ቅድስት

የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡ ‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህንን የመሰለ የሰንበት ቅድስናን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት 40 ቀን ጌታችን ጾም የሚጀምርበት ሳምንት ስለሆነም  ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡

የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ ዘጸ. 20፥8 ይህንን ቃለ እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሯል፡፡ ዕረፉባት ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ባሕሪ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍሰሐን ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡  በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት/በመማር/' ንስሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል' የተጣላ በማስታረቅ' ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሠረ በመጠየቅ' በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ .25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘለዓለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ. 56፥4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ. 15፥32-36

Read more: ቅድስት

ዐቢይ ጾም

እንኳን ታላቅ በረከትና ጸጋ ለምናገኝበት ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ለጾመው ለዐቢይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ፡፡ በበዓላት እንኳን አደረሳችሁ እንደምንባባለው ሁሉ በጾም መግቢያ ላይም እንኳን ለወርኃ ጾም አደረሳችሁ መባባል ይገባል፡፡ የጾም ወቅት የሚናፍቅ መሆን አለበት ምክንያቱም ጾም ፈቃደ ነፍስ ፈቃደ ሥጋን የምትገዛበት ከልዑል እግዚአብሔር የምንገናኝበት በረከት የምንቀበልበት ልዩ ወቅት ስለሆነ ነው፡፡ከአጽዋማት ሁሉ ታላቅ መሆኑን ስሙም ጭምር የሚጠቁመው ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከተጠመቀ በኋላ በገዳም ገብቶ 40 ቀንና 40 ሌሊት የጾመው ጾም ሲሆን በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፡፡ ማቴ. ፬ ከቁጥር ፩ ጀምሮ፡፡

Read more: ዐቢይ ጾም

የዐብይ ፆም ሳምንታት

ኅዳር 21 ፡- ታቦተ ጽዮን

እስራኤል በግብጽ ባርነት ሲኖሩ ጌታ ግብጻውያንን በዘጠኝ መቅሰፍት አሥረኛ ሞተ.በኵር በአሥራ አንደኛ ስጥመት አጥፍቶ ጸልየው እንዲድኑባት ሰውተው እንዲከብሩባት ታቦተ .ጽዮንን ሰጥቶ 40 ዘመን መና ከደመና እያወረደ ውኃ ከጭንጫ እያፈለቀ በሠናይ መግቦ ምድረ.ርስት አግብቷቸዋል ነህ 9 ፡21 ሐዋ 13፡18 ከዚህም በኋላ መስፍን ሲሞት መስፍን ካህን ሲሞት ካህን እየተተካ ሥርዓቱ ሳይጓደል ከዔሊ ደረሰ፡፡ ዔሊም ክህነት ከመስፍንነት አስተባብሮ ይዞ 40 ዘመን አስተዳድሮ ቢደክም አፍኒን ፊንሐስ የሚባሉ ልጆቹን ከበታቹ ሾማቸው፡፡ ይልቁንም ጌታን የሚያስቆጣ ሦስት ዐበይት ኃጣውእ ሠርተዋል፡፡ ሙሴ አሮን በሠሩት ሥርዓት በቀዳማይ ሰዓተ.ሌሊት በርቶ በቀዳማይ ሰዓተ.መዓልት ይጠፋ የነበረውን ፋና ከባዶ ቤት ሲበራ ቢያድር ምን ይረባል ብለው አስቀርተውታል፤ እስራኤል መስዋዕት በሚሰዉ ጊዜ ገና ስቡ ሳይጤስ የወደዱትን ሥጋ ነጥቀው ይበሉ ነበር፤ ሴቶችን ያስነውሩ ነበር፡፡

 

Read more: ኅዳር 21 ፡- ታቦተ ጽዮን

ኅዳር 21 እናታችን ጽዮን

በዚህ ጽሑፍ በጥቂቱ የምንመለከተው ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጣች፣ ኅዳር 21 ቀን ስለምናከብረው ዓመታዊ በዓል፣ በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ምስጢራዊ ትርጉም ነው፡፡ ታቦት አንቺ ነሽ» ብሏል፡፡

ታቦተ ጽዮን በፈቃደ እግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሰው ልጆች ተሰጥታ እስራኤላውያን ሲባረኩባት፣ መሥዋዕታቸውን ሲያቀርቡባት ከእግዚአብሔር ሲታረቁባት ኖረዋል፡፡ ከአራት ሺሕ ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ዓመተ ዓለም (4327 ዓ.ዓ) ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ያህል እስራኤላውያንን በክህነት ያገለግል የነበረው ካህኑ ዔሊ ዕድሜው ሲገፋ ሁለት ልጆቹን ጠርቶ ዋናና ምክትል አድርጎ ሾማቸው፡፡

 በደብተራ ኦሪት ታቦተ ጽዮንን እንዲያገለግሉ የተሾሙት ሁለቱ ወጣት ካህናት /አፍኒን እና ፊንሐስ/ ፈቃደ እግዚአብሔርን ተላልፈው ሦስት ታላላቅ በደሎችን ፈጸሙ፡፡ የመጀመሪያው በደል፤ በሙሴ ሥርዓት በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት በርታ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት የምትጠፋ መብራት እንድትቀመጥ የተሠራ ሥርዓት ነበር፡፡ ሆኖም አገልግሎት ከሌለ ሲበራ ማደሩ ለምን ? ብለው መቅረዙን አነሡ፤ መብራቱንም አጠፉ፡፡ ሁለተኛ፣ ለራሳቸው ሥጋዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው ለመሥዋዕት እንዲሆን ከመጣው እንስሳ ታርዶ ስቡ ሳይጤስ፣ደሙ ሳይፈስ ሥጋውን እየመረጡ ተመገቡ፡፡ ሦስተኛ ጸሎት እናደርሳለን ሥርዓተ አምልኮ፣ እንፈጽማለን ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጡ ከነበሩት እስራኤላውያን ቆነጃጅት ጋራ በዝሙት ወደቁ፡፡ አባታቸው ካህኑ ዔሊም የልጆቹን በደል እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ ቸል በማለቱ እግዚአብሔር አዘነ፡፡ በዚህም ምክንያት ፍልስጥኤማውያንን አስነሥቶ በጦርነት ቀጣቸው፡፡

Read more: ኅዳር 21 እናታችን ጽዮን

የምስራች ለልጆችና ለአዋቂዎቸ

Page 4 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine