ሐሙስ /አምስተኛው ቀን/

በዚህ ዕለት የተደረጉ ዐበይት ድርጊቶች፡-

ð  የትሕትና መምህር የሆነው ጌታችን ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ በመቅረቡ ትሕትናን ሊያስተምር የደቀመዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ ‹‹እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል›› በማለት የትሕትናን ትምህርት አስተምሯል፡፡ /ዮሐ. 131-20/

ð  ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻዋን እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲበላ ምሥጢረ ቁርባንን ከዚህች ዕለት መስርቷል፡፡ ‹‹ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራውን አንስቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና እባካችሁ ብሎ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡  ጽዋውንም›› አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፡፡ ሁለታችሁም ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡ በማለት ስለኛ በፈሰሰ ደሙ በኃጢአታችን ይቅርታ አድርጎ እንደታረቀን እንዲህ በማለትም አረጋግጧል፡፡‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፡፡›› /ዮሐ. 1515/

ማቴ. 2626-29         ሉቃ. 227-23

Read more: ሐሙስ /አምስተኛው ቀን/

አርብ /ስድስተኛው ቀን/

ð  ይህች ቀን አዳም ኋላም ሔዋን የተፈጠሩባት፣ ከገነት ተሰደው የወጡባት ዕለት ናት፡፡ ጌታም ቀድሞ የሥነ ፍጥረት ሥራውን እንደፈጸመበት አሁንም የድኅነት ሥራውን ፈጸመባት፡፡ በዚህች ዕለት በአምላካችን ላይ የተፈጸመው መከራ እጅግ አሰቃቂ ነበረ በፍጡርም ሊገለጹ የማይችሉ ናቸው፡፡

ð  የክብርን ባለቤት ጭፍሮች ይዘው በሊቀ ካህናት ቢት አቀረቡት፡፡ ሊቀ ካህናቱም ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆንክ ንገረን›› አለው ጌታም ‹‹አንተ አልህ . . . የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ›› ቢለው ሊቀ ካህናቱ ተሳደበ በማለት ፊቱን ነጨ ልብሱን ቀደደ፡፡ በኦሪት ሕግ እንዲህ ያደረገ ይሻር ትል ነበር፡፡ ጌታ እንደተሾመበት እርሱ እንደተሻረበት ለማጠየቅ፡፡

ð  ጌታ እንደተናገረው ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ ካደው በዚህ ጊዜ ዶሮ ጮኸ ጌታ ያለውን አስታውሶም እንዲህ ሲል አለቀሰ ‹‹ከሁሉ ይልቅ እኔ እወደው ከሁሉ አስቀድሞ እኔ እክደው›› ብሎ ከልቡ ስላለቀሰ ንስሐውን ተቀብሎታል፡፡

ማቴ. 2669-75      ማር. 1466-72

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት በየሰዓታቱ የተፈጸመበት ድርጊቶች፡-

Read more: አርብ /ስድስተኛው ቀን/

ረቡዕ /አራተኛው ቀን/

=>  በዚህ ዕለት የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰብስበው እንዴት በተንኮል እንደሚይዙትና እንደሚያስገድሉት ምክር የቆረጡበት ዕለት ነው፡፡ ነገር ግን የፋሲካ በዓል ቀርቦ ስለነበር ሕዝቡም በትምህርቱ ተመስጦ በተአምራቱ ተማርኮ ስለነበር ሁከት እዳይፈጠር እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ሲጨነቁ ከጌታ ደቀመዛሙርት መሃል ይሁዳ ከምክራቸው በመቀላቀል ጭንቃቸውን አቀለለላቸው፡፡

    ማቴ. 2635       ሉቃ. 221-6         ማር. 141እና2

Read more: ረቡዕ /አራተኛው ቀን/

ማክሰኞ /ሦስተኛው ቀን/

በዚህ ዕለት የተደረጉት ዐበይት ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡

ð  ደቀመዛሙርቱ የበለሷን መድረቅ አይተው ሲገረሙ ጌታችን ሃይማኖት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩ ይህን ተራራ ከዚህ ተነስተህ ከባሕር ግባ ብትሉት ይቻላችኋል ብሎ ስለ እምነት አስተምሯቸዋል፡፡

ማቴ. 2120-21 ፣ ማር. 1120-26  ዮሐ. 141

ð  በቤተመቅደስ ሲያስተምር ሳለ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች መጥተው ከምድራውያን ካህናት ወገን ያይደለህ ከምድራውያን ነገሥታት ወገን ያይደለህ ይህን የምታደርግ በምን ሥልጣንህ ነው ብለው ጠየቁት እርሱም ከእናንተ አኔ ቅድሚያ አለኝ ሲል ጠየቃቸው ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነው?›› (ዮሐንስ ማስተማሩ በማን ፈቃድ ነው?) እነሱም ከሰማይ እንዳይሉ አያምኑበት ከምድር እንዳይሉ ሕዝቡን ፈሩትና አናውቅም አሉት እርሱም እኔም አልነግራችሁም ብሎ ረታቸው፡፡

ማቴ. 2123-27፣ ማር. 112733 ሉቃ. 202140

Read more: ማክሰኞ /ሦስተኛው ቀን/

ሰኞ /ሁለተኛው ቀን/

 በዚህ ዕለት የተደረጉት ዐበይት ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡

ð  መርገመ በለስ /ያላፈራችውን በለስ ረገመ/፡- ጌታችን በቢታንያ አድሮ ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበና ፍሬ ባገኝባት ብሎ ከመንገድ ዳር የነበረችውን በለስ ተመለከተ ፍሬ ስላጣባትም ‹‹ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ›› ብሎ ረገማት፡፡ በማርቆስ ወንጌል የበለስ ጊዜ አለመሆኑን ይገልጻል፡፡ ታዲያ ለምን እያወቀ እንዲህ አደረገ ቢባል አውቃለሁ ብሎ ሥራውን ከመሥራት እንደማይተው ሊያስተምረን ፈቅዶ ነው፡፡ በምሥጢሩ ከበለስ ፍሬ መሻቱ ከሰው ፍቅር ተርቦ በለስ እስራኤልን በኢየሩሳሌም አገኘ ሃይማኖት ምግባር አገኝባቸው ብሎ ቢያይ አጣባቸው፡፡ በዚህም ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡

ð  አንጽሖተ ቤተመቅደስ፡- በሆሣዕና ዕለት ቤተመቅደሱን ከነጋዴዎች እንዳጸዳ የተረፈውን ጥቃቅኑን ደግሞ በዚህ ዕለት አጽድቶአልና አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡፡

Page 2 of 5

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine