መስከረም 10 ጼዴንያ ማርያም

  በደሳለኝ አላምሬ ዘኆኅተ ብርሃን

          በሀገረ ደማስቆ በጼዴንያ ክፍል በመሪና ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች ፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጱያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም መሽቶበት በእንግድነት አድሮ ጧት ሊሄድ ሲነሳ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱን አውቃ የእመቤቴን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ አለችው ገንዘቡን ሳመጣልሽ ትሰጭኛለሽ ብሏት ሄደ ፡፡

        ቅዱሳት መካናት እጅ ነሥቶ ሥዕሉን ዘንግቶ ሳይገዛ ሲመለስ አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያች ሴት ያለችህን ለምን እረሳህ የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ ተመልሶ ሂዶ ገዝቶ በረሃውን በረሃውን ሲሄድ አንበሳ መጣበት፡፡ ፈርቶ ሲጨነቅ ከስእሉ ድምፅ ተሰምቶ አንበሳው ሸሸ፡፡ ሁለተኛ ሁለት ሽፍቶች አግኝተውት ሲፈራ እንደቀድሞው አይነት ድምጽ ከሥዕሉ ተሰማ፡፡ ምን መጣብን ብለው ሸሽተዋል፡፡

Read more: መስከረም 10 ጼዴንያ ማርያም

መስከረም 10 ዕረፍታ ለዮዲት ነቢይት

                                                                                     በደሳለኝ አላምሬ ዘኆኅተ ብርሃን               

       አባቷ ሜራሪ ይባላል ሕጋዊ ባል አግብታ ትዳር መሥርታ ስትኖር የነበረች ናት፡፡ ባሏም ምናሴ ሞቶ ከእንግደህ ወደ ግብረ ዓለም አልመለስም ብላ በጾም፣ በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ የፋርስ ንጉሥ ፍስዮስ (ምክሀስዮስ) ሌላ ስሙም ናቡከደነጾር አርፋስክድን ድል  ነሥቶ ከባጥና ሲመለስ ቢትወደድ ሆሎፎርኒስን ግብር እንዲያስገብር ላከው፡፡ እርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገሰግስ በደብረ ቤልጥዋ ከምርኮ የተመለሱ እስራኤላውያን ጎጆ ሠርተው ይኖሩ ነበርና አንሰው ቢያያቸው እነዚህ ምንድን ናቸው? አለ፡፡ አክዮር የተባለ ሰው ጌታዬ የእነሱ ነገር ድንቅ ነው በኢየሩሳሌም ሳሉ ኃጢአት ቢሠሩ ጣዖት ቢያመልኩ አምላካቸው አስማረኳቸው ሰባ ዘመን በፋርስ ባቢሎን ኖሩ፡፡ ኋላ ግን ንስሐ ቢገቡ አምላካቸው ታረቃቸው አህዛብንም ድል አድርገው ባሕር ተሻግረው ወጥተዋል፡፡ አሁንም ተጣልቷቸው ከሆነ አንድ ብላቴና ብትልክ ማርኮ ያወጣሀል ያልተጣላቸው ከሆነ ግን ልታሸንፋቸው አትችልም አለው፡፡

Read more: መስከረም 10 ዕረፍታ ለዮዲት ነቢይት

አንዲት ድንግል

                                                                                                                                                                                                                                                        

በመ/ር ሳሙኤል አስረስ ዘደብረ ኤልያስ

ስለ ድንግል ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ስንመረመርና ስንመለከት እግዚአብሔር ለሌላ ለማንም ሳይሰጥ ለእርሷ ግን የሰጣትን ልዩ ጸጋ እናገኛለን፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኤልሳቤጥ በተመሳሳይ ቃል ‹‹አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ›› ብለው ያመሰገኗት፡፡ ሉቃ. 1፥28፣1፥42

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሐሳብ ያልተረዱ ብዙዎች ግን ስለ እርሷ ሲነገር ለመከራከር ቁጭ ብድግ የሚሉ ምስጋናዋ ሲነሳ ሆድ ቁርጠት የሚለቅባቸው አረፋ የሚያስደፍቃቸው ብዙ ናቸው፡፡ እንግዲ ምን እንላለን ከእግዚአብሔር የሆነን የእግዚአብሔር የሆኑትን አውቆ ክብር ይሰጣል፡፡

ስንጀምር የእግዚአብሔር ሐሳብ እና ቋንቋ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው የተጻፈው ግን በሰው ቋንቋ ነው፡፡ እንግዲ ከቋንቋው በስተጀርባ ያለውን የእግዚአብሔርን ሐሳብና ፈቃድ ለመረዳት መሪ ወይም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስፈልጉናል፡፡ አልያም ለክርስቶስ የልደት ዘመን ከቀረቡ በመንፈሳዊ ዕውቀት ዳብረው ቤተክርስቲያንን በመከራና በእሳት ውስጥ ካገለገሉ ቅዱሳን አባቶች የተገኘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ማየትና መመልከት ይጠበቅብናል፡፡

ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ‹‹በእውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?›› ብሎ ሐዋርያው ፊልጶስ በሰረገላ ላይ ሆኖ ስለሚያነበው የነቢዩ የኢሳይያስን ትንቢት ትርጉም በጠየቀው ጊዜ እንዲህ ነበር ያለው ‹‹የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?›› የሐዋ. 8፥30

ወደ ትምህርቱ ዓላማ ስንመጣ በሉቃስ ወንጌል የተጻፈውን ‹‹አንዲት ድንግል›› የሚለውን ቃል ስናገኝ እንደ ቀልድ አንብበን አልፈነው ይሆናል፡፡ ግን ብዙ ትንታኔና አንድምታ የበዛው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ‹‹አንዲት ድንግል›› የምትለዋ ሐረግ በራሷ ያለ ምክንያት አልተጠቀሰችም  በቀጥታ የእመቤታችንን ማንነት የሚያመለክቱ በርካታ ቁም ነገሮችን ታስከትላለች ዋና ዋና የምንላቸውን በማብዛት ሳይሆን በማሳነስ በማስረዘም ሳይሆን በማሳጠር እነሆ፡፡

Read more: አንዲት ድንግል

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል

መላእክት የሚለው ቃል መልእክተኞች' ተላላኪዎች' የእግዚአብሔር ይቅርታ ወደ ሰው የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ' የእግዚአብሔር ልዩ ወዳጆች ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ አለቆች ገዥዎች ወይም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ማለት ይሆናል፡፡

ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ እግዚአብሔር' እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?›› ማለት ነው፡፡ ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል /ዳን.10፥13' 2፥1/ ውስጥ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክም ለበርካታ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ሌላ በብሉይ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍት በኪዳነ አብርሃም ውስጥ ተጠቅሶም ይገኛል፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› /ዳን.12፥1/ በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› /ዳን. 10፥13/ በማለት ያስረዳል፡፡ በዚህ ቃል ላይ ከዋንኞቹ አለቆች አንዱ የሚለውን በመያዝ ሚካኤል ብቻ የመላእክት አለቃ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን የሌሎች አለቅነት የተወሰነ ወይም ዝቅተኛ ሲሆን በአንድ ነገድ ላይ በአንድ የመላእክት ከተማ ላይ ነው፡፡ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት ግን በመላእክት ሁሉ ላይ ከሆነ ከሌሎቹ ይለያል፡፡ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ እንደተገለጸው ሰባት ሊቃነ መላእክት ቢኖሩም አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

Read more: ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል

Page 12 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine