ጥቅምት፡- 25 ዕረፍቱ ለአባ ቡላ (አቢብ )

        ቡላ ማለት ፍሬ ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ሐሪክ ልጅ አጥተው ሲያዝኑ በአንድ መልአክ የበሰለ ፍሬ ሲሰጣቸው አይተው ጸንሰዋቸዋልና፡፡ በተወለደም ጊዜ ከደጃቸውም ታላቅ ዛፍ በቅሎ  በቅጠሎቹም ላይ ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር የሚል ጽሑፍ በሮማይስጥ ቋንቋ ተጽፎ ተገኝቷል፡፡ ይህን እያደነቁ ዓመት ያህል ሳያስጠምቋቸው ቢቆዩ እመቤታችን ለሊቀ  ጳጳሳት ተገልጻ ከደጃቸው ይህን ምልክት ታገኛለህ ሕፃኑን ተቀብለህ አጥምቀው ስሙንም ቡላ በለው አለችው፡፡ ተቀብሎም አጥምቋቸዋል፡፡ ሲጠመቁም አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ አባት እናታቸው ገና በልጅነታቸው ሞተዋል፡፡ በ10 ዓመታቸው ሃይማኖታቸውን ካዱ ለጣዖት ስገዱ የሚል ዐላዊ ንጉሥ ተነሣ፡፡ ሄደው ዘለፉት ሕፃን ነው ልራራለት ሳይል በችንካር አስቸንክሮ ገደላቸው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በዘንጉ ነክቶ አስነሣቸው፡፡ ከሌላው ዐላዊ ሄደው መሰከሩ፡፡ በሰይፍ አስመትቷቸዋል፡፡ቅዱስ ሚካኤልም አንስቶ ከበረሃወስዶ ልብሰ ምንኩስና አልብሷቸው ቆብ ደፍቶላቸው ሄዷል፡፡  

        አባ ቡላ በእድሜ ትንሽ ቢሆኑም ቅሉ መንፈስ ቅዱስ ከኃጢአት ስላነጻቸው ለተጋድሎ ጽኑዕ አድረጓቸዋልና ከእድሜ ባለጸጋዎች በላይ በጾም በጸሎት ተወስነው በትምህርት ኗሪ ሆነዋል፡፡ ሥጋቸውን ለማድከም ሰውነታቸውን ሲገርፉ ፊታቸውን ሲነጩ ይኖሩ ነበር፡፡ የጌታም ሕማሙን ሞቱን እያሰቡ ከዛፍ ላይ ራሳቸውን ይወረውሩ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ጸንቶባቸው በደወቁበት ሞቱ፡፡ ጌታ 4 ባሕርያተ ሥጋ 3 ግብራተ ነፍስ አስማምቶ አስነስቶ እንግዲህ የብዙኃን አባት ትሆናለህና ስምህ አቢብ ይሁን ብሏቸዋል፡፡ አቢብ ማለት አቢብ ብዙኃን /የብዙዎች አባት/ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የጌታን ሕማሙን ሞቱን እያሰቡ 40 ዘመን እህል ውኃ ሳይጠጡ 12 ዓመት 6 ወር በራሳቸው ቆመው ሲያዝኑ ሲያለቅሱ ኖረዋል፡፡ በመጨረሻም ከዛፍ ወድቀው በጦር ተወግተው ዐርፈዋል፡፡ እመቤታችን መላእክትን አስከትላ መጥታ ‹‹ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ አቢብ›› አለቻቸው፡፡ በድናቸው ተነስቶ ሰላም ለኪ ኦ ንግሥተ ሰማያት ወምድር ብሎ እጅ ነስቷል፡፡ ጌታም ከሞት አስነስቶ በተስፋህ ያመነውን በቃል ኪዳንህ የተማጸነውን ሁሉ እሰከ 10 ትውለድ ድረስ እምርልሃለሁ ብሎ ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይቶ በስሐበተ መላእክት በቃለ አቅርንት አሳርጓታል፡፡

የጻድቁ በረከት ቃል ኪዳን ተካፋዮች ያድርገን አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር  

በደሳለኝ አላምሬ ዘኆኅተ ብርሃን

 

ስለ ጽድቅ የሚስደዱ ብጽዓን ናቸው፡፡ ሜቴ 5፥10

 

 

                   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

    በክርስቶስ ክረስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማርያም የአሥራት የበርከት ልጆች በወደደንና በመረጠን በአምላካችን በልዑል እግዚአብሔር ሰላምታ እንደምን ሰነበታችሁ  አመላካችን ቢወድና ቢፈቅድ ወቅቱን በተመለከተ ስብከት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡  የምናስተውሉበትን ልቦና ልዑል አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን ለሁላችን ያድለን፡፡   

      ቃሉን የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንቀጸ ብፁዓን ተብሎ በሚጠራው በተራራው ስብከቱ ነው፡፡ የቃሉን ፍቺ ስንመለከት ስለ ጽድቅ የሚስደዱ ብፁዓን ናቸው ማለት ስለ እግዚአብሔር ፍቅር፣መንግሥት፣ በረከት፣ ረድኤት ብለው ከትውልድ ሀገራቸው ተለይተው ከከተማ ከሕዝብ ርቀው በምድር የላመ የጣመ ምግብ  ሳይመገቡና ሣይጠጡ  ለቁመተ ስጋ ብቻ ያገኙትን ቅጠል የሚመገቡ ይህችን ዓለም የጠሉ አባቶች እናቶች እነሱ የተመስገኑ ቅዱሳን፣ የተመረጡ ቡሩካን፣  የተለዩ ምስጉኖች ማለት ነው፡፡

1.1 ሰደት መቼ ተጀመረ ?

      በዓለመ መላዕክት ነው፡፡ እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ከፈጠራቸው ከሰባቱ ሥነ-ፍጥረታት ውስጥ  መላዕክት ናቸው፡፡ ከፈጠራቸው በኋላ የተሰወረባቸውም የእርሱን አምላክነት ምሀሪነት ሁሉን ቻይነቱን ይረዱ ያውቁ ዘንድ ተሰወረባቸው፡፡ የመላእከት አለቃ የነበረ ሳጥናኤል እኔ ፈጠርኳችሁ በማለት ብዙዎችን አሳተ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሚካኤል ሃይማኖታችንን እስከ ምናውቀው ባለንበት እንቁም(ንቁም በበህላዊነ እሰከ ንረክቦ ለአምላክነ) ብለው መላዕክትን አጽናኑ፡፡ ሳጥናኤልና ከሰማይ ወደዚህ ዓለም(ምድር) ተሰደዱ ስደትም በእዚያን ጊዜ ተጅመረ፡፡

 

Read more: ስለ ጽድቅ የሚስደዱ ብጽዓን ናቸው፡፡ ሜቴ 5፥10

መስከረም 21፡ ብዙኃነ ማርያም

በደሳለኝ አላምሬ ዘኆኅተ ብርሃን

 

       ይህ በዓል መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው የአርዮስ የምነፍቅና ትምህርት የእስክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ እለእሰስክንድሮስ አውግዞት በዚህ ምክንያት በጉባኤ እንዲደረግ የሮሙ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነቂያ ጉባኤ ይሁን ብሎ አዋጅ አስነግሮ በዚህ ዕለት ሃይማኖት ዶግማ አስቀምጠውልናል ፡፡

      ሁለተኛው መስቀልን ይመለከታል፡፡ ዐፄ ዳዊት ከግብጽ ጌታችን የተሰቀለበት ቀኝ እጁ ያረፈበት ዕፀ መስቀል የገባበትና ኢትዮጵያን እየዞረ ከባረከ በኃላ ዐፄ ዘርዕ ያዕቆብ በታዘዙት መሠረት ማለትም ‹‹መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ›› በዚህ ትእዛዝ መሠረት ግሸን ደብረ ከርቤ አስምጠውታል፡፡ ይህን በማስመልከት ከመስቀሉ በረከት ረድኤት ከቃል ኪዳኑ ተካፋይ ለመሆን መስከረም 21 ቀን ወደ ግሸን ጉዞ ደደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር

ወርኀ ጽጌ

ወርኃ ክረምት አልፉል፡፡ነጎድጓዱም ጸጥ ብሏል፡፡አእዋፍ ከየተሸሸጉበት ጉድባና ከሸሹበት ሀገር መሰብሰብ ጀምረዋል፡፡ ተራራውና ሜዳውም በአበባ አጊጦ ስጋጃ የተነጠፈበት መስሏል፡፡ተፈጥሮ እንዲህ ውብ ሆና በምትታይበት ወቅትም ቤተክርስቲያን ትምህርቷን ከወቅቱ ጋር አሰላስላና ሰምና ወርቅ አድርጋ ታቀርባለች፡፡ለዚህም አብነት የሚሆን ወርኃ ጽጌ ነው፡፡

      ከመስከረም 26 እስከ ታህሳስ 25 ያለው ጊዜ መጸው ወይም ጥቢ ይባላል፡፡ይህ ወቀት ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡እነርሱም ጽጌ፣አስተምሮ እና ስብከት ይባላሉ፡፡ እያንዳንዳቸውም የየራሳቸው የሆነ ሰፊ ትምህርት አላቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል የወርኃ ጽጌን ብቻ እንደሚከተለው እናያለን፡፡

‹‹ጸጌ›› የሚለው ቃል ‹‹ጸገየ›› ካለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም አበባ ማለት ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያሉት አርባ ቀናት ‹‹ዘመነ ጽጌ›› ይባላሉ፡፡ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ዘመኑን አስመልክቶ ማኅሌት ይቆማል፤መዝሙር ይዘመራል፡፡

Read more: ወርኀ ጽጌ

የሰንበት ት/ቤታችን ቋሚ አባላት በከፊል

Page 11 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine