በዓለ ደብረ ዘይት

የዐቢይ ጾም የአምስተኛው ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት የዳግም ምጽአቱን ነገር ማስተማሩ ይነገርበታል፡፡ ደብረዘይት የስሙ ትርጓሜ የዘይት ተራራ ማለት ነው ስያሜ የተሰጠው በቦታው ብዙ ወይራ ተክል ይበቅልበት ስለ ነበር ነው፡፡

እርሱም በደብረዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው?›› አሉት ማቴ. 24፥3 ስለ ጌታ መምጣት    ዘካ. 14፥5 ፤ ሐዋ. 1፥11 ፤ 1ኛ ተሰ. 4፥16 ፤ ራዕ. 22፥7 Read more: በዓለ ደብረ ዘይት

ጸንተን እንጠብቀው

የደብረ ዘይት መዝሙራት

 ጸንተን እንጠብቀው

ከመላእክት ጋራ ሲገለጥ በሰማይ

ጸንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ

በግርማ ሲመጣ በአስደንጋጭ ሁኔታ

ወዮልሽ ነፍሴ ሆይ ወየው የዛን ለታ

            ኧኸ ምስጋና ይድረስ ሁልጊዜ ጠዋት ማታ

            ሀሌ /2ጊዜ/ ሉያ የሠራዊት ጌታ /2ጊዜ/

ሰማይና ምድር ከፊቱ ሲሸሹ

መግቢያ አቶ ይጮሃል ትልቁ ትንሹ

ጻድቃን ሲደሰቱ የኃጥአን ፋንታ

ሆኖ ጠበቃቸው ለቅሶና ዋይታ

            ስለማይታወቅ አምላክ አመጣጥህ

            በሃይማኖት አጽናን ጸንተን እንጠብቅህ

            ጠላት እንዳይገዛን በእርሱ እንዳንረታ

            እግዚአብሔር አድነን ሁንልን መከታ

የነነዌ ጾም /ለሕፃናት/

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 

ፍሬሕይወት ጸጋዬ ዘኆኅተ ብርሃን

 

የነነዌ ጾም /ለሕፃናት/

 

እንደምን አላችሁ ልጆች? እንኳን ለነነዌ ጾም በሰላም አደረሳችሁ ስለ ነነዌ ጾም እነግራችኋለው በደንብ ተከታተሉኝ፡፡

 

በአንዲት መንደር የሚኖር አንድ ስሙ ዮናስ የሚባል ሰው ነበረ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን እግዚአብሔር ወደ እርሱ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ተነሥተህ ወደ ነነዌ ከተማ ሂድ፤ሕዝቡ ኃጢአት ስለሠራ ልቀጣቸው ነው፡፡ አንተ ግን ሔደህ ብታስተምራቸው እነሱም ከጥፋታቸው ቢመለሱ እኔም እምራቸዋለሁ” አለው፡፡ ዮናስ ግን የእግዚአብሐርን ትዕዛዝ ወደ ጐን ትቶ ተርሴት ወደምትባል ሀገር በመርከብ ተሳፍሮ ጉዞውን ጀመረ፡፡ በጉዞውም ላይ አስቸጋሪ ነገር ገጠመው መርከቧ በማዕበል ልትገለበጥ ደርሳ ስለነበር በውስጧ ያሉ ሰዎች እጅግ ተጨነቁ፡፡ አምላካቸው ከደረሰባቸው ችግር ያወጣቸው ዘንድ ይማፀኑ ነበር፡፡ ወዲያው ከመካከላቸው አንዱ ተነሥቶ “ይህ ነገር በማንኛችን ጥፋት ሊደርስብን እንደቻለ እጣ እንጣጣል አለ፡፡” ሁሉም በሀሳቡ ስለተስማሙ እጣው ሲጣል በዮናስ ላይ ወጣ ይኽን ጊዜ ዮናስም የአምላኩን ትዕዛዝ ሳይቀበል ከእርሱ ሸሽቶ መምጣቱ ስህተት እነደሆነ ስለተረዳ ጥፋተኛ መሆኑን ገልጾ ወደባሕር ውስጥ ጣሉኝ አላቸው፡፡ እነሱም ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ እግዚአብሔር ግን ምንም እንኳን ዮናስ ጥፋት ቢሠራም በባሕር ውስጥ እንዲሞት አልፈቀደም፡፡ አንድ ትልቅ ዓሣ ልኮ ዮናስን እንዲውጠው አደረገ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ ሆድ ውስጥ ካደረ በኋላ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ዓሣው ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው፡፡

Read more: የነነዌ ጾም /ለሕፃናት/

ጾመ ነነዌ

 

                      በየመንዝወርቅ ኪዳኔ ዘኆኅተ ብርሃን

 ጾመ ነነዌ

ጾም ማለት ከቃሉ ብንጀምር ከሥጋ ፈቃድ መከልከል መወሰን በደልን አስቦ ሥጋን አድክሞ ነፍስን ማዳን ማለት ነው፡፡ በጾም የሚገኘውን በረከት የሚያውቀው ክርስቲያን ብቻ ነው፡፡ አዳም አምላኩ ካዘዘው ቃል ወጥቶ ከአምላኩ እቅፍ ከወጣ በኋላ ወደ አምላኩ የተመለሰው በጾም እና በጸሎት ነው፡፡ በደሉን አውቆ የሚፀፀት፣  ንሰሐ የሚገባ እና የአምላኩን ትዕዛዝ የሚፈጽም ሰው ዘወትር ከአምላኩ ጋር ነው፡፡

 እኛም በክርስቶስ አምላክነት እና በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ ለሚያምኑ ክርስቲያኖች በሙሉ እንኳን ለዚች ለተቀደሰች ጾም በሰላም አደረሳችሁ እያልን ይኸችን ጾም የነነዌ ሰዎችን በዮናስ አማካኝነት በሦስት ቀን ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት አማካኝነት የዳኑበት ሲሆን፣ የሰው ልጅም ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ከተጸጸተ እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጥ የተረዳንበት ጾም ናት፡፡ ይህች ጾም የሦስት ቀን ብትሆንም   ብዙ በረከት እና ረድኤት የምናገኝባት ጾም ነች፡፡ በዚህም ጾም የነነዌ ሰዎች ከትልቅ እስከ ትንሹ ንጉሡንም ጨምሮ ልባቸውን ሰብረውና ተጸጽተው አምላክ ምሕረትን ይሰጣቸው ዘንድ ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው የጸለዩበት ጊዜ ነው፡፡ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርም ከልብ መጸጸታቸውን አይቶ ከቁጣው ተመልሶ ሊመጣባቸው ከነበረው ጥፋት ድነዋል፡፡ እኛም ክርስቲያኖች ይህን በማዘከር ንስሐ ብንገባ እንደ ነነዌ ሰዎች ከተቃጣው ማንኛውም መቅሰፋት እንድናለን፡፡ በማለት በየዓመቱ ከዓብይ ጾም መግቢያ ሁለት ሳምንት አስቀድሞ ካለው ከዕለተ ሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ “ጾመ ነነዌ” በማለት እንጾማለን፡፡

 እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ የሚመጣብንን መቅሰፍት የሚያይ አምላክ ከሚመጣብን መከራና መቅሰፍት ሁሉ ይጠብቀን እመ ብርሃን ቅድስት ድንግል እናታችን በምልጃዋ አትለየን፡፡ አሜን!!!

 

 

የ5 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ (ከ2005ዓ.ም - 2009ዓ.ም)

{edocs}files/HohiteBirhan5YearStrategicPlan.pdf,100%,400{/edocs}

9ኛ ዓመት

እንኳን ለ9ኛ ዓመት የሰንበት ትምህርት ቤታችን የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

እነሆ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ይህን ታሪካዊ ቀን ሲያከብር በዚች ዕለት የተቀበላትን የቤተክርስቲያን ኃላፊነት በመዘከርና ወደ ፊቱም ከሰ/ት/ቤቱ ሆነ ከምእመናንና ከሌሎች ሰ/ት/ቤቶች ጭምር ምን እንደሚጠበቅባቸው በማስገንዘብ ጭምር ነው፡፡ ይህን የሰ/ት/ቤቱን እና የቤተክርስቲያኒቱን ልደት ስናከብር ይህ በዓል የሰ/ት/ቤቱ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ጭምር መሆኑን በማስታወስ ነው ዛሬ በዚች ቦታ ለማክበር ወዳችሁ ሽታችሁ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ከሰ/ት/ቤቱ በአካል ርቃችሁ የምትገኙ የሰ/ት/ቤቱ አባላት እና ይህ መልእክት የሚደርሳችሁ ምእመናን በሙሉ በተጨማሪም በሥራ ምክንያት ከአገር ወጥታችሁ በተለያዩ አገሮች የምትኖሩ፣ በዩኒቨርስቲና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ተበታትናችሁ ያላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች በሙሉ እንኳን ለሰ/ት/ቤቱ የዘጠነኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አደረሳችሁ፡፡

ይህች ታሪካዊ ቀን ለሰ/ት/ቤቱም ልጆች ሆነ ለአንባቢው ምዕመን ልዩ ቀን ናት እንደ እግዚአብሔር ቸርነትና እንደ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በተለያየ ስፍራ የምንገኝ ልጆቿን ስብስባ አንድ አድርጋ በመንፈሳዊ ሕይወት እንድንታነፅ በምግባር እንድንበለፅግ የተጠራንበት ዕለት ናት፡፡ ብዙዎቻችን በዚች እቤት እንድንኖርባት እና የነገዋን ቤተክርስቲያን ተረካቢዎች እንድንሆን አደራ የተቀበልንባት ቀን ብትኖር ይህች ዕለት ናት፡፡ ዛሬ እኛ የተቀበልነው ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን አደራም ጭምር ነው፡፡ ይህ አደራ ደግሞ ሰማያዊ አደራ ብቻ ሳይሆን ምድራዊ አደራ ጭምርም ነው፡፡ ዛሬ ከኛ ቤተክርስቲያን አለሁልሽ የሚላት በምግባሩና በሕይወቱ የሚመሰክርላትን ልጆች ትሻለች፤ ዛሬ ቤተክርስቲያን እሳቱን የሚያበርድላት ልጆችን  ትፈልጋለች፤ዛሬ ቤተክርስቲያን በሥነ ምግባር የታነፀ በሃይማኖት በመንፈሳዊ እውቀት የበለፀገ ክርስቲያን ትፈልጋለች፡፡ ለዚህ ሁሉ ሀላፊዎች ደግሞ አደራው የተሰጠው ለቅርብ ተጠሪዎች ለሰ/ት/ቤት ወጣቶችና እና በአገልግሎት ላይ ያሉ መሰል ሰ/ት/ቤቶች ጭምር ነው፡፡ ይህ አደራ ደግሞ በውስጧ ላለን ልጆቿ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ምዕመናንም ጭምር ነው፡፡ ስለሆነም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላችሁ የሰ/ት/ቤቶችን ምዕመናን በሙሉ በተሰጠን ጸጋ እግዚአብሔርን እንድናገለግለው ቤተክርስቲያናችን ተስፋፍታ ምዕመኖች ሁሉ የክርስቶስን ሥጋና ደም ተቀባዮች እንዲሆኑ ወንጌል ያልደረሰባቸው ሀገራት ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል እንዲደርሳቸው ሁላችንም ሃላፊነታችንን አንድንወጣ ሰ/ት/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ሰንበት ት/ቤቱ ራዕይም ነገ የቤተክርስቲያን ልጆች የቅድስት ቤተክርስቲያንን እምነት ሥርዓት ሀብት ለመጪው ትውልድ የሚያስረክብ በሃይማኖት በምግባር የታነፀ በዓላማዊና በመንፈሳዊ እውቀት የበሰሉ ክርስቲያን ሲኖር ማየት ነውና ራዕይዋ ጎኖ በመሆን ራዕዩን እንድናሳካ የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ጸጋና በረከት አይለየን፡፡ አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Page 13 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine