የመዝሙር ግጥሞች

የምስጋና መዝሙራት

 

አንደበቴም ያውጣ

አንደበቴም ያውጣ የምስጋናን ቅኔ

የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በአይኔ

በገባዖን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ

ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ

            ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ

            ከሃጥያት ፍላጻ ከሞት አመለጥኩን

            የአናብስቱን አፍ በሀይሉ የዘጋ

            የዳንኤል አምላክ ይኞራል ከእኔጋ

በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ

ከቅዱሳን ጋራ ልዘምር አበሬ

እሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ

ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁ

            አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድ

            ለጣኦት እንድሰግድ ነገስታት ቢያውጁ

            ሁሉም ቢተወኝ ቢጠላኝም ዓለም

            ጽናት ይሆነኛል ጌታ መድሀኔአለም

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine