የመዝሙር ግጥሞች

የጥምቀት የከተራ መዝሙራት (ጥር 10 እና ጥር 11)

የጥምቀት የከተራ መዝሙራት (ጥር 10 እና ጥር 11)

 

1.  ከድንግል ተወልዶ

ከድንግል ተወልዶ እኛን ሊቀድስ

ተጠመቀ ኢየሱስ በባሕረ ዮርዳኖስ /2 ጊዜ/

         መጥምቁ ዮሐንስ ምንኛ ታደለ

         ከነቢያት ሁሉ ሥልጣኑ ከፍ አለ

ትንቢቱን ሊፈጽም አስቦ ክርስቶስ

ተጠምቆ አዳነን በባሕረ ዮርዳኖስ

         ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዚያን ለታ

         ምን ይከፈለዋል ለአምላክ ውለታ

እመቤቴ ማርያም ምንኛ ታደልሽ

ከአዳም ልጆች ሁሉ አንቺ ተመረጥሽ

         ቸሩ አባታችን መድኃኔዓለምን

         ኑ እናመስግነው በአንድነት ሆነን

2.  ዮሐንስ አጥመቆ

ዮሐንስ አጥመቆ ለኢየሱስ /2ጊዜ/

በፈለገ ዮርዳኖስ በፈለገ /2ጊዜ/ ዮርዳኖስ /2ጊዜ/

 

3.  ሖረ ኢየሱስ

ሖረ ኢየሱስ /2ጊዜ/

እም ገሊላ /3ጊዜ/ ኀበ ዮርዳኖስ /2ጊዜ/

 

4.  መጽአ ቃል

መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል /2ጊዜ/

ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር /4ጊዜ/

 

5.  ኀዲጎ ተስዓ

ኀዲጎ ተስዓ ወተስዓተ ነገደ /2ጊዜ/

ማዕከለ ባሕር /4ጊዜ/ ቆመ ማዕከለ ባሕር /2ጊዜ/

 

6.  ተጠምቀ ሰማያዊ

ሀሌ /3ጊዜ/ ሉያ ሀሌ /2ጊዜ/ ሉያ ሀሌ ሉያ /2ጊዜ/

ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ /4ጊዜ/

 

7.  ኀዲጎ ተስዓ

ኀዲጎ ተስዓ /8ጊዜ/

ወተስዓተ /2ጊዜ/ ተስዓተ ነገደ /2ጊዜ/

 

8.  ወተመሰሎ

ወተመስሎ ሰባዐ ዓይነ አባግዐ ላባ ወማይ /2ጊዜ/

ወጥምቀት ዐባይ /2ጊዜ/ ዐባይ /2ጊዜ/ ወጥምቀት ዐባይ /2ጊዜ/

 

9.  ኧኸ ኀዲጎ ተስዓ

ኧኸ ኀዲጎ ተስዓ  ኧኸ ወተስዓተ ነገድ /2ጊዜ/

ኧኸ ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር /2ጊዜ/

 

10.     ዮሐንስኒ ሀሎ

ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ /2ጊዜ/

በሄኖን በቅሩበ ሳሌም /4ጊዜ/

 

11.     ወረደ ወልድ

ወረደ ወልድ /6ጊዜ/

እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት /4ጊዜ/

 

12.     እንዘ ሕፃን

እንዘ ሕፃን ልሕቅ በዮርዳኖስ ተጠምቀ

በዮርዳኖስ /3ጊዜ/ ተጠምቀ በዮሐንስ

 

13.     ግነዩ ለእግዚአብሔር

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር /2ጊዜ/

እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም /4ጊዜ/

         እናመስግንሽ የአምላክ እናት በዝማሬ /2ጊዜ/

         የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ /4ጊዜ/

በድንግልና የወለድሽው ያንችው ጽንስ /2ጊዜ/

ለድኩማኖች ብርታት ነው ለሕሙማን ፈውስ /4ጊዜ/

         ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ /2ጊዜ/

   መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ /4ጊዜ/

በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ /2ጊዜ/

በቸርነቱ ጠብቆ ከበደል አራቀን /4ጊዜ/

         ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም ያዘከረ /2ጊዜ/

         በመንግሥተ ሰማይ ይኖራል እንደተከበረ /4ጊዜ/

እመቤታችን እናታችን ማርያም /2ጊዜ/

የተማፀነሽ ይኖራል እስከ ዘለዓለም /4ጊዜ/

         ኃይለ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ /2ጊዜ/

         ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ /4ጊዜ/

14.    በእደ ዮሐንስ

በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ /2ጊዜ/

ሰማያዊ /5ጊዜ/ ኢየሱስ ናዝራዊ /2ጊዜ/

ትርጉም ፡- ሰማያዊው የናዝሬቱ ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ

 

15.    እግዚኡ መርሐ

እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብጽሐ /2ጊዜ/

ወበህየ ዮሐንስ /2ጊዜ/ ፍጹመ ተፈሥሐ /2ጊዜ/

ትርጉም፡-

ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው /2ጊዜ/

በዚህም ዮሐንስ /2ጊዜ/ በፍጹም ደስ አለው /2ጊዜ/

 

16.    ውስተ ማኅፀነ

ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ ማኅፀነ ድንግል /2ጊዜ/

ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ ሰማይ ወምድር በማይ ተጠምቀ /2ጊዜ/

ትርጉም፡- ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ

      በእመቤታቸን ማኅፀን አደረ በውኃ ተጠመቀ

 

17.    የዓለምን በደል

የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ

ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ

ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ

         የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ

         አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ

የሰማየ ሰማይ የማይችለው ንጉሥ

ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ

ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ በመንፈስ

         ባሕር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ

         ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ

         እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ

ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሠርት

መጣ በደመና ሰማያዊው አባት

እየመሰከረ የልጁን ጌትነት

         እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ

         መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ

         በርግብ ምሳሌ ክንፉን አሰይፎ

ባሕር ስትጨነቅ ተራራው ሲዘምር

ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር

ዓለም በዛሬው ቀን አየች ይህን ምሥጢር

 

18.    ጥምቀተ ባሕር

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2ጊዜ/

ሀሌ ሉያ /4ጊዜ/

               ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች

               አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች

               ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ

               ዮርዳኖስም ሸሸ ሄደ ወደ ኋላ

አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ

መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ

ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና

ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና

               ጌታችን ሲጠመቅ በ30 ዓመት

               ባሕር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት

               ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ

               ምሥጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ

እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ

የጽድቅ መሰላል የድኅነታችን መገኛ

ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ

እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine