የመዝሙር ግጥሞች

የምስጋና መዝሙራት - በምን በምን

በምን በምን

በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን

ምሳሌ የላትም ክብሯን የሚመጥን

                  የሙሴ ጽላት ነሽ የምህረት ቃል ኪዳን

                  የያእቆብ መሰላል የአብርሀም ድንኳን

                  የብርሃን መውጫ የኖህ ድንቅ መርከብ

                  የመላእክት እህት የሩህሩሃን እርግብ

የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር

የእዝራ መሰንቆ የጌድዮን ፀምር

ድንግል እመቤት ናት የፃድቃኖች በር

ሆና የተገኘች የአምላክ ማህደር

                  የቅዱሳን እናት የአለም ንግስት

                  ችላ የተሸከመች መለኮተ እሳት

                  ብርሃን ትሁነን ጨለማን ገላልጣ

                  አማልዳ ታስምረን ከዚህ አለም ጣጣ

ከማር ይጣፍጣል የድንግል መአዛ

አምላክን አቅፋለች በሁለት እጇ ይዛ

አለም ሁሉ የዳነው በልጅሽ ነውና

እናታችን ፅዮን ይድረስሽ ምስጋና

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine