ደብረ ዘይት

ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው፡፡ ደብር መባሉ ከፍታውን ሲገልጽ ዘይት ደግሞ አካባቢውን የሸፈነው የወይራ ዘይት ስለነበረ፤ ከፍሬውም ዘይት ስለሚገኝ ደብረ ዘይት ተብሏል፡፡ ይህም የወይራ ዛፍ የበዛበት መሆኑን ይገልጻል፡፡ ይህም ቦታ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ካለው ከቄድሮስ ሸለቆ ራቅ ብሎ የሚገኝ፣ ርዝመቱ 2 ኪሎ ሜትር ከፍታው ደግሞ ከኢየሩሳሌም ከተማ በላይ 62 ሜትር ያህል ከፍ በማለት ያለ ተራራ ነው፡፡ /ዘካ. 14፥4፤ ሕዝ. 11፥23/ ይህ ተራራ ጌታ የሚመጣበትን ምልክት የገለፀበትና /ማቴ. 24፥1/ የዚህን ዓለም ተልኮ ሲያጠናቅቅ የዐረገበት ተራራ ነው፡፡ /ሐዋ. 1፥12/ ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ከደብረ ዘይት ሲሆን ቤተ ፋጌና ቢታንያም የሚገኙት ከዚሁ ተራራ ግርጌ ነው፡፡ /ማር. 11፥1/  ይህ ደብረ ዘይት የሚባለው ሰንበት ስለምጽአት የተነገረበት ከመሆኑም በስተጀርባ በዚህ ዕለት ምጽአት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ስለ ቅድመ ምጽአቱ ምልክት በተናገረበት ተራራ ስም ደብረ ዘይት እየተባለ ይጠራል፡፡

 

Read more: ደብረ ዘይት

መፃጕዕ

በእንተ ሰሙነ መጻጒዕ
+++++++
1. ስለ ዕለቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ
2. በሽታ ምንድን ነው? ከምንስ ይመጣል? እግዚአብሔር ፈጥሮታል(ሥነ ፍጥረት ነው) ማለት እንችላለን?
3. ከበሽታ መፈወሻ መንገዶች ምን ምን ናቸው?
ቀንዲል፣ ጸበል ………
4. ፈውስን ለማግኘት ከኛ ምን ይጠበቃል? (ከመጻጒዕ ታሪክ ጋር ተገናኝቶ)
5. ቤተክርስትያን ዓለማዊ ሕክምናን እንዴት ታየዋለች? መንፈሳዊ እና ዓለማዊ ሕክምና አንድ ላይ ሊሄዱ ይችላሉ?

 

መፃጕዕ

የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡ ጌታ ሕሙማን መፈወሱን ሙት ማስነሳቱን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ማቴ. 8፥1-34 ፤ማር. 7፥24-37፤ ዮሐ. 5፥1-18 በመፃጕዕ የተሰየመው እርሱ ለእኛ ትምህርት ተግሳጽ እንዲሆነን አንጂ በዚህ ሳምንት የሚታሰበው በአጠቃላይ ሕሙማን መፈወሱ ሙት ማስነሳቱ ነው፡፡

በቤተክርስቲያን በሽተኞች በሦስት ስያሜ ይጠራሉ፡፡ የዕለት ሕመም ወይም ከአንድ ዓመት በላይ ሕመሙ የጸናበት መፃጕዕ ይባላል፡፡ ስለዚህ መፃጉዕ የተባለው ስለሕመሙ ጽናት እንጂ ስሙ አይደለም፡ Read more: መፃጕዕ

የንስሓ መዝሙራት

እንደበደሌማ

እንደበደሌማ ከሆነ ቅጣቴ

አያልቅም ተነግሮ ብዙ ነው ጥፋቴ

እንጃልኝ ፈራሁኝ አዬ ሰውነቴ/2/

      እመለሳለሁ እያልኩ ጠዋት ማታ

      ዘመኔን ጨረስኩ ሳስብ ሳመነታ

      ምን እመልስ ይሆን የተጠራሁ ለታ/2/

በላዬ ሲያንዣብብ ሞት እጁን ዘርግቶ

ስጋዬን ሲውጠው መቃብር ተከፍቶ/

የነፍሴ ማረፊያ ወዴት ይሆን ከቶ/2/

      ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን

      አቤቱ ጌታ ሆይ እኔን ባሪያህን

      ይቅር በለኝና ልየው ፊትህን/2

Read more: የንስሓ መዝሙራት

ምኵራብ

 የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ምራብ ይባላል፡፡ ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት' የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢየሩሳሌም አይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሠሩ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ግን ብዙ ምኩራቦች ነበሩ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡

Read more: ምኵራብ

ምኵራብ

ምኵራብ ማለት ሰቀላ መሰል አዳራሽ ማለት ነው፡፡ አይሁድ ስግደትና መሥዋዕት በኢየሩሳሌም ባለው መቅደስ ብቻ ነው ብለው ቢያምኑም /ዮሐ. 4፥20/ በተበተኑበት ቦታ ምኵራብ ሠርተው ትምህርተ ኦሪትን እየተማሩ ሃይማኖታቸውን ያፀኑ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም በሮማውያን ቅኝ ግዛት ሥር ወደቀችና ጭቆናው ከጊዜ ወደ ጊዜ በተራው ሕዝብ ላይ እየበረታ ሄደ፡፡ በመሆኑም ይህ ጭቆና የኑሮውን ውድነት ከዕለት ወደ ዕለት ያባብሰው ጀመር፤ በዚህ ጊዜ ሁሉም እያንዳንዱ ለራሱ በሚመቸው መልኩ ገንዘብ የሚያገኝበትን መንገድ በመምረጡ ሕዝቡ የማይወጣው ከፍተኛ ጫና ወደቀበት፤ ግማሹ የቄሳርን የሥራ አመራር በመጠጋት በገበያ ይቀርጣል፣ ሌላው የሃይማኖትን ነጻነት ሽፋን በማድረግ ፖለቲከኞችን አሳምኖና ከቀረጥ ነጻ ትሆናላችሁ በማለት ሕዝቡን አባብሎ ገበያውን ወደ ቤተመቅደሱ አንደኛ ግቢ ውስጥና በየምኵራቦቹ ውስጥ እንዲሆን አስወስኖ በቤተመቅደስ ዙሪያ በተለያየ ምክንያት ዘረፋውን ያጧጡፋል፡፡ እንዲህ መሆኑም መንፈሳዊያን ፖለቲከኞችና የጥገኝነት ፖለቲካ አራማጆችን ችግሩ አንድም ቀን ነክቷቸው አያውቅም፡፡ ይህ በመሆኑም የደሀው ኅብረተሰብ ንብረት በካህናት እጅ በተለያየ ስልት ሙልጭ ብሎ ገባ እንጂ ሕዝቡ አሁንም ቢሆን ያወቀው፣ የተረዳው ነገር አልነበረም፡፡

Read more: ምኵራብ

Page 3 of 17

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine