የመዝሙር ግጥሞች

የንስሓ መዝሙራት

እንደበደሌማ

እንደበደሌማ ከሆነ ቅጣቴ

አያልቅም ተነግሮ ብዙ ነው ጥፋቴ

እንጃልኝ ፈራሁኝ አዬ ሰውነቴ/2/

      እመለሳለሁ እያልኩ ጠዋት ማታ

      ዘመኔን ጨረስኩ ሳስብ ሳመነታ

      ምን እመልስ ይሆን የተጠራሁ ለታ/2/

በላዬ ሲያንዣብብ ሞት እጁን ዘርግቶ

ስጋዬን ሲውጠው መቃብር ተከፍቶ/

የነፍሴ ማረፊያ ወዴት ይሆን ከቶ/2/

      ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን

      አቤቱ ጌታ ሆይ እኔን ባሪያህን

      ይቅር በለኝና ልየው ፊትህን/2

እኔስ በምግባሬ

  እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኛለሁ/2/

እዘኝልኝ ድንግል እለምንሻለሁ/2/

      ያንን የእሳት ባህር እንዳላይ አደራ

      እዘኝልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ/2/

የዳዊት መሰንቆ የኤልያስ መና

የናሆም መድሃኒት ንኢ በደመና/2/

      አንቺ ነሽ ጉልበቴ በደከመኝ ጊዜ

      የልቤ መፅናኛ እረዳት ምርኩዜ/2/

አፈሳለሁ እንባ በጣም ተጨንቄ

እማፀንሻለሁ በደሌን አውቄ/2/

አቤቱ አንተን እጠራለሁ

አቤቱ አንተን እጠራለሁ

ነፍሴን ወደአንተ አነሳለሁ

ዝም አትበለኝ እጮሀለሁ/2/

      የሀጥያት ሸክም ከብዶኛል

      የስጋ ወጥመድም አስሮኛል

      የሰይጣን ፍላፅ አጥቅቶኛል/2/

ደካማ ነኝ በጣም ችግረኛ

ምስኪን ተስፋ ቢስ አነስተና

ከመንጋው የራኩኝ ብቸኛ/2/

      ሀጥያቴን ሁሉ ይቅር በለኝ

      የንስሐን በር ክፈትልኝ

      መጣሁኝ ጌታ ተቀበለኝ/2/

ከአንተ ኮብልዬ ተንከራተትኩ

ምንም ላይረባኝ ከንቱ ባዘንኩ

ለበስባሽ ስጋዬ ተገዛሁ/2/

      የቤትህ ናፍቆት አቃጠለኝ

      የቃልህ በረከት እራቀኝ

   እባክህ ጌታ ይቅር በለኝ/2/

የሰው ልጅ ሁልጊዜ

የሰው ልጅ ሁልጊዜ በጣም ደስ ቢለው/2/

ደግሞም የጭንቁን ቀን ማሰብ ተገቢ ነው/2/

ምንም ቢደሰቱ ቢበዛ ምቾት/2/

አይቀርም በኋላ መወሰድ በሞት/2/

ችግር ቢፈራረቅ ሀዘን ቢከበን/2/

ከክርስቶስ ፍቅር ማንም አይለየን/2/

ሳናውቀው ዲያቢሎስ እንዳይነጣጥለን /2/

ነቅተን እንጠብቀው የእምነትን ሰይፍ ይዘን/2/

ልቤ አቤት በል እንጂ

ልቤ አቤት በል እንጂ አምላኬ ሲጣራ

ሀጥያትን ተውና መልካም ምግባር ስራ

በደሌን አውቄ ይቅርታ ልጠይቅ

ሁሉን ቻይ ነህና ፍጥረትን የማትንቅ

      አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ

      አውቃለሁ አምላኬን ብዙ በድያለሁ

      ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ

      ጎስቋላ ሆኛለሁ ሀጥያት ያደከመኝ

መንገድ ተላልፌ ፈጣሪ አስቀየምኩህ

በሚጠፋ ንብረት አምላኬን ለወጥኩህ

አሁን ግን አምኜ ብዙ እንደበደልኩህ

ምህረትን እንዳገኝ ይቅርታን ለመንኩህ

      የሀጥያት መጋረጃ ፊቴን ሸፍኖታል

      ሀይሌ ከኔ እርቆ መቆም ተስኖኛል

      ነሽና በፊቱ ክብር ሞገስ ያለሽ

      ድንግል ልመናዬን አድርሽ ከልጅሽ

ጉልበት አንተ ሁነኝ መተማመኛዬ

በደሌን አጥፋልኝ ሁን አስተማሪዬ

ከበደል እንድርቅ እጅህን ዘርጋና

ዳግም እንዳልበድል አፅናኝ በምስጋና

እመቤቴ ማርያም

እመቤቴ ማርያም እለምንሻለሁ

በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄአለሁ

እመቤቴ ስሚኝ ተማፅኜሻለሁ/2/

      ሀዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለሁ

      ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለሁ

      እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለሁ/2/

ሀዘኑ በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ

እንደምን ልቻለው እኔስ ደካማ ነኝ

የአማኑኤል እናት ፈጥነሽ ድረሽልን/2/

      በጣም ተንገዳገድኩ ልወድቅ ነው እኔ

      እመአምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ

ምንም አጋር የለኝ ከአንቺ በቀር ለእኔ/2/

አልተወኝም ጌታ

አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል/2/

ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል

ዛሬም ስበድለው ልሄ ነሽ ይለኛል

 በበደል ጉራንር በሀጥያት ጫካ

   ብጠፋበት እንኳ አልተወኝም ጌታ

   ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል

  ካስ አልጠላኝም ጌታ ይወደኛል

ለስልጣን ለክብሬ ብዬ ስክደው

ለገንዘብ አድልቼ እኔ ብረሳው

ለእኔ ያለው ፍቅር አልቀነሰብኝም

ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም

   ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለው ወሰን

   ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን

   በሕይወቴ ሁሉ ፍፁም ለመራኝ

   ክብርና ምስጋናን አቀርባለሁኝ

ኑ ተመልከቱልኝ

ኑ ተመልከቱልኝ የአምላኬን ቸርነት

አንደበት የለኝም ስራውን ለማውራት/2/

ሰላምና ፍቅሩ በልቤ ተሞልቷል

በምን ቋንቋ ላውራው ቃላት አጥረውኛል/2/

      ሰማይ ጉም ቢመስል ቀላይት ቢናጉ

      የጥፋት አጋንንት እጅጉን ቢተጉ

      እኔን የሚጠብቅ አይኑን አይሰውርም

      እረኛዬ ከኔ ዘወትር አይርቅም/2/

ፍርሃት ከእኔ እራቅ ጨለማ ተወገድ

በጌታዬ ትምክህት እንደልቤ ልሒድ

የሞት አበጋዞች ተስፈቸው ጨልሟል

እግዚአብሔር ሊያድነኝ ከአጠገቤ ቆሟል/2/

      ቅዱሳን በሙሉ ለእኔ ዘብ ቆመዋል

      ወደ እነርሱ ህብረት ሊስቡኝ ጓጉተዋል

      ዘወትር በመሃል ድንግል ትመጣለች

      በብርሃን እጆቿ ትባርከኛለች/2/

በጌቴ ሰማኔ

በጌቴ ሰማኔ በአታክልቱ ቦታ/2/

ለኛ ሲል ጌታችን በአለም ተንገላታ/2/

አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት/2/

እኛም ነበረብን የዘለአለም ሞት/2/

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ/2/

ይገርፉት ነበር ሁሉም በየተራ/2/

ተጠማሁ /3/ ሲላቸው/2/

ኮምጣጤ አመጡለት ከሀሞት ቀላቅለው/2/

ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ/2/

እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ/2/

በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው/2/

እንዲህ ሲል ፀለየ አባት ሆይ ማራቸው/2/

በረቂቅ ስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ/2/

በሰው ልጅ ተገርፎ ሞተ ተቀበረ/2/

ፍቅሩን የገለፀው ተወልዶ በስጋ/2/

ኢየሱስ ጌታ ነው አልፋና ኦሜጋ/2/

ጌታ ሆይ

 ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ወይ

የአለም መድሃኒት የአለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ/2/

የአዳም በደል አደረሰህ እንተን ለመሰቀል

የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/

ንፁሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ ብለህ ስለእኛ

መስቀል አሸክመው አስረው ገረፉህ/2/

እጅና እግርህ በብረት ተወጋ የአለም ጌታ

የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/

ግብዞችም እንደራሳቸው መስሏቸው

ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/

በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል

ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/

ይቅር ባይ በደላችንን ሁሉን ሳታይ

አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ/2/

አድኝኝ እናቴ

አድኝኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና

ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና

ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለው

አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለው /2ጊዜ/

            የአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል

                  አትጥፊ ከፊቴ እንድትሆኝን ኃይል

                  ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቁልና

                  ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና /2ጊዜ/

      ተስፋዬ ነሽና እመካብሻለው

      ግራ ቀኝ አልልም ምርኮኛሽ ሆኛለው

      ስቅበዘበዝ አይቶ ተስፋ የሰጠኝ

      እግዚአብሔር ይመስገን ከአንቺ ያስጠጋኝ /2ጊዜ/

                  በሥጋ ደክሜ በነፍስ እንዳልጠፋ

                  እማጸንሻለው ድንግል የኔ ተስፋ

                  የመንግሥቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ

                  መልካም ሥራን መሥራት እኔን አስተምሪኝ /2ጊዜ/

      አንቺ የሌለሽበት ጉባኤ ባዶ ነው

      በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው

      ከመካከል ገብተሸ ሙይው ጎዶሎውን

      ሠርጉ ተደግሷል ጎብኝልን ጓዳውን /2ጊዜ/

ጌታ ሆይ ውለታህ

ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው

አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው /3ጊዜ/

            በሐዋርያት አድረህ ብዙ መክረኸኛል

            ስለ ኃጢአቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተኸኛል

            ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው

አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው

      በሐዘኔ ደርሰህ ፈጥነህ አረጋጋኸኝ

      አይዞህ ልጄ ብለህ ስወድቅ አነሳኸኝ

      ከማይጠፋ እሳት ከሞት አወጣኸኝ

      ለአንተ የምከፍለው ምን ስጦታ አለኝ

                  እውነተኛ ረዳት ወገኔ አንተ ነህ

                  ጌታ ሆይ ከእናት ፍቅር እጅግ ትበልጣለህ

                  መታመን በአንተ ነው ደግሞም መመካት

                  ወቅት የማይለውጥህ የማታውቅ ወረት

      ስምህ ምግቤ ሆኖ ስጠራህ ጠግባለው

      ፍቅርህን ቀምሼ ፍጹም እረካለው

      በሰማይ በምድር በነፍስም በሥጋ

      በአንተ እመካለው አልፋና ኦሜጋ

እናት አለኝ

እናት አለኝ እኔስ እናት አለኝ

ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ የምታጽናናኝ

እናት አለኝ እኔስ እናት አለኝ

            የተቀኘላት ዕዝራ በመሰንቆ

            እናትነቷን ንጽሕናዋን አውቆ

            ያመሰገናት ዳዊት በበገና

            አትለየኝም እናቴ ናትና /2ጊዜ/

ሳለቅስ ስተክዝ ወድቄ ከፊቷ

አቅፋ አጽናናችኝ እኔን ከደረቷ

ታነባለች ሁሌ ለኃጥአን

ትማጸናለች በእንባ ዘውትር ልጇን /2ጊዜ/

            የአዳም ተስፋ ናት ድንግል እናታችን

            መርጦ ያደረባት ክርስቶስ ጌታችን

            ታማልዳለች ዛሬም ለዘለዓለም

            የአምላክ እናት ናት የፍጥረታት ሰላም /2ጊዜ/

ልቤ አቤት በል እንጂ

ልቤ አቤት በል እንጂ አምላኬ ሲጣራ

ኃጢአትን ተውና መልካም ምግባር ሥራ

በደሌን አውቄ ይቅርታን ልጠይቅ

ሁሉን ቻይ ነህና ፍጥረትን የማትንቅ

            አለቅሳለው ዘውትር አነባለው

            አውቃለው አምላኬ ብዙ በድያለው

            ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ

            ጎስቋላ ሆኛለው ኃጢአቴ አደከመኝ

መንገድ ተላልፌ ፈጠሪ አስቀየምኩ

በሚጠፋ ንብረት አምላኬን ለወጥኩ

አሁን ግን አምኜ ብዙ እንደበደልኩ

ምሕረትን እንዳገኝ ይቅርታን ለመንኩ

            የኃጢአት መጋረጃ ፊቴን ሸፍኖታል

            ኃይሌ ከኔ ርቆ መቆም ተስኖኛል

            ነሽና በፊቱ ክብር ሞገስ ያለሽ

            ድንግል ልመናዬን አድርሺ ከልጅሽ

ጉልበት አንተ ሁነኝ መተማመኛዬ

በደሌን አጥፋልኝ ሁን አስተማሪዬ

ከበደል እንድርቅ እጅህን ዘርጋና

ዳግም እንዳልበድል አጽናኝ በምስጋና

አቤቱ አንተን እጠራለው

አቤቱ አንተን እጠራለው

ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለው

ዝም አትበለኝ እጮሃለው /2ጊዜ/

            የኃጢአት ሸክም ከብዶኛል

            የሥጋ ወጥመድም አስሮኛል

            የሰይጣን ፍላጻ አጥቅቶኛል /2ጊዜ/

ደካማ ነኝ በጣም ችግረኛ

ምስኪን ተስፋ ቢስ አነስተኛ

ከመንጋህ የራቁኝ ብቸኛ /2ጊዜ/

            የቤትህ ናፍቆት አቃጠለኝ

            የቃልህ በረከት እራቀኝ

            እባክህ ጌታ ይቅር በለኝ /2ጊዜ/

ከአንተ ኮብልዬ ተንከራተትኩኝ

ምንም ላይረባኝ ከንቱ ባከንኩኝ

ለበስባሽ ሥጋ እየተገዛሁኝ /2ጊዜ/

            ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ

            የንስሓ በር ክፈትልኝ

            መጣሁኝ ጌታ ተቀበለኝ /2ጊዜ/

እኔስ በምግባሬ

እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኛለው /2ጊዜ/

እዘኝልኝ ድንግል እለምንሻለው

እዘኝልኝ ድንግል እማጸንሻለው

            ያንን የእሳት ባሕር እንዳላይ አደራ

            ድረሽልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ /2ጊዜ/

የዳዊት በገና የኤልያስ መና

የናሆም መድኃኒት ነይ በደመና /2ጊዜ/

            አንቺ ነሽ ጉልበቴ  በደከመኝ ጊዜ

            የልቤ መጽናኛ እረዳት ምርኩዜ /2ጊዜ/

አፈሳለው እንባ በጣም ተጨንቄ

እማጸንሻለው በደሌን አውቄ /2ጊዜ/

እመቤቴ ማርያም

እመቤቴ ማርያም እለምንሻለው

በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄአለው

እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለው /2ጊዜ/

ሐዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለው

ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለው

እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለው /2ጊዜ/

ሐዘኑ በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ

እንደምን ልቻለው እኔ ደካማ ነኝ

የዐማኑኤል እናት ፈጥነሽ ድረሽልኝ /2ጊዜ/

በጣም ተንገዳገድከ ልወድቅ ነው እኔ

እመ አምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ

ምንም አጋር የለኝ ከአንቺ በቀር ለእኔ /2ጊዜ/

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine