ረቡዕ /አራተኛው ቀን/

=>  በዚህ ዕለት የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰብስበው እንዴት በተንኮል እንደሚይዙትና እንደሚያስገድሉት ምክር የቆረጡበት ዕለት ነው፡፡ ነገር ግን የፋሲካ በዓል ቀርቦ ስለነበር ሕዝቡም በትምህርቱ ተመስጦ በተአምራቱ ተማርኮ ስለነበር ሁከት እዳይፈጠር እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ሲጨነቁ ከጌታ ደቀመዛሙርት መሃል ይሁዳ ከምክራቸው በመቀላቀል ጭንቃቸውን አቀለለላቸው፡፡

    ማቴ. 2635       ሉቃ. 221-6         ማር. 141እና2

=> ክርስቶስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በማዕድ ተቀምጦ ሳለ ማርያም መግደላዊት የምትባል ዘመኗን በዝሙት ያቃጠለች የመግደሎን አገር ሴት መጣች፡፡ ይህች ሴት ቀረሽ የማትባል ቆንጆ ነበረች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ሰውነቷን በመስታወት ተመልክታ ፈራሽ በስባሽ መሆኑን ስትረዳ በዚህ ገላዋ ባፈራችው ገንዘብ የማያልፈውን መንግሥት ለማግኘት ኃጢአቷን ለማስተሰረይ ቆርጣ ሽቶ ልትገዛ ሄድኖክ ከሚባል ነጋዴ ለነገሥታት የሚገባ ሽቶ ስጠኝ ብላ 3፻ ወቄት ወርቅ ሰጠችው፡፡ እርሱም በዘመናቸው ሐሰት የለም ነበርና ይህን ያህል የሚያወጣ የለኝም አላት ነገር ግን እናቱ የምታውቀው ዳዊት ሰሎሞን ተቀብተውበት የተረፈ ነበርና እርሱን ሸጠላት፡፡ እርሷም በስምዖን ቤት ገብታ በእግሩ ሥር በመደፋት ስለ ኃጢአቷ አነባች ንስሐዋንም ተቀብሎ ይቅር አላት፡፡ ያንንም ሽቶ አምጥታ ራሱን ቀባችው፡፡ ይህ ያዩ ሐዋርያት ተቆጡ ለምን ተሸጦ ገንዘቡ ለደሀ አይሰጥም ሲሉ፡፡ ነገር ግን ምሥጢሩ ጌታን ለመቃብሩ ስታዘጋጀው ነበር፡፡ ይህ ያስከፋው ይሁዳ ለድሆች ከሚሰጠው ገንዘብ ለራሱ ያስቀር ስለነበር ድርሻውን ለማስመለስ ጌታውን በ30 ብር ለመሸጥ በቃ፡፡ ለማርያም ግን ጌታችን ‹‹. . .  እርስዋ ያደረገችውን ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል›› እንዳለላት ይህንን ታሪክ አራቱም ወንጌላውያን መዝግበውታል፡፡

    ማቴ. 266-13      ማር. 143-9        ሉቃ. 737-39         ዮሐ. 121-8

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine