ትምህርተ ሃይማኖት

አዕማደ ምሥጢራት - ምሥጢረ ሥጋዌ

ምሥጢረ ሥጋዌ

 

ሥጋዌ ‹‹ተሰገወ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ሥጋን መንሳት /ሰው መሆን/ ማለት ነው፡ ምሥጢረ ሥጋዌ ከሦስቱ አካላት አንዱ እግኢአብሔር ወልድ ሰው የመሆኑ ምሥጢር ነው፡፡ ሰው ሆነ ማለትም የሰውን ባሕርያት ነፍስና ሥጋን በረቂቅ ባሕርይው ተዋሐደ ማለት ነው፡፡

 

አምላክ ለምን ሰው ሆነ?

 

Ø  እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ለማዳን ቃል ኪዳን ስለገባላቸው ቃል ኪዳኑን ለመጠበቅ አምላክ ሰው ሆነ፡፡ ዘፍ 2፡17 ፣ 1ኛ ተሰ 5፡9 ፣ ገላ 4፡4፡፡ በስመጨረሻ ሁሉን አሟልቶ በአርአያውና በምሳሌው ለፈጠረው ሰው ፍጽም የሆነ ፍቅሩን በገሀድ ለማሳየት አምላክ ሰው ሆነ፡፡ ዮሐ 3፡6

Ø  ምድር ለመልካም ተፈጥራ ሳለ ስለሰው ኃጢአት በመረገሟ በቅዱሳን እግሮቹ ተራምዶ ሊቀድሳት በደሙ ፈሳሽነት ሊያነጻት አምላክ ሰው ሆነ፡፡ ት.ኢሳ 45፡18 ፣ ዘፍ 3፡17 ፡፡

Ø  ሰው በምድር ካለ የሚቀናቀነው የለም ስለሆነም በልብ መታበይ አምላክ ነኝ እንዳይል ሁሉን የፈጠረ አምላክ መኖሩን ሊያስረዳ፡፡

Ø  ዲያብሎስ አዳም ሔዋንን ከይሲ / እባብ/ ሰውነት አድሮ እንዳሳታቸቸው እርሱም በሰው አካል አድሮ ሊያድናቸው፡፡

 

አምላክ ሰው ባይሆን ማዳን አይችልም ነበረን?

     

      ፍርድ እንዲገባ

 

Ø  አምላካችን ሁሉን ማድረግ የሚችል የማይሳነው ነው፡፡ ዘፍ 18፡14 ፣ ኢዮ 39፡4

ሉቃ 1፡37 ነገር ግን ሥርዓት አልባ አይደለም ፤ ሁሉን በሥርዓት ያደርጋል፡፡ 1ኛ ቆሮ 14፡33

Ø  የፍርድ ቃልን የሚለውጥ አይደለምና በመሐሪነቱ አንጻር ግን ይቅር ባይ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ትክክለኛና የማይሻር ዳኝነቱን ሊያሳይ ሰው ሆነ፡፡

ዕብ 6፡17፣ ማቴ 7፡7 ያዕ 2፡5

 

   ፍጹም ፍቅሩን ሊያስረዳን

 

Ø  የበደለ ኃጢአትን የሠራ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ጥተኛ ፍርድ መሠረት የኃጢአትን ዋጋ  መክፈል ያለበት ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ከሰው ልጆች መካከል ባሕርይው ያላደፈበት ወንጀለኛ ያልሆ ስለጠፋ ሁሉም ራሱ መዳ የሚያስፈልገው ስለሆነ ፍጡር ሰው ፍጡር ሰዎችን ማዳን አልቻለም፡፡ ስለዚህ የማይለወጥ አምላክ ለተሠራው በደል የሚከፍል ሞትን ይፈጽም ዘንድ ሰው ሆነ፡፡ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ ት.ኢሳ 59፡16 ፣ ሮሜ 3፡23

ሮሜ 5፡6

 

 

የአምላክ ሰው መሆን /መወለድ/

 

ከቅድስት ድንግል ማርያም ሲወለድ ማኅተመ ድግልናዋ ሳይለወጥ ነው፡፡ በዚህ ድግል ስትባል ትኖራለች፡፡ ምሳሌው አምላክ ሰውም ሲባል መኖሩ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከድንግል ማርያም ያለ ዘር ሩካቤ መወለዱ ለአካላዊ መሲህ መለያ ምልክቱ ነው፡፡ ሕጻናትን በማሕጸን የሚፈጥር የእግዚአብሔር ልጅ በሥጋና በነፍስ በሕጻናት ጽንስ መጠን በድንግል ማርያም ማሕፀን ተጸነሰ፡፡

 

ጌታ ከጽንስ ጀምሮ የሰውነት ጠባዩ አልተለወጠም፡፡ 9ወር ከ5 ቀን ሲሆ ተወለደ፡፡ በልደቱም እናቱ ጭንቅ ምት አላገኛትም፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን በድንግልና መውለድ ከሌሎች ሴቶች ፀንሶ መውለድ ይለያል፡፡ 

  

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine