የመዝሙር ግጥሞች

ጸንተን እንጠብቀው

የደብረ ዘይት መዝሙራት

 ጸንተን እንጠብቀው

ከመላእክት ጋራ ሲገለጥ በሰማይ

ጸንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ

በግርማ ሲመጣ በአስደንጋጭ ሁኔታ

ወዮልሽ ነፍሴ ሆይ ወየው የዛን ለታ

            ኧኸ ምስጋና ይድረስ ሁልጊዜ ጠዋት ማታ

            ሀሌ /2ጊዜ/ ሉያ የሠራዊት ጌታ /2ጊዜ/

ሰማይና ምድር ከፊቱ ሲሸሹ

መግቢያ አቶ ይጮሃል ትልቁ ትንሹ

ጻድቃን ሲደሰቱ የኃጥአን ፋንታ

ሆኖ ጠበቃቸው ለቅሶና ዋይታ

            ስለማይታወቅ አምላክ አመጣጥህ

            በሃይማኖት አጽናን ጸንተን እንጠብቅህ

            ጠላት እንዳይገዛን በእርሱ እንዳንረታ

            እግዚአብሔር አድነን ሁንልን መከታ

የጥምቀት የከተራ መዝሙራት (ጥር 10 እና ጥር 11)

የጥምቀት የከተራ መዝሙራት (ጥር 10 እና ጥር 11)

 

1.  ከድንግል ተወልዶ

ከድንግል ተወልዶ እኛን ሊቀድስ

ተጠመቀ ኢየሱስ በባሕረ ዮርዳኖስ /2 ጊዜ/

         መጥምቁ ዮሐንስ ምንኛ ታደለ

         ከነቢያት ሁሉ ሥልጣኑ ከፍ አለ

ትንቢቱን ሊፈጽም አስቦ ክርስቶስ

ተጠምቆ አዳነን በባሕረ ዮርዳኖስ

         ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዚያን ለታ

         ምን ይከፈለዋል ለአምላክ ውለታ

እመቤቴ ማርያም ምንኛ ታደልሽ

ከአዳም ልጆች ሁሉ አንቺ ተመረጥሽ

         ቸሩ አባታችን መድኃኔዓለምን

         ኑ እናመስግነው በአንድነት ሆነን

2.  ዮሐንስ አጥመቆ

ዮሐንስ አጥመቆ ለኢየሱስ /2ጊዜ/

በፈለገ ዮርዳኖስ በፈለገ /2ጊዜ/ ዮርዳኖስ /2ጊዜ/

 

3.  ሖረ ኢየሱስ

ሖረ ኢየሱስ /2ጊዜ/

እም ገሊላ /3ጊዜ/ ኀበ ዮርዳኖስ /2ጊዜ/

 

4.  መጽአ ቃል

መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል /2ጊዜ/

ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር /4ጊዜ/

 

5.  ኀዲጎ ተስዓ

ኀዲጎ ተስዓ ወተስዓተ ነገደ /2ጊዜ/

ማዕከለ ባሕር /4ጊዜ/ ቆመ ማዕከለ ባሕር /2ጊዜ/

 

6.  ተጠምቀ ሰማያዊ

ሀሌ /3ጊዜ/ ሉያ ሀሌ /2ጊዜ/ ሉያ ሀሌ ሉያ /2ጊዜ/

ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ /4ጊዜ/

 

7.  ኀዲጎ ተስዓ

ኀዲጎ ተስዓ /8ጊዜ/

ወተስዓተ /2ጊዜ/ ተስዓተ ነገደ /2ጊዜ/

 

8.  ወተመሰሎ

ወተመስሎ ሰባዐ ዓይነ አባግዐ ላባ ወማይ /2ጊዜ/

ወጥምቀት ዐባይ /2ጊዜ/ ዐባይ /2ጊዜ/ ወጥምቀት ዐባይ /2ጊዜ/

 

9.  ኧኸ ኀዲጎ ተስዓ

ኧኸ ኀዲጎ ተስዓ  ኧኸ ወተስዓተ ነገድ /2ጊዜ/

ኧኸ ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር /2ጊዜ/

 

10.     ዮሐንስኒ ሀሎ

ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ /2ጊዜ/

በሄኖን በቅሩበ ሳሌም /4ጊዜ/

Read more: የጥምቀት የከተራ መዝሙራት (ጥር 10 እና ጥር 11)

የስቅለት መዝሙራት

ስቀለው ስቀለው

ስቀለው /2ጊዜ/ እያሉ አይሁድ በአንተ ላይ ተባባሉ

እውነተኛ ዳኛ አንተ ሆነህ ሳለህ

የጲላጦስን ፍርድ ፍቅርህ ተቀበለ

      ጌታ ይቅር በለን /2ጊዜ/

      ምንም ብንበድልህ የእጆችህ ሥራ ነን /2ጊዜ/

ተጠማው /2ጊዜ/ እያለ በቀራንዮ ላይ በመስቀል ላይ ሆነህ

የአፍላጋት ጌታ አንተ ሆነህ ሳለህ

ኮምጣጤ አመጡልህ ሳለህ ተቸንክረህ

      ማን መታህ ንገረን እያሉ ፊቱን እየጸፉ ሲሳደቡ ዋሉ

      ምንም አልመለሰም ምነውም አላለም

      ሕማሙን በትዕግስት አውቆ ተቀበለ

ምራቅ እየተፉ ፊትህ ላይ ሲመቱህ ሲሰድቡህ ስትሰቃይ

ምንም ሳትመልስ በፍቅር አየሃቸው

በመስቀል ሰቀሉህ ወደህ ሞትክላቸው

      ይቅር ባይ ነህና መሐሪ ትሕትና ፍቅር አስተማሪ

      ጠልተው ለሰቀሉት ለተፉት በፊቱ

      ምሕረትን ጠየቀ ከአብ ከአባቱ

መከራህን ሳስብ ስቃይ መስቀል ላይ እንደዋልህ እርቃንህን

ነፍሴ ተጨነቀች እጅጉን አዘነች

ፍዳና በደሏን እያሰላሰለች

ጌታ ሆይ

ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን ሰቀሉህ ሆይ

የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ሆይ /2ጊዜ/

የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመስቀል

የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት /2ጊዜ/

ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ ብለህ ስለኛ

መስቀል አሸክመው አስረው ገረፉህ እያዳፉህ /2ጊዜ/

እጅና እግርህ በብረት ተመታ የዓለም ጌታ

የሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህም ተወጋ አልፋ ኦሜጋ /2ጊዜ/

ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው

ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ /2ጊዜ/

በመስቀል ላይ ተጠማው ስትል ታላቅ በደል

ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው /2ጊዜ/

ይቅር ባይ በደላችንን ሁሉን ሳታይ

አንተ ይቅር በለን በኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2ጊዜ/

 መስክሪ ቀራንዮ

መስክሪ ቀራንዮ ንገሪን ጎልጎታ

ካሳ እንደሆነልን እንዳዳነን ጌታ

      በአምላክነቱ ፈጥሮ ዓለማትን

      ሥጋን መዋሐዱ ሰዎችን ለማዳን

      ክብሩን ዝቅ አድርጎ በታላቅ ትሕትና

      ሞትን አጠፋልን ያየውን ፈተና

ለፍርድ ሊወሰድ ሊቀበል መከራ

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ

አይሁድ በየተራ ሲገርፉት ሲያዳፉት

እንደታገሳቸው በፍጹም ቸርነት

      ምንም ሳያጠፋ በደል ሳይኖርበት

      በመስቀል እንዲሞት ቅጣት ተፈርዶበት

      ወደ ኋላ ታስሮ ተገርፎ ተመቶ

      ያየውን መከራ የሾህ አክሊል ደፍቶ

በሞቱ ሙታንን ከመቃብር ጠርቶ

በእርሱ ውርደት ክብርን ለሰው ልጆች ሰጥቶ

በሕይወት እንድንኖር ዳግም እንዳንጠፋ

ትንሣኤን መስክሩ በከበረች ሰንበት

ድንግል የዚያን ጊዜ

ድንግል የዚያን ጊዜ  /2ጊዜ/ ሐዘንሽ በረታ  /2ጊዜ/

በመስቀል ላይ ሁኖ ልጅሽ ሲንገላታ  /2ጊዜ/

      የግፍ ግፍ ደርሶበት የዚያን ጊዜ ተጠማው ሲልሽ

      ለውሻ ያጠጣሽ በወርቅ ጫማሽ /2ጊዜ/

ሴቶች ሲያባርሩት የዚያን ጊዜ እራርቶ ሆድሽ

ለፍጡር በማዘን ውሃ ያጠጣሽ  /2ጊዜ/

      ተጠማው እያለ የዚያን ጊዜ ሲናገር ልጅሽ

      ታዲያ እንደምን ቻለው ወላድ አንጀትሽ

እንደዚያ ስታለቅሽ የዚያን ጊዜ ሐዘን ሲውጥሽ

እነማን ነበሩ ያስተዛዘኑሽ /2ጊዜ/

      ስታለቅሽ በማየት የዚያን ጊዜ ራርቶ ሆድሽ

      ዮሐንስን አጽናኝ እንደ ልጅ ሰጠሽ  /2ጊዜ/

በዕፀ መስቀል ላይ

በዕፀ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ

አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ሆይ

አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ሆይ

      መስቀል አስይዘው ኪራላይሶን

      ወደ ጎልጎታ ኪራላይሶን

      ሲገርፉህ ሲያዳፉህ ኪራላይሶን

      ስትንገላታ ኪራላይሶን

ያንን አቀበት ኪራላይሶን

ያንን ዳገት ኪራላይሶን

ጀርባህ ተገርፎ ኪራላይሶን

ስትቃትት ኪራላይሶን

      አንተን እያዩ ኪራላይሶን

      ሴቶች ሲያለቅሱ ኪራላይሶን

      እናቶች ቀርበው ኪራላይሶን

      እንባህን አበሱ ኪራላይሶን

መስቀል አስይዘው ኪራላይሶን

እንዲያ ሲያዳፉህ ኪራላይሶን

የቀሬናው ሰው ኪራላይሶን

ስምዖን አገዘህ ኪራላይሶን

 

ዘጠኝ ሰአት ሲሆን

ዘጠኝ ሰአት ሲሆን አባት ሆይ

በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ

ድምፅን በማሰማት አባት ሆይ

ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ

      ከዋክብት ከሰማይ በሙሉ ረገፉ

      ጨረቃና ፀሐይ ደመና አጎረፉ

      ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ

      ስጋህ በመስቀል ላይ ተጋልጦ ስላዩ

ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ

አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ

ማርና ወተት ለሚመግበው

ሀሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው

      አካሉ ሲወጋ ውሃ ደም ፈሰሰ

      በምድር ተረጭቶ አለምን ቀደሰ

      የእስራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ

      ለእነሱ አዘንክ እንጂ ለአንተም አላሰብክ

እናቱ ስታለቅስ በመስቀል ስር ሆና

ዮሃንስን ሰጣጥ ጠብቆ እንዲያፅናና

መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ

የአይሁድ ሰራዊት ፈርተው ተረበሹ

 

የቅድስት ሥላሴ መዝሙራት (ጥር 7) 2004

የቅድስት ሥላሴ መዝሙራት (ጥር 7)

  1. ነአምን በአብ

ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ /2ጊዜ/

ወነአምን /4ጊዜ/ ነአምን በመንፈስ ቅዱስ /2ጊዜ/

 

ትርጉም፡-

እናምናለን በአብ እናምናለን በወልድ /2ጊዜ/

እናምናለን /4ጊዜ/ እናምናለን በመንፈስ ቅዱስ /2ጊዜ/

Read more: የቅድስት ሥላሴ መዝሙራት (ጥር 7) 2004

የሆሣዕና መዝሙራት

 1.ሆሣዕና እምርት

ሆሣዕና እምርት እንተ አቡነ ዳዊት /2ጊዜ/

ቡርክት /2ጊዜ/ እንተ ትመጽእ መንግሥት /4ጊዜ/

 

2.ሆሣዕና በአርያም

ሆሣዕና በአርያም /2ጊዜ/

ድኅነት ሆነ ለሁላችን ዛሬ በዓለም       /2ጊዜ/

አፍቅሮናል ፈጣሪያችን በኢየሩሳሌም

 

3.ሰላምሽ ዛሬ ነው

ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም

ወዳጅ መጥቷልና አምላክ ዘላለም /2ጊዜ/

            ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ

            ሕፃናት በኢየሩሳሌም

ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት

በኢየሩሳሌም ያሉ ሕፃናት /2ጊዜ/

            አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ

            የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ /2ጊዜ/

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት

መስቀል ተሸክሞ ሊሆን መድኃኒት /2ጊዜ/

            የኢየሱስን ሕማም ደናግላን አይተው

            እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው /2ጊዜ/

 

4.ሆሣዕና

እናቶች አባቶች ሕፃናት በሙሉ

ለዓለም መድኃኒት ሆሣዕና በሉ /2ጊዜ/

            ሆሣዕና /3ጊዜ/ ለወልደ ዳዊት

በአህያ ጀርባ ላይ አምላክ ቁጭ አለና

አሳየ ለሕዝቡ ታላቁን ትህትና /2ጊዜ/

            ቤተመቅደስ ገብቶ የዓለሙ ዳኛ

            ይውጣ ብሎ አዘዘ ሌባና ቀማኛ /2ጊዜ/

 

5.ሆሣዕና በአርያም

ሆሣዕና /2ጊዜ/ በአርያም ሆሣዕና በአርያም

            ቅድስት አገር ሆይ ኢየሩሳሌም

            ምስጋናሽ ብዙ ነው ለመላው ዓለም

በአህያ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ የገባው

ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው

            ኃይልና ስልጣን        ላይ ስላለው

            ጠላቶችሽ ፈሩ ሕዝቦችሽም ደስ አላቸው

  •  Start 
  •  Prev 
  •  1  2  3 
  •  Next 
  •  End 

Page 1 of 3

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine