ግዕዝ

ልሳነ ግእዝ

ሙባእ/መግቢያ/

የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና አገልግሎት በአንድ ቋንቋ የሚወሰን አይደለም፡፡ እንደ ግእዝ ቋንቋ አይነቶቹ ቋንቋዎች ግን ከሌሎች ልሳናት በይበልጥ ለረጅም ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግለዋል፡፡

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል፡፡ ፍጥረታት በሐሌዎ'በነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ(ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ፡፡  እነዚህ ሊቃውንት ቅዱስ ገብርኤል ንቁም በበህላዌነ ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው—አዳምም ለ7ዓመታት በገነት ሲኖር በፀሎት ሲተጋ የነበረው በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል፡፡

ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ እግዚአብሔር በቋንቋ የሚወሰን አይደለም' በመጀመሪያ አዳምን ሲፈጥረውም የሁሉንም ቋንቋ አዋቂ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን አዳም የሞት ሞትን (ሞተ ልቦናን) ሲሞት ቀደም ሲል የነገረው እውቀትም ከውስጡ በመሞቱ እና ቋንቋም የእውቀቱ አንድ አካል በመሆኑ ጠፋበት፡፡ ከዚያም በሰናዖር ሰዎች የአመጽ ጊዜ ቋንቋዎቹ ተገለፁ፡፡ ስለዚህ የግእዝ ቋንቋ ለብቻው የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ማለት አይቻልም ይላሉ፡፡

ከዚህ የተለዩት ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ የመጀመሪያው የአለም ቋንቋ ዕብራይስጥ መሆኑን አስረግጠው ይናገራሉ፡፡

 ከተጠቀሱት የተለየ አመለካከት ያላቸው አይጠፉም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የግእዝ ቋንቋ ጥንታዊና ከቀዳማዊያን ልሳናት አንዱ መሆኑን ሁሉም ይስማማል፡፡

 

ጥናታዊ ታሪኩ

የግእዝ ቋንቋ ጥናታዊ ወይም ሳይንሳዊ ታሪክን ስንመለከት ቋንቋው ከኢትዮጵያ ሴማውያን ቋንቋዎች ማለትም ከሳባ' ትግረ' ትግርኛ' አማርኛ' ጉራጊኛ' አርጎብኛና ከመሳሰሉት ጋር ተደምሮ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ በሴማዊያን ቋንቋዎች ምድብ አረቢክ' አካዲያንና ከነዐናይትን (ዕብራይስጥ' ፍንቄ) የመሳሰሉት ጥንታዊ ቋንቋዎች ይገኛሉ፡፡

      ፊደላተ ግእዝ

አዳም ሞተ ልቦናን ከሞተ በኋላ የጠፋበት የቋንቋና ፊደላት እውቀት (እንደ አንዳንድ ሊቃውንት አገላለጽ) በፀፍፀፈ ሰማይ ለሴት ተገለጸለት፤ ሴትም በአባቱ ምክንያት ሞተ ልቦናን ሞቶ ስለነበር ከጊዜ በኋላ ጠፋበት፡፡

እግዚአብሔር አምላክም በድጋሚ በፀፍፀፈ ሰማይ ለሄኖክ ፊደላትን ገለጸለት፡፡ ሄኖክም እንደ አያቶቹ እንዳይጠፋበት በሸክላ የፊደላቱን ቅርጽ ቀረጸ፡፡ እነዚህ ፊደላት የግእዝ ፊደላት ናቸው ብለው የሚከራከሩ እንዳሉ ሁሉ ከሴማውያን ቋንቋዎች የአንዱ (በተለይም የዕብራይስጥ) ናቸው የሚሉ አሉ፡፡

በቅርጽ ስናያቸው የሴም ቋንቋዎች ፊደላት ተመሳሳይ ቅርጽ አላቸው፡፡ የግእዝ ፊደላት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' ' '

-    ጰ እና ፐ ድምፃቸው የግሪክ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ሞክሼ ፊደላት እና ልዩነታቸው

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት ሀ' ' — ' — ' — ' ፀ ናቸው፡፡ እነዚህ ፊደላት የድምፅም' የቅርጽም' የትርጉምም ልዩነት አላቸው፡፡

የድምፅ ልዩነት

' '

-  ላልቶ ይነበባል

- ጠብቆ ይነበባል

- በጉሮሮ ይነበባል

'

- እንደ ሸ ይነበብ ነበር

- በጥርስ ይነበብ ነበሰር

ለምሳሌ፡- ንጉሥ ብለን ነጋሽ እንላለን፡፡ ይህም ሠ እንደ ሸ ይነበብ እንደ ነበር ያስረዳል፡፡

     '

     - ላልቶ ይነበባል

     - ጠብቆ ይነበባል

     '

     - የራሱን ድምፅ ይይዛል

     - እንደ ጠ ይነበብ ነበር

ለምሳሌ፡- ፀሐይ የሚለውን ቃል ጠሐይ ብለው የሚጽፉና የሚያነቡ አሉ፡፡

     የትርጉም ልዩነት

1. ንሰ - ትርጉም የለሽ

   ንሰ - ፀፀት' ሐዘን

   ንስ - ክርፋት' ግማት

2. ድነት - መዳን' መፈወስ

   ነት - ማጣት' መቸገር

3. በ -  ኮሶ

   በ -  ወደ

4. ሰለ - ለመነ

  ለ - ስዕል ሳለ

  ለ - አሳለ' ኡሁ አለ

የአማርኛ ፊደላት

     ከጊዜ በኋላ ድምፅና ቅርጽን ከግእዝ ፊደላት በመውሰድ የተፈጠሩ ናቸው፡፡

የአማርኛ ፊደላት

ድምፃቸውን የወሰዱት

ቅርጻቸውን የወሰዱት



 

የግእዝ አናባቢ ፊደላት

     በአሁኑ ጊዜ በአናባቢነት እያገለገሉ ያሉ ፊደላት 7 ሲሆኑ ከ አ እስከ ኦ ያሉት ናቸው፡፡ የጥንት አናባቢዎች ግን የሚከተሉት ናቸው፡፡

' --- ራብዕንና ሳድስ ድምፅን

      ለምሳሌ፡- በ + አ = ባ'

              በ + ሀ = ባ'

--- ካዕብንና ሳብዕን

     ለምሳሌ፡- በ + ወ = ቡ'

--- ሐምስንና ሣልስን

     ለምሳሌ ፡- በ + የ  = ቤ'

     እነዚህ አናባቢዎች አባ ፍሬምናጦስ - እና 0 ቅጥያዎችን እስኪፈጥሩ ድረስ ማለትም እስከ 334 ዓ.ም ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ከ334 -350 ዓ.ም ጥናት ተደርጎ ለውጥ ተካሂዷል፡፡

ስለዚህ የግእዝ ፊደላት እንደሚከተለው ማየት እንችላለን፡፡

ቀዳማይ ግእዝ

 ደሐራይ ግእዝ

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

 

 

 

 

 

 

                                            

የቀዳማይ ግእዝ ቃላት                          የጸሐራይ ግእዝ ቃላት

ሀለወ  =  ኖረ                                 ሀልሀ  =  ወደረ

ለመደ  =  ለመደ                               ለምዐ  =  ለማ

ሐለመ   =  አለመ                              ለቅሐ  =  አበደረ

ሐለወ  = ጠበቀ                                ልህየ  = ወዛ

መለከ  =  ከሳ                                 ልሕመ  = ላመ

መሰለ  =  መሰለ                               ሎሐ  = መጻፍያ መሳሪያ

መነነ  =  ናቀ' ተወ                            ሎሰ  =  ለወሰ

መከረ  =  መከረ                               ምዕዘ  =  ጣፈጠ

ሠለሰ  =  ሦስት አደረገ                          ሞአ   =  አሸነፈ

ሰበከ  =  አስተማረ                              ሞቅሐ  =  አሰረ

ሰከበ  =  ጋደም አለ                             ሞተ  =  ሞተ

                                             ሠርዐ  = ሠራ

                                             ሣርሀ  =  አበራ

                                             ሦአ  = ሰዋ 

ሥርዓተ ንባብ

የግእዝ ሥርዓተ ንባብ ዐራት ዓይነት ነው፡፡

1.ተነሽ ንባብ

2.ወዳቂ ንባብ

3.ተጣይ ንባብ

4.ሰያፍ ንባብ

1. ተነሽ ንባብ

- ተነሽ ንባብ በአምስቱ ንባብ (ቀጥሎ በተዘረዘሩት) እየደረሰ መድረሻ ፊደልን ይዞ ይነሳል፡፡

ግዕዝ       ካዕብ       ሣልስ       ራብዕ       ሳብዕ

ገብረ         ገብሩ        ግበሪ        ገብራ        ባርኮ

ዘንተ        ሐሙ        ሑሪ         ሐራ         ሕድጎ

ሰማየ        ሑሩ         ጸውዒ       ጸውዓ        ዕቀቦ

ወምድረ      ስብኩ        ምተኪ       ሐተታ

            ጸውኡ       ሰኣሊ        አመራ       ኰንኖ

                                                ኩኖ

ምሳሌ፡- ገብረ ሰማየ ወምድረ

        ሐሙ ርሕቡ ወተመንደቡ

        ሑሪ  ጸውዒ ምተኪ

        ሖራ ወስበካ ወዜናዋ

        ባርኮ ወቀድሶ

2. ወዳቂ ንባብ

- ወዳቂ ንባብ በሰባቱም ፊደላት እየደረሰ መድረሻውን ፊደል በመያዝ ወድቆ ይነበባል፡፡

 ግዕዝ     ካዕብ     ሣልስ      ራብዕ     ሐምስ     ሳድስ    ሳብዕ

አሐደ       ዝንቱ       ዛቲ        ሐተታ       ሥላሴ               ባርኮ

ክልኤተ      አሐዱ      አሐቲ                  ብእሴ        እምዝ      ሰአሎ

ሠለስተ      ክልኤቱ     ክልኤቲ     ወለታ       ወራሴ      ከመዝ      ጸውዖ

            እስፍንቱ    መዋቲ      ደብተራ      ድምሳሴ               አመሮ

                      ሰአሊ        ሐረያ       ኩነኔ                  ፈነዋ

                       ሐዋሪ       ምኅርካ       ምናኔ

                      ነጋዲ     

ምሳሌ

-    አሐተ ወለተ ሐረየ ብእሲ

-    ዝንቱ አቡሁ ጸውዖ ለወልዱ

-    ብእሲ ተከለ ደብተራ

-    ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ

-    ከልሐ እግዚእነ ብሂሎ ኤሎሄ

-    ዝ ውእቱ ወልድነ

3. ተጣይ ንባብ

- በሳድስ ፊደልና ድምፅ እየደረሰ ቅድመ መድረሻውን ይዞ ወዳቂ ሆኖ ይነበባል፡፡

      - እግዚአብ

      - አ

      - ቅር

      - ብር

      - ድቅ

      - ክር

      - ሀይማ

ምሳሌ

-    ሀይማኖት ወክብር ያከብሩ ሰብአ

-    ጽድቅ ወሰላም ተራከባ

-    ምክር ሠናይት ለኩሉ ዘይገብራ

4. ሰያፍ ንባብ

- ሰያፍ ንባብ በሳድስ ፊደል እየደረሰ ቅድመ መድረሻውን ፊደል ይዞ ይነሳል፡፡

      - ይነ

      - ይመ

      - ይ

      - ይጽ

      - ይስ

      - ይሕ

      - ይገ

ምሳሌ
      - ይገብር ጽድቅ አብርሃም

-   ይነብብ ሰሎሞን ጥበበ

-   ይስቅ ወያዕቆብ ወረሱ ርስተ

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine