ትምህርተ ሃይማኖት

የትምህርተ ሃይማኖት ኮርስ የመማሪያ መፅሐፍ

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከሚሰጣቸው ተከታታይ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ ትምህርተ ሃይማኖት ነው፡፡ የዚህን ኮርስ የመማሪያ መፅሐፍ ለማግኘት ይህን ይጫኑ

አዕማደ ምሥጢራት

 

አዕማድ ቋሚ ፣ ተሸካሚ ፣ ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእምነት መሠረት የሆኑትን ትምህርቶች አዕማደ ምሥጢራት ትላቸዋለች፡፡ አዕማድ የተባሉት ልቦናን ከኑፋቄ ፣ ከጥርጥር የሚያድኑ ስለሆነ ነው፡፡ ምሰሶ የሌለው ቤት እንደሚወድቅ ሁሉ አዕማደ ምሥጢራትም ያላመነ ፣ ያላወቀ ሰው ቢኖር ይወድቃል፡፡

 

አዕማደ ምሥጢራት አምስት ናቸው፡፡ እነዚህም

 

  1. ምሥጢረ ሥላሴ
  2. ምሥጢረ ሥጋዌ
  3. ምሥጢረ ጥምቀት
  4. ምሥጢረ ቁርባን
  5. ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው፡፡

 

ምሥጢር መባላቸው ስለምንድን ነው

Read more: አዕማደ ምሥጢራት

ሥነ-ፍጥረት

ልዑል እግዚአብሔር በእውቀቱ ሰማይን ምድርን እንዲሁም በእነርሱ የሚገኙትን ሁሉ ከምንም ወይም ካለመኖር ወደ መኖር የፈጠረው ብቁ ንቁ የሆነ ሥነ-ፍጥረት የፈጠረበትን ሁኔታ ሥርዓት የምንማርበት ትምህርት ሥነ-ፍጥረት ይባላል፡፡ ሥነ-ፍጥረት ማለት የፍጥረት መበጀት ማለት ነው፡፡ ይህ የሚታየው ዓለምና በውስጡ ያለው ሁሉ ከዚህ ከሚታየው ዓለም ውጭም ያለው የማይታይ ዓምና በውስጡ ያሉት ረቂቃን ፍጥረታት ሁሉ በእግዚአብሔር ተፈጥረዋል፡፡

Read more: ሥነ-ፍጥረት

ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት

ሃይማኖት የሚለው ቃል ሃይመነ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማመን ፣ መታመን ፣ አመኔታ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ቅድመ ዓለም ከሁሉም በፊት የነበረ ፍጥረታትን የፈጠረ ማዕከላዊ ዓለም ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ ድህረ ዓለም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ለእርሱ ግን አስገኝ አሳላፊ የሌለው መሆኑን በአንድነት በሦስትነት ያለ ሁሉን ቻይ አምላክ እንዳለ ማመን ማለት ነው፡፡ ሮሜ 10.9 ሃይማኖት ፈጣሪና ፍጡር የሚገናኙበት ረቂቅ መንገድ ነው፡፡ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማግኘት ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡ ዕብ 11.6

 

v    ሃይማኖት ለዓለም ፈጣሪ አለው ብሎ ማመን ነው፡፡

v    ሃይማኖት ለሚቀበሉት የድል ወይም የድኅነት መሣሪያ ነች

v    ሃይማኖት አንዲት ናት፡፡ ኤፌ 4.5 ኤር 6.16 በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው የእውነት ግንኙነት አንድ ነውና፡፡

 

በአጠቃላይ ሃይማኖት በዓይን የማይታይ በእጅ የማይዳሰስ በጆሮ ብቻ ሰምቶ ይህ እንዴት ሊደረግ ይችላል? ሳይሉ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ብለው በእምነት ሕሊና አምነው የሚቀበሉት ረቂቅ ምስጢር ነው፡፡ ሉቃ 1÷26-37 ፣ ዘፍ 18.14 ፣ ዕብ 11÷1-3 ፣ ሮሜ 4÷3

Read more: ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine