ትምህርተ ሃይማኖት

ሥነ-ፍጥረት

ልዑል እግዚአብሔር በእውቀቱ ሰማይን ምድርን እንዲሁም በእነርሱ የሚገኙትን ሁሉ ከምንም ወይም ካለመኖር ወደ መኖር የፈጠረው ብቁ ንቁ የሆነ ሥነ-ፍጥረት የፈጠረበትን ሁኔታ ሥርዓት የምንማርበት ትምህርት ሥነ-ፍጥረት ይባላል፡፡ ሥነ-ፍጥረት ማለት የፍጥረት መበጀት ማለት ነው፡፡ ይህ የሚታየው ዓለምና በውስጡ ያለው ሁሉ ከዚህ ከሚታየው ዓለም ውጭም ያለው የማይታይ ዓምና በውስጡ ያሉት ረቂቃን ፍጥረታት ሁሉ በእግዚአብሔር ተፈጥረዋል፡፡

 

ዘፍ 1÷1 ፣ መዝ 101÷25 ፣ ኢሳ 66÷1-2 ፣ ዕብ 11÷3፡፡ እግዚአብሔር ግዙፉንና ረቂቁን ዓለም የፈጠረው ከምንም ተነስቶ የሚያገናኛቸውና የሚያዋሕደው ነገር ሳይኖረው ነው፡፡ መዝ 32÷9 ፣ ጥበብ 11÷18 ፣ የሐዋ.ስራ 17÷24 ፣ መዝ 148÷5

 

·                     እግዚአብሔር ፍጥረታትን የፈጠረው ሰውንና መላእክትን ስሙን ለመቀደስ፣ ክብሩን ለመውረስ ሲሆ የተቀሩትን ፍጥረታት ግን ለአንክሮ፣ ለከተዘክሮ፣ ለምግበ ሥጋ፣ ለምግበ ነፍስ ነው፡፡ መዝ148÷1-13፣ ራዕይ 4÷11፣ የሐዋ.ሥራ 14÷7፣ ሮሜ 1÷20፡፡

 

·                     እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ያከናወነው በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ዘጽ 20÷9-11፡፡ በእነዚህ ቀናት የተፈጠሩት ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ቢቆጠሩ ፍጡር ተናግሮ አይፈጽመውም ነበር፡፡ ነገር ግን በባሕሪያቸው በአኗኗራቸው በ22 ይመደባሉ፡፡ ኩፋሌ 3÷9 የተፈጠሩትም በሦስት መንገድ ነው፡፡

 

1.       በአርምሞ (በዝምታ) አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ፣ ጨለማ ፣ መላእክት ፣ ሰማያት

2.       በነቢብ (በመናገር) ብርሃን ፣ ጠፈር ፣ እንስሳት ፣ ዕፅዋት

3.       በገቢር (በመሥራት) ሰውን ብቻ፡፡

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine