ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር

ክርስቲያናዊ ሥነ - ምግባር

ክርስቲያናዊ ሥነ - ምግባር

 

‹‹ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ›› ማቴ. 5፡16

 

የመንፈሳዊ ትምህርት ማሰሪያው የምስጢራት መወሰኛው/የመጀመሪያው/ በጥሩ ሥነ ምግባር እራስንና ሌሎችን ቀርጾ መገኘት መሆኑን እምነታችንንና ምግባራችንን በጥሩ ሥራ መግለጽ አለብን ያዕ.2፡14

አንድ ሰው ጥሩ ወይም መጥፎ ሥነ ምግባር አለው ስንል ሥነ ምግባሩን በሁለት ነገሮች ማየት አለብን፡፡

1.  ውጫዊ ሥነ ምግባር

2.  ውስጣዊ ሥነ ምግባር

ነፍስና ስጋ እንደማይለያይ ሁሉ ሃይማኖትና ምግባር አይለያዩም፡፡ ያዕ. 2፡14

 

የሥነ ምግባር ሕግጋት

 

ሕግ ማለት ለማድረግ የሚያዝ ከማድረግ የሚከለክል ውሳኔና ሥርዓት ነው፡፡ ማንኛውም ክርስቲያን በእግዚአብሔር ዘንድ ቅድስናን አግኝቶ ይኖር ዘንድ የሥነ ምግባር ሕጎች የትኞቹ እንደሆኑ ግብራቸውና ስልታቸውን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡

 

 

 

                        የሥነ ምግባር ሕጎች

 
 
 

 


      መንፈሳዊ / አምላካዊ/ ሕግ             ሥጋዊ /አለማዊ/ ሕግ

                                     

 

ኢ - ጽሑፋዊ ሕግ        ጽሑፋዊ ሕግ    የቤተክህነት ሕግ   የቤተመንግስት ሕግ

       
   
 

 


ሕገ ልቡና  ሕገ ሕሊና   ብሉይ ኪዳን       ሐዲስ ኪዳን

                    (አስርቱ ትዕዛዛት)  (ስድስቱ ቃላተ ወንጌል)

 

 

- ክርስቲያን ሁሉ መንፈሳዊነትም ሥጋዊነትም ያለው ምድራዊ ፍጡር እንደመሆኑ እርሱንም የሚመለከተው ሕግ ሁለት ጠባይ ወይም በሁለት ክፍል ያለው ሕግ ይሆናል፡፡ ይኸውም

            - መንፈሳዊ/አምላካዊ/ ሕግ

            - ሥጋዊ ሕግ በመባል የሚታወቅ ነው፡፡

 

መንፈሳዊ /አምላካዊ/ ሕግ ለሰው ሁሉ ከልዑል እግዚአብሔር በተፈጥሮና በጽሑፍ የተሰጠው ሲሆን ዘለዓለማዊ በመሆኑ እና ከእግዚአብሔር በመገኘቱ መንፈሳዊ ሕግ ተብሏል፡፡

 

ኢ - ጽሑፋዊ ሕግ በሁለት ይከፈላል፡፡

-    ሕገ ልቡና

-    ሕገ ሕሊና

 

- ሕገ ልቡና፡- ይህ ሕግ በሰው ልቦና አንድ ጊዜ ከተጻፈ በኋላ ሳያረጅ ሳያፈጅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ያለ የኖረ የተፈጥሮ ሕግ ነበር፡፡ ሮሜ. 1፡14 ሕገ ልቡና የተባለው ሰው በተባለው ሁሉ በልቦናው ተጽፎ የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው ማንም ሳያስተምረው ክፉውንና ደጉን ለይቶ ሳይነግሩት እንዲያውቅ የሚያደርገው ስለሆነ ነው፡፡

 

 ሕገ ልቦና ሕገ ተፈጥሮአዊ ወይም ሕገ ጠባያዊ እየተባለ የሚጠራ ሲሆን ሰው የሚመሰገነው በተፈጥሮ የተሰጠውን ይህንን ሕግ በንጽሕና በመያዙና በማዳበሩ ነው፡፡

የሰው ልጅ ክፉውን ለይቶ ያውቅበት ዘንድ የተሰጠው ሕግ ነው፡፡

 

- ሕገ ሕሊና፡- ሕገ ሕሊና ወይም ሕሊናዊ ሕግ የእግዚአብሔር ድምጽ ለነፍስ የሚተላለፍበት በማናቸውም ክርስቲያን ሁሉ አድሮ የሚሠራ ሥነ ምግባራዊ ሕግን እንድንፈጽም የሚያነቃ አርፈን እንቀመጣለን ብንል እረፍት የሚነሳ ነው፡፡ አንድ ሰው ነፍስ አጥፍቶ እንደሆነ የሚከስ አልምቶም ከሆነ እንዲደሰት የሚያደርግ የሕሊና ዳኛ ነው፡፡

 

- ይኽ ሕግ አንድ ግብር እንዲፈጸም ወይም እንዳይፈጸም ማስጠንቀቂያና ምርጫን የሚያደርግ ሲሆን ከተደረግ በኋላ መጥፎ እንደሆነ መጸጸትን ሐዘንን ያመጣል መልካም ከሆነ ደግሞ ደስታን መጽናናትን ይሰጠናል፡፡ ማንኛውም የክርስትና ተከታይ የሆነ በስሙ የተጠራ ግን ሁሉ ፍለጋውን የሚከተሉ ሁሉ የራሱን ሕሊና ምርጫ ማክበር የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ግዴታው ይሆናል፡፡ እየተጠራጠረ እያመነታም የሚሠራ ሰው ሁሉ ከሕሊናው ግምት ውጭ ይሠራል ማለት ነው፡፡ ይህም እርሱን መበደል ነው፡፡ ሮሜ. 14፡23 ስለዚህ ሳይሠራ ያመልጣል ከሁሉ አስቀድሞ በምንሠራው ሥራ እንደ ሃይማኖታችን ጽናት መጠራጠር አይገባንም፡፡ ይህንን ሁሉ ለማስወገድ ከሁሉ በፊት

 

1.  ጸሎት መጸለይ ማለት የሚሠሩትን ሁሉ ‹‹ ወይኩን ፈቃድከ ›› ብሎ መጠየቅ

2.  ዓለማዊ ማንኛውም ከእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ የእሱን አምልኮትና ፍቅር መግለጫ መሆን ይኖርበታል፡፡ አምላክ ሰውን አፍቅሮ አንድያ ልጁን ለእኛ አሳልፎ ቤዛ እንደሰጠ ሁሉ ዮሐ. 3፡16

3.  ስለ እግዚአብሔር ክብር ተብሎ የሚሰራ መሆን ይኖርበታል 1ቆሮ 10፡31

4.  ስለ ባልንጀራው ፍቅር መሆን ይገባዋል፡፡

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine