ አስቴር የእስራኤል ምክረ ሞት ተፈጽሞበት ነበር፡፡ ኋላም ረቡዕ የጌታ ምክረ ሞት ተፈጽሞበታልና በዘመነ ሐዲስ ጾመ ረቡዕ ገብቶበታል፡፡ በጾመ ዮዲትም እንዲሁ ሆለሆርኒስ ድል ተደርጎበታል፡፡ በዘመነ ሐዲስናም በዕለተ ዓርብ ዲያብሎስ ድል ሆኗልና በጾመ ዮዲት ጾመ ዓርብ ገብቶበታል፡፡

ዘመነ ጰራቅሊጦስ የሚባለው ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ ከሃምሳኛው ቀን ጀምሮ ቀጥሎ እስከ አለው እሑድ ድረስ ያለው 8 ቀን ነው በዚህም መሠረት ከትንሣኤ እስከ ጰራቅሊጦስ /እስከ ወረደ መንፈስ ቅዱስ/ 58 ቀን ይሆናል፡፡ . . .

Read more: ዘመነ ጰራቅሊጦስ

የፍቅር ስጦታ

 በፍጹም ምራው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዐቢይ ጾምን በሦስት ክፍል ስትጾም ቆይታለች፡፡ ይህም ማለት የመጀመሪያውን ሳምንት ንጉሥ ሕርቃል የሚታሰብበትን 40ውን ቀን ጌታችን በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመውንና የጸለየውን በማሰብ የመጨረሻውን ሳምንት ደግሞ ሰሙነ ሕማማት በማለት ሰቆቃውን፣ መከራውን፣ የደረሰበትን እንግልትና ስቃይ በምንባባቱ፣ በዜማው፣ በስግደቱ ስታስብ ሰንብታለች፡፡

የጌታችን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ፍቅር ለበደለው ለሰው ልጅ የተዋለ ውለታ ነው፡፡ ‹‹በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸከመ . . . በእርሱም  ቊስል እኛ ተፈወስን፡፡›› ኢሳ. 53፥4 እንዳለ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማስተሥረይ መከራ ተቀበለ፡፡ ለባሕሪው ሕመም ድካም ሞት የሌለበት አምላክ አትብላ የተባለውን ዕፅ በልቶ ለዘመናት እግዚአብሔርን የመሰለ ጌታውን ገነት የመሰለ ቦታውን አጥቶ በዲያብሎስ ሲወገርና ሲቀጠቀጥ የነበረውን የሰውን ልጅ አዳምን መስሎ የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ ካሳ መክፈል የሚገባው ሰው ሆኖ ሳለ በአዳም ተገብቶ እሱ ራሱ እውነተኛ ካሳ ሊከፍል ተገረፈ፣ ተወገረ፣ ተሰቀለ፣ ሞተ፡፡ ሠለስቱ ምዕት በጸሎተ ሃይማኖታቸው ‹‹በጲላጦስ በሹመት ዘመን ስለእኛ ታመመ ስለእኛም ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ›› ብለው ስለኛ የከፈለውን ክፍያ ይናገራሉ፡፡ እንግዲህ ይህ የሚያሳየው ቤተክርስቲያናችን ትንሣኤከ ብላ ከመዘመሯ አስቀድማ ሕማሙንና መከራውን በእንባ በስግደትና በፍጹም ሐዘን ማሰቧ የደስታህ ብቻ ሳይሆን የመከራህም ተካፋይ ነን ስትል ነው፡፡ ይህ ሥርዓቷ ደግሞ ከሁሉም ፋሲካን እናከብራለን ከሚሉ አካላት ይለያታል፡፡

Read more: የፍቅር ስጦታ

አርብ /ስድስተኛው ቀን/

አርብ /ስድስተኛው ቀን/

  ይህች ቀን አዳም ኋላም ሔዋን የተፈጠሩባት፣ ከገነት ተሰደው የወጡባት ዕለት ናት፡፡ ጌታም ቀድሞ የሥነ ፍጥረት ሥራውን እንደፈጸመበት አሁንም የድኅነት ሥራውን ፈጸመባት፡፡ በዚህች ዕለት በአምላካችን ላይ የተፈጸመው መከራ እጅግ አሰቃቂ ነበረ በፍጡርም ሊገለጹ የማይችሉ ናቸው፡፡

የክብርን ባለቤት ጭፍሮች ይዘው በሊቀ ካህናት ቤት አቀረቡት፡፡ ሊቀ ካህናቱም ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆንክ ንገረን›› አለው ጌታም ‹‹አንተ አልህ . . . የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ›› ቢለው ሊቀ ካህናቱ ተሳደበ በማለት ፊቱን ነጨ ልብሱን ቀደደ፡፡ በኦሪት ሕግ እንዲህ ያደረገ ይሻር ትል ነበር፡፡ ጌታ እንደተሾመበት እርሱ እንደተሻረበት ለማጠየቅ፡፡

ጌታ እንደተናገረው ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ ካደው በዚህ ጊዜ ዶሮ ጮኸ ጌታ ያለውን አስታውሶም እንዲህ ሲል አለቀሰ ‹‹ከሁሉ ይልቅ እኔ እወደው ከሁሉ አስቀድሞ እኔ እክደው›› ብሎ ከልቡ ስላለቀሰ ንስሐውን ተቀብሎታል፡፡

ማቴ. ፳6፥፷9-፸5      ማር. 04፥፷6-፸2

Read more: አርብ /ስድስተኛው ቀን/

Page 16 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine