ተንስኡ ለጸሎት

በዓለ ሆሣዕና

በስምንተኛው ሳምንት የሚከበር ሲሆን ከጌታ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ሆሣዕና መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ይህም በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ በመቅደሱ ዙሪያ ያሉትን ለዋጮችና ሻጮችን ያስወጣበት' ቤተመቅደሱ የጸሎት ቤት መሆኑን ያወጀበትና ክብሩን የገለጸበት በዓል ነው፡፡ በዚህ ዕለት አቀባበል ያደረጉለት የሰው ልጆችም በቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ እንደተናገረው ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም›› እያሉ አመስግነውታል፡፡ ማቴ. 21፥9 በጊዜው የነበሩ ፊሪሳውያን ይህን የእርሱን የአምላክነት ክብር ባለመቀበላቸው የሚቀርብለትን ምስጋና በመቃወማቸው ጥያቄ አንስተው ነበር፡፡ እራሱ ግን የሚገባው እንደሆነ አስረግጦ ነግሯቸዋል፡፡

Hosaena
Read more: በዓለ ሆሣዕና

ኆኅተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ወደ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ጉዞ አዘጋጀች

በወለተ ትንሣኤ

‹‹መልካም ሥራ የክፉ ቀን ስንቅ ነው ››

በሰባተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት (ኒቆዲሞስ) የኆኀተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና የአካባቢው ምዕመናን  በሰንበት ትምህርት ቤቱ በጎ አድራጎት ክፍል አስተባባሪነት  እሑድ መጋቢት 20 ቀን ፣ 2007 ዓ.ም. በሕመም የተጎዱ ወገኖችን የመጠየቅ መርሐ ግብር ተከናውኗል ፡፡

Read more: ኆኅተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ወደ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ጉዞ አዘጋጀች

ጌርጌሴኖን

ጉዞ በጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ

ቅድስት

የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት 40 ቀን የጌታችን ጾም የሚጀምርበት ሳምንት ስለሆነ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡

‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ›› ዘጸ. 20፥8 ይህንን ቃለ እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሯል፡፡ ዕረፉባት  ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ባሕሪ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት/በመማር/፣ ንስሓ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረ በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ. 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ. 56፥4-8 ይህችንም ዕለተ ሰንበት ያላከበረ እንዲገደል ትእዛዝ ተሠርቶ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ለሙሴ ‹‹ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ፤ የሚያረክሰውም ሁሉ ፈጽሞ ይገደል÷ ሥራንም በእርሱ የሠራ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ፡፡ . . . ››ዘጸ. 31፥14-15 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋልና፡፡ ዘኁ. 15፥32-36

Read more: ቅድስት

መፃጕዕ

መፃጕዕ ማለት በሽተኛ /ድውይ/ ማለት ነው፡፡ ይህ ቀን የሚያመለክተው የሕመምተኞችን ብዛት የሸፈነው የአብ ጸጋ ክሂሎት ከፍጡራን መካከል ወደር ያልተገኘለት መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም ከብዙ ዓይነት በሽታ ከተያዙት በሽተኞች ብዛት ይልቅ በአንድ ጌታ ሥልጣን በብዙ በሽተኞች ላይ የሚካሄደው የፈውስ ጸጋ ጥበቡ በዓለም ላይ እጅግ የበዛ መሆኑ ነው፡፡ ጌታችን ከፈወሳቸው በሽተኞች መካከልም ረጅም ዕድሜ በሕመም ያስቆጠሩ ሰዎች ይገኙበታል፤ ይኸውም ዕድሜ ከ12 ዓመት እስከ 38 ዓመት የሚደርስ ነው፡፡ /ሉቃ. 13፥10 ማቴ. 9፥20/ እንዲሁም ከእናታቸው ማኅፀን ያለ ዓይን ብርሃን የተወለዱ ነበሩ፡፡ ከዚያም ባሻገር ሙተው የተነሡና በሕይወት ዘመናቸው በአጋንንት ፈተና የሚሰቃዩ ብዛት ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ፡፡ /ማቴ. 8፥28/ ይህ ታሪክ በየዕለቱ የሚነገር መለኮታዊ ተግባር ቢሆንም ቤተክርስቲያን ከዚህ ለየት ላሉት ትምህርተ መለኮትና ሥነ ምግባር ጊዜ ለመስጠት ይህን ታሪክ በሚያመች መልኩ ረጅሙን ታሪክ ሰብሰብ አድርጋ በዚህ በአራተኛው እሑድ ፈጣሪዋን ኢየሱስ ክርስቶስን ፈዋሴ ድውያን በማለት ታመሰግናለች፡፡ እንዲሁም በ4ኛው ክፍለ ዘመን /በዘመነ ነገሥት/ በፈሳሽ  ውኃ በሽተኞችን የማጥመቁ ሥርዓት በስፋት ይከናወን ስለነበር ይህ አራተኛ ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡

Read more: መፃጕዕ

Page 6 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine