ነቢየ እግዚአብሔር ዮናስ

 ዮናስ ማለት የዋህ ርግብ ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ነው፡፡ የተወለደው በሰራፕታ ነው፡፡ በዘመኑ የነበረ ነቢይ ኤልያስ ነው፡፡ ይህም ነቢይ  በዘመኑ ንጉሥ አክአብ ንግሥቲቱ ኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣዖት አቁመው ጣዖት ሲያመልኩ ተው ቢሏቸው አልመለስም ቢሉ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም እንዳይዘንም አድርጓል፡፡ 1ነገ.18፥1-46፤ ያዕ. 5፥17

ከዚህ በኋላ ምግቡን ያመላልሱለት የነበሩ ቁራዎች ቀርተውበት ውኃውም ደርቆበት ወደ ጌታ ቢያመለክት ‹‹ወደ ሰራፕታ ሂድ በዚያም አንዲት መበለት ሴት ትመግብሃለች›› ብሎት ሰራፕታ የዮናስን እናት አግኝቷት ‹‹ውኃ አጠጪኝ ጥቂት ቁራሽም አምጪልኝ›› አላት፡፡ ‹‹ሕያው እግዚአብሔርን እፍኝ ዱቄት አለችኝ ጋግሬያት አንተም እኔም ልጄም (ዮናስ) በልተናት እንሞታለን›› አለችው፡፡ ኤልያስም የረሀቡ ዘመን እስኪያልፍ ይበርክት አላት፡፡ ብትገባ ዱቄቱ በማድጋው ዘይቱ በማሰሮው መልቶ አገኘች፡፡

ልጅዋ ዮናስም ታሞባት በሞተ ጊዜ ሄዳ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስን ሳይገባኝ ከቤቴ ገብተህ ኃጢአቴን ተመራምረህ ልጄን ትገድልብኝ አለችው፡፡ እጁን ከእጁ እግሩን ከእግሩ ገጥሞ እየወደቀ እየተነሣ ቢጸልይ በሰባተኛው ተነሥቷል፡፡ 1ነገ. 17፥1-24

 

Read more: ነቢየ እግዚአብሔር ዮናስ

እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት

በስመ አብ ወወለድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አምላክ አሜን

በክረስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉድ በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኛችሁ  እግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የጻድቃን የሰማዕታት የቅዱሳን መላዕክት ወዳጆች በወደደን ባፈቀረን ስለ እኛ እራሱን አሳልፎ በሰጠን በልዑል እግዚአብሔር ሰላምታ አንደምን ሰነበታቸሁ፡፡ አሜን በግሩም ጥባቆቱ ጠብቆ በቸርነቱ ጎብኝቶ አስከ እዚች ስዓት ያደረሰን የአምላካችን ስም በእኛ በልጆቹ አንደበት ከትውልድ እስከ ትውልድ የተመሰገነ ይሁን አሜን፡፡ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢወድ በዓሉን በተመለከተ አጭር ትምህርት ይዤላችሁ ቀርቤአሉ የልድያን ልብ የከፈተ አምላካችን እኔ የምናገርበትን አንደበት ለእናንተ የምታስተውሉበትን ልቦናና አእምሮ አምላካችን ማስተዋል ጥበቡን ያድለን፤ ለአባቶቻችን የላከውን መንፈስ ቅዱስ ለእኛም ይላክልን፡፡

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኒት ተወልዶላችኋል ይኸውም ቡሩክ ክርስቶስ ነው፡፡ሉቃ2÷11

ቃሉን የተናገረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሲሆን የተናገረውም ለእረኞቹ ነው፡፡ የቃሉን ፍች ስንመለከተው ከሁሉም ታናሽ ክፍል በምትሆን በኤፍራታ ክፍል በቤተልሔም ነቢያት ተስፋ ያደርጉት ሱባኤ የቆጠሩለት የዓለም ሁሉ አዳኝ ፈዋሽ መድኃኒት ተወለደ፡፡ መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለበት በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል የዓለም መድኀኒት የሚሆን የባሕርይ አምላክ በዳዊት ከተማ ፍጹም ሰው ሆኖ ተወልዷልና፡፡ የነቢዩ ኢሳይያስም እንዲህ ብሎ የተናገረው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ በኛም መካከል ተመላለሰ ከኛም ጋር አደረ ሕሙማንንም ሲፈውስ ተመለከትን አየን አለ፡፡ ኢሳ 7÷14 ‹‹ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ›› ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች  ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡

Read more: እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት

ጸሎት /ለሕፃናት/

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ዛሬ ስለ ጸሎት ምንነት እን አደራረግ ዝግጅቱን በተመለከተ ትማራላችሁ፡፡ በደንብ ተከተሉኝ እሺ፡፡

ጸሎት “ጸለየ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ የቃሉ ፍችም አመሰገነ፣ ለመነ፣ ዘመረ ማለት ሲሆን ጸሎት ማለት ልመና ፣ ምስጋና ፣ ዝማሬ ይኸውም ከአምላክ ጋር መነጋገር ማለት ነው፡፡

ጸሎት የሚቀርበው ለእግዚአብሔር/ወደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ጌታችንም ”ለምኑ ይሰጣችኋል ፈልጉ ታገኛላችሁ ደጅ ምቱ ይከፈትላችኋል” ማቴ. 7፥7 በማለት መጸለይ እንደሚገባን አስተምሮናል፡፡

ጸሎት ጥቅም

ጸሎት ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ ለዚህ ትምህርት እንዲሁኑ ጥቂቶቹን እንደሚከተለው እንመለከታለን።-

-    እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቅመናል፡፡

-    በጸሎት በደላችንን ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር እንናዘዛለን(እንናገራለን) ይቅርታውንም እንለምናለን፡፡

-    ከእግዚአብሔር ዘንድ የፈለግነውንና የጎደለንን ለማግኘት ያስችለናል፡፡

-    መንፈሳዊ ኃይል እንድናገኝ ያስችለናል፡፡

እንግዲህ ጸሎት ይህን ያህል ጥቅም እንዳሉት ከተረዳን እንዴት መጸለይ እንደሚገባን እንደሚከተለው እንማማራለን፡፡

ጸሎት እደራረግ ሥርዓትና ዝግጅት

ልጆችዬ ጸሎት በቤተክርስቲያን በዘፈቀደ የሚከናወን ሳይሆን ራሱን የቻለ ሥርዓት ያለው ነው፡፡ ይህም ከመጸለያችን በፊት በቂ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ማድረግ የሚገባንን ዝግጅት ለመረዳት ያስችለን ዘንድ በሁለት ወገን ከፍለን እንመለከተዋለን፡፡ ከእነዚህም አንዱ ውጫዊ /አፍአዊ ዝግጅት/ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ ዝግጅት ነው፡፡ በዛሬው ትምህርታችን ውጫዊ /አፍአዊ ዝግጅቶች/ ውስጥ የሚጠቃለሉትና ማድረግ የሚገባንን እንመለከታለን፡፡

Read more: ጸሎት /ለሕፃናት/

ኅዳር 12 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ በዓል

ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡

ስለዚህ ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፤ ጠባቂነትና አማላጅነት ከአባቶቻቸው የተማሩትን በኑሮአቸው ያዩትን አባቶቻችን ጽፈዋል፡፡ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከጻፉት አባቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፡-

 + ዮሐንስ አፈወርቅ
+ ኤዎስጣቴዎስ ዘአንፆኪያ
+ ቅዱስ መቃርዮስ
+ ቅዱስ ያሬድ
+ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
+ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባዲማቴዎስ ናቸው፡፡

 እኛም የአባቶቻችንን አንደበት አንደበታችን አድርገን በኅዳር 12 ክቡር ገናና የሆነ ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸውና ከሠራቸው ብዙ ተአምራት ውስጥ የተወሰኑትን በመልአኩ ተረዳኢነት እንዲህ ብለን እንናገራለን አንጽፋለን፡፡

      ንግስት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ጣዖት የሠራችው ቤተ ጣዖት በእስክንድርያ ነበር፡፡ ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እስክንድርያው ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ እለ እስክንድሮስ ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝቡ ከልቡ ገና የአምልኮ ጣዖት ስላልጣፋ 18 ፓትርያርኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት በነበረው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንዲያከብሩ አውጆ ቤተ ጣዖቱንም በቅዱስ ሚካኤል ስም ሰይሞ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡ ከዚህ በኋላ በቅዱስ ሚካኤልም ስም አብያተ ክርስቲያናት መታነጽ ጀመሩ  በዓሉ በዚህ ቀን እንዲከበር ተወስኗል፡፡  

       

Read more: ኅዳር 12 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ በዓል

ኅዳር 6፡ ቊስቋም

 

 

እመቤታችን ጌታን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማዳን ረሀቡን ጽሙን ታግሳ 3ዓመት ከ6 ወር በስደት ቆይታለች፡፡ ራዕ 12÷1-6 ሄሮድስ ከክፋቱ የማይመለስ ቢሆን መላአኩ ሰይፍ መዓቱን መዞ ታይቶት ተልቶ ቆስሎ ሞቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ዮሴፍን የሕጻኑን ነፍስ የሚፈልገው ሰው ሞቷልና ከምድረ ግብጽ ወጥተው በረሀ በረሀውን ተጉዘው በዚህ ዕለት ደብረ ቊስቋም ገብተዋል፡፡ በአጠቃላይ ይህ በዓል እመቤታችን ከስደት መመለሷን በማስመልከት የሚከበር የሚዘከርበት ነው፡፡

ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ

ኅዳር 6፡ ዕረፍቱ ለቅዱስ ፊልክስ የሮሜ ሊቀ ጳጳስ

የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት አስተማሩት የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት እንጦንስም ዲቁና ሾመው ደግሞ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ዮስጦስም ጠባን ጽድቁንና የቱሩፋትን ደግነት አይቶ ቅስና ሾመው፡፡ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስስ በዐረፉ ጊዜ ይህን አባት ፊልክስን መረጡት በእግዚአብሔርም ፈቃድ በሮም ሀገር ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የክርስቶስንም መንጋዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ፡፡ ትሩስ ቄሳርም ከሞተ በኋላ ቴድሮስ ቄሳር ነገሠ እርሱም በምእመናን ላይ ታላቅ መከራን አብዝቶ ጭንቅን በሆነ ሥቃዮች አሰቃያቸው፡፡ ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡

ይህም አባት ከዚህ ከሀዲ ታላቅ መከራና ስቃይ ደረሰበት፡ ስለ እርሱም ወደ እግዚአብሔር ማለደ ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ከሀዲ በ2ኛው ዘመነ መንግሥቱ አጠፋው፡፡ ከዚህም በኋላ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ ጊዜ ክርስቲኖችን አብዝቶ ማሰቃየት ጀመረ፡፡ ይህም አባት ፊልክስ የክሪስቲያኖችን ስቃይ እንዳያይ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዲዮቅልጢያኖስም በመጀመርያው ዘመነ መንግሥቱ ዐረፈ፡፡ ይህ አባት ብዙዎች ድረሳናትንና ተግሳጾችን ደርሷል ስለ ውግዘትና ስለ ቀናች ሃይማኖት ተመላለሱበት አለ እነዚህም ለክርስቲያን ወገን እጅግ የሚጠቅሙ በጎዎች ናቸው፡፡

                                                                    ምንጭ፡ ስንክሳር

Page 10 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine