ትምህርተ ሃይማኖት

አዕማደ ምሥጢራት

 

አዕማድ ቋሚ ፣ ተሸካሚ ፣ ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእምነት መሠረት የሆኑትን ትምህርቶች አዕማደ ምሥጢራት ትላቸዋለች፡፡ አዕማድ የተባሉት ልቦናን ከኑፋቄ ፣ ከጥርጥር የሚያድኑ ስለሆነ ነው፡፡ ምሰሶ የሌለው ቤት እንደሚወድቅ ሁሉ አዕማደ ምሥጢራትም ያላመነ ፣ ያላወቀ ሰው ቢኖር ይወድቃል፡፡

 

አዕማደ ምሥጢራት አምስት ናቸው፡፡ እነዚህም

 

  1. ምሥጢረ ሥላሴ
  2. ምሥጢረ ሥጋዌ
  3. ምሥጢረ ጥምቀት
  4. ምሥጢረ ቁርባን
  5. ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው፡፡

 

ምሥጢር መባላቸው ስለምንድን ነው

 ምሥጢር

አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣ ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት

·         በሥጋው ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ

·         ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ

 

 

ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-

 

የፈጣሪ ምሥጢር፡- ሊገለጥ የማይችል ነው፡፡ ከ እስከ የሌለው ምሥጢርም ይባላል፡፡

 

የፍጡራን ምሥጢር፡- በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅ/ ነው፡፡ የሰውና የመላእክት ምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine