ሐሙስ /አምስተኛው ቀን/

በዚህ ዕለት የተደረጉ ዐበይት ድርጊቶች፡-

ð  የትሕትና መምህር የሆነው ጌታችን ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ በመቅረቡ ትሕትናን ሊያስተምር የደቀመዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ ‹‹እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል›› በማለት የትሕትናን ትምህርት አስተምሯል፡፡ /ዮሐ. 131-20/

ð  ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻዋን እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲበላ ምሥጢረ ቁርባንን ከዚህች ዕለት መስርቷል፡፡ ‹‹ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራውን አንስቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና እባካችሁ ብሎ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡  ጽዋውንም›› አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፡፡ ሁለታችሁም ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡ በማለት ስለኛ በፈሰሰ ደሙ በኃጢአታችን ይቅርታ አድርጎ እንደታረቀን እንዲህ በማለትም አረጋግጧል፡፡‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፡፡›› /ዮሐ. 1515/

ማቴ. 2626-29         ሉቃ. 227-23

 ð  ጌታችን ደቀመዛሙርቱ ሁሉ በአይሁድ እጅ ሲወድቅ ጥለውት እንደሚሸሹ የመጽሐፍ ትንቢት ጠቅሶ ቢነግራቸው /ዘካ. 137/ ቅዱስ ጳውሎስ ጌታዬ ሞትህን ሞቴ ያድርገው እንጂ አልክድህም አለው፡፡ ጌታም ዶሮ ሳይጮኽ በዚህች ሌሊት ሦስት ጊዜ እንደማታውቀኝ ትክደኛለህ አለው፡፡

ማቴ. 263-35      ማር. 1426-31      ሉቃ. 2231-34    ዮሐ. 1336-38

ð  ደቀመዛሙርቱ ወደ አብ እሄዳለሁ ባላቸው ጊዜ ልባቸው ታወከ እርሱም ‹‹እመኑብኝ እኔ የምሄደው በአባቴ ቤት ካለው ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው›› በማለት አጽናናቸው፡፡ ከሐዋርያት አንዱ ፊሊጶስ አብን አሳየን ቢለው ‹‹እኔን ያየ አብን አይቷል›› በማለት አብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ፣ ወልድ በአብና በመንፈስ ቅዱስ፣ መንፈስ ቅዱስ በአብና በወልድ ሕልዋን እንደሆኑ አስተማራቸው፡፡ አስቀድሞ ከእናንተ እለያለሁ ሲላቸው ብቻቸውን የሚተዋቸው መስሏቸው ታውከው ነበርና እንዲጽናኑ አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን እንደሚሰጣቸው በመግለጽ አረጋጋቸው፡፡ /ዮሐ. 141-17/

ð  ክርስቶስ ሊቀበላት ያለችው መከራ ቀርባለችና ጌቴሴማኒ ወደ ምትባለው የአትክልት ቦታ ገብቶ ወደ አባቱ ጸለየ እናንተም መከራ በመጣባችሁ ጊዜ አስቀድማችሁ ጸልዩ ለማለት አብነት ሲሆነን እንዲህ አደረገ፡፡ እዚህ ላይ ግን ጌታችን መጸለዩ የሚመጣበትን መከራ በመፍራት አይደለም፡፡ አስቀድሞ በዮሐንስ ወንጌል ‹‹ነፍሴን አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል እኔ በፈቃዱ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም›› /ዮሐ. 1017-18/ እንዳለ የሚሞተው በፈቃዱ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ከመሆኑ በፊት ሁሉን የሚያውቀው ክርስቶስ በዚያች ሌሊት ሊይዙት እንደሚመጡ ያውቅ ስለነበር ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ የአይሁድ ጭፍሮችም እርሱን ለመያዝ የደፈሩት ‹‹የምትፈልጉኝ እኔ ነኝ›› በማለት ካደፋፈራቸው በኋላ ነበር፡፡

ማቴ. 2636-46        ማር. 1432-42     

ð  ከደቀመዛሙርቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ ጌታውን በመሳም ለአይሁድ አሳልፎ ሰጠ ጌታም ትእምርተ ፍቅሩን /የፍቅሩን ምልቱን/ ትእምርተ ጽብእ /የጠብ ምልክት/ አድርገኸው መጣኽን በማለት ተናገረው፡፡ ጭፍሮቹም የመላእክት አለቆች በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን ወደ ፊትና ወደ ኋላ እያንገላቱ ወሰዱት በዚያችም ሌሊት አንደበት ከሚገልጸው በላይ አሰቃይተውታል፡፡

ማቴ. 2647-56        ማር. 1443-50   

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine