ማክሰኞ /ሦስተኛው ቀን/

በዚህ ዕለት የተደረጉት ዐበይት ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡

ð  ደቀመዛሙርቱ የበለሷን መድረቅ አይተው ሲገረሙ ጌታችን ሃይማኖት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩ ይህን ተራራ ከዚህ ተነስተህ ከባሕር ግባ ብትሉት ይቻላችኋል ብሎ ስለ እምነት አስተምሯቸዋል፡፡

ማቴ. 2120-21 ፣ ማር. 1120-26  ዮሐ. 141

ð  በቤተመቅደስ ሲያስተምር ሳለ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች መጥተው ከምድራውያን ካህናት ወገን ያይደለህ ከምድራውያን ነገሥታት ወገን ያይደለህ ይህን የምታደርግ በምን ሥልጣንህ ነው ብለው ጠየቁት እርሱም ከእናንተ አኔ ቅድሚያ አለኝ ሲል ጠየቃቸው ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነው?›› (ዮሐንስ ማስተማሩ በማን ፈቃድ ነው?) እነሱም ከሰማይ እንዳይሉ አያምኑበት ከምድር እንዳይሉ ሕዝቡን ፈሩትና አናውቅም አሉት እርሱም እኔም አልነግራችሁም ብሎ ረታቸው፡፡

ማቴ. 2123-27፣ ማር. 112733 ሉቃ. 202140

 

ð  አይሁድም ተሰብስበው ሳሉ ክርስቶስ ስለ ራሱ ማንነት ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም የዳዊት ልጅ ነው ብለው መለሱለት እርሱም ‹‹እግዚአብሔር ጌታዬን …››            /መዝ. 1091/ በመጥቀስ የዳዊት ልጅ ከሆነ እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው እነርሱም አንዲት ቃል እንኳን ሊመልሱለት ተስኗቸው ዝም አሉ፡፡

ማቴ. 224146    ማር. 123536    ሉቃ. 2041-44

ð  ጸሐፍት ፈሪሳውያንን በግብዝነታቸው እየወቀሰ ለሐዋርያቱና ለሕዝቡ ‹‹በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋልና ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም ነገር ግ እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ፡፡ ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ እነሱ ግን በጣታቸውስ እንኳ ሊነኩት አይወዱም›› በማለት እየወቀሰ ተናግሯል፡፡

ማቴ. 231-39    ሉቃ. 2045-47

ð  ጌታ በምጽዋት ሳጥን ፊት ተቀምጦ ሳለ ያለትን ሁሉ ምንም ሳታስቀር የሰጠችውን የድሀዋን መበለት ስጦታ አደነቀ፡፡ ምንም እንኳን ከሀብታሞቹ ያነሰ ብትሰጥም እርሷ ያላትን ሁሉ ስትሰጥ እነርሱ ግን ከትርፋቸው ሰጥተዋልና፡፡

ማር. 1241-44    ሉቃ. 211-4

ð  ስለዳግም ምጽአቱ ሰፊ ትምህርት የሰጠበትም ዕለት ነው፡፡ ከላይ ‹‹ደብረዘይት›› በሚለው ክፍል የተገለጸው በዚህ ዕለት የተነገረ ነው፡፡

ð  በአጠቃላይ ይህ ዕለት በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ጥያቄ የቀረበበትና መልስ የተሰጠበት ዕለት ስለሆነ የጥያቄ ቀን፣ ሰፊ ትምህርት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑም የትምህርት ቀን በመባል ይታወቃል፡፡

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine