ግዕዝ

ልሳነ ግእዝ

ሙባእ/መግቢያ/

የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና አገልግሎት በአንድ ቋንቋ የሚወሰን አይደለም፡፡ እንደ ግእዝ ቋንቋ አይነቶቹ ቋንቋዎች ግን ከሌሎች ልሳናት በይበልጥ ለረጅም ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግለዋል፡፡

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል፡፡ ፍጥረታት በሐሌዎ'በነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ(ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ፡፡  እነዚህ ሊቃውንት ቅዱስ ገብርኤል ንቁም በበህላዌነ ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው—አዳምም ለ7ዓመታት በገነት ሲኖር በፀሎት ሲተጋ የነበረው በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል፡፡

ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ እግዚአብሔር በቋንቋ የሚወሰን አይደለም' በመጀመሪያ አዳምን ሲፈጥረውም የሁሉንም ቋንቋ አዋቂ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን አዳም የሞት ሞትን (ሞተ ልቦናን) ሲሞት ቀደም ሲል የነገረው እውቀትም ከውስጡ በመሞቱ እና ቋንቋም የእውቀቱ አንድ አካል በመሆኑ ጠፋበት፡፡ ከዚያም በሰናዖር ሰዎች የአመጽ ጊዜ ቋንቋዎቹ ተገለፁ፡፡ ስለዚህ የግእዝ ቋንቋ ለብቻው የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ማለት አይቻልም ይላሉ፡፡

ከዚህ የተለዩት ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ የመጀመሪያው የአለም ቋንቋ ዕብራይስጥ መሆኑን አስረግጠው ይናገራሉ፡፡

 ከተጠቀሱት የተለየ አመለካከት ያላቸው አይጠፉም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የግእዝ ቋንቋ ጥንታዊና ከቀዳማዊያን ልሳናት አንዱ መሆኑን ሁሉም ይስማማል፡፡

Read more: ልሳነ ግእዝ

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine