መዝሙርና ምሥጢራዊ ሥርዓቱ

መዝሙርና ምሥጢራዊ ሥርዓቱ

መዝሙር ምንድን ነው? የሚለውን መጠይቅ ለርዕሰ ነገራችን ሐተታዊ ፍሬ ነገር መነሻ በማድረግ መሠረታዊ ትምህርታችንን እንጀምራለን፡፡

መዝሙር የባሕርይ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በሰማይና በምድር የሚመሰገንበት፣ የሚቀደስበትና የሚለመንበት ዐቢይ የጸሎት ክፍል የሆነ ጣዕመ ዜማ ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና ለአምላካችን ምስጋና ማቅረብ ያማረ ነውና››ይለናል መዝሙረኛው ዳዊት መዝ. 146፥1 በተጨማሪ  ኢሳ. 6፥1-5፣  መዝ. 65፥1-5 መመልከት ሰለ መዝሙር ምንነት ያስረዳል፡፡

መዝሙር ማለት ምን ማለት ነው? ያልን እንደ ሆነ መዝሙር ዘመረ አመሰገነ ካለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙም ምስጋና፣ ልመና ወይም መማፀን፣ ማስደሰት፣ መደሰት፣ ማዜም ማለት ነው፡፡ ከዚህም ሌላ እግዚአብሔርን በእጥፍ ድርብ ማመስገን ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ‹‹ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን እልል እንበል . . . አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና›› ይለናል መዝ. 94፥1-3 ስለ ጠቅላላ ትርጉሙ መዝ. 116፥1-2፣ ኢሳ. 35፥1-6 /38፥9/ መዝ.149፥1-4፣ መዝ. 150፥1-7፣ መዝ. 80፥1-3፣ ማቴ. 26፥30፣ ማር. 14፥26፣ ቆላ. 3፥16፣ ራእ. 14፥1-5 ማቴ. 21፥9፣ ማር. 11፥9፣ ሉቃ. 19፥38 መመልከት ይጠቅማል፡፡ ከላይ እንዳልነው መዝሙር ሲባል ማዜም ማለት ነው፡፡ ዜማ ማለት ራሱ በቀጥታ ሲፈታ ጩኸት /ድምፅን ማሰማት/ ማለት ነው፡፡

ይሁን እንጂ ዜማ የምስጋና ብቻ ሳይሆን የሐዘን /የለቅሶ /የቀረርቶ /የሽለላ /የፉከራና የደስታ ስሜት መግለጫ ድምፅ ነው፡፡ ኢሳ. 6፥1-5  ማቴ. 26፥30

ከዚህ ላይ ግን ዜማ ባልን ጊዜ የምስጋና መዝሙር ድምፅ ሐሴት ማለታችን ነው፡፡ ለምን ቢሉ ዜማ ራሱን የቻለ ጥሬ ቃል ቢሆንም ዘመረ፣ አመሰገነ፣ አዜመ ካለው ቃል ጋር በጠባይና በግብር ይመሳሰላልና ነው፡፡

የመዝሙር ወይም የዜማ ጥቅሙ ምንድን ነው?

ሀ. መዝሙር ለመማሪያና ለማስተማሪያ መዝሙር እግዚአብሔርን በተመስጦ ለማመስገን

ለ.  መዝሙር ወደ እግዚአብሔር ልባዊ ጸሎት ወይም ልመና ለማቅረብ

ሐ. መዝሙር ልብን ለማነፅና ነፍስን ለማስደሰት ማለትም መንፈስን ለማደስ ለምክርና ለተግሣፅ ደግሞም ለማፅናናትና ለመፅናት እጅግ አድርጎ ይጠቅማል፡፡

መዝሙር ወይም ዜማ፡- የተጀመረው በአራቱ ሰማያት ማለትም በሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ በኢዮር፣ በራማና በኤረር በእነዚህ ያሉ መላእክት እግዚአብሔር ፈጣሪያቸውን ያለ ዕረፍት ሲያመሰግኑት ነው፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፡፡ . . . አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጮኹ ነበር፡፡ የመድረኩም መሠረት ከጩዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ ቤቱም ጢስ ሞላበት፡፡›› ይላል ኢሳ. 6፥1-5፣ ራእ. 4፥4 ይህም በኪሩቤልና በሱራፌል ማለት በመላእክት የተጀመረው ጣዕመ ዜማ /መዝሙር/ በእነሱ አሰሚነት ለሰው ልጆች ታድሏል፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሥልጣነ እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፅ የባርነት አገዛዝ ነፃ ባወጣበት ጊዜ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ በደረቅ ምድር ሲያሻግራቸው ሙሴና ተከታዮቹ በተለይም እኅቱ ማርያምና ሙሴ እግዚአብሔርን በከበሮ ድምፅ እያጀቡ በጣዕመ ዜማ አመስግነዋል፡፡ መዝሙርም በይፋ መጀመሩ የታወቀው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ዘጸ. 15፥1-22 ደግሞም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ባየው ራአይ 14፥1-6 በምድር የተዋጁት 144 ሺህ ወገኖች ማንም ያልዘመረውንና ሊዘምረውም የማይቻለውን ጣዕሙ ልዩ የሆነ አዲስ መዝሙር በመድኃኒታችን ዙፋን ፊት በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል እንደዘመሩ ይገልፃል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዜማ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘወትር ፈጣሪዋን የምታመሰግንበት ልዩ ዜማ /መዝሙር/ ከመላእክት የተገኘ ነው፡፡ ስለዚህ መዝሙራችን እስከ አሁን በዓለም ተወዳዳሪ አልተገኘለትም የተገኘውም በኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አማካኝነት ነው፡፡

እኛም አሁን የምንዘምረው መዝሙር በቅዱስ ያሬድ ዜማ ነው፡፡ የቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያው ዜማም አርያም ይባላል፡፡ አርያም ማለትም ልዑል ከፍተኛ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያውን ዜማ አርያም ብሎ የሰየመው ከሰማይ ካሉ መላእክት ሰምቶ መዘመር ስለጀመረ ነው፡፡ ይህም ሲታወቅ ‹‹ቀዳሚ ዜማ ተሰምአ እም ሰማይ›› እያለ ይሄድ እንደነበር ሊቃውንት ይተርካሉ፡፡ ይህ ታላቅ ሊቅ በመንፈሳዊ ተመስጦ ሰማየ ሰማያት ተነጥቆ ከመላእክት ያገኘው ዜማ ዓይነቱ ሦስት ነው፡፡

      እነዚህም፡-    1ኛ. ግእዝ

                  2ኛ. ዕዝል

                  3ኛ. አራራይ ይባላሉ፡፡

እስከ አሁን በዓለም የማናቸውም ፍጥረት ዜማ ጣዕሙ ይለያይ እንጂ በእነዚህ የዜማ ዓይነቶች ብቻ የተጠቃለለ ነው፡፡ እነዚህ ሦስቱ የዜማ ስልቶችም ምሳሌና ትርጉም አላቸው ይኸውም፡-

ግእዝ፡- ርቱዕ ማለት ነው፡፡ አብን ርቱዕ ሎቱ ነአኰቶ ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን ማለት ነው፡፡

ዕዝል፡- ጽኑዕ ማለት ነው፡፡ ወልድ ጽኑዕ መከራ ተቀብሎ አዳምን እንዳዳነው ለማጠየቅ ነው፡፡

አራራይ፡- ጥዑም  ማለት ነው፡፡ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን እንደተጎናጸፍን ለማስረዳት ነው፡፡

ይህም ቢሆን ታዲያ ተነጣጥለው አይቀሩም ግእዝ ከተሰኘው ዜማ ዕዝልና አራራይ ይወጣሉ፡፡ ይህም በአሐዱ አብ ዜማ ይታወቃል፡፡ ምሥጢረ ሥላሴም ከአብ እምቅድመ ዓለም ወልድ ለመወለዱ፣ መንፈስ ቅዱስ ለመስረጹ ምሳሌ ነው፡፡ ከዚህም ጋር የንባቡና የድምፁ ቃና አንድ መሆን የሥላሴን አንድነት ሲያስረዳ የዜማው ሦስት ዓይነት መሆን ደግሞ የሦስትነታቸው ምሳሌ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የያሬድ ዜማ በቂና ጥሩ ጥሩ ምሳሌ ያላቸው 8 ዐበይት ምልክቶች አሉት፡፡ እነዚህም ዜማውን ለሚማር ደቀመዝሙርና ለሚዘምረው ሁሉ ፈረንጆች ኖታ እንደሚሉት በምልክትነት ሲያገለግል ምሳሌያቸውና ምሥጢራቸው ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ስለእኛ የተቀበለውን መከራ የሚያስታውሱን ናቸው፡፡

እነዚህም ኋላ ሊቃውንት ከጨመሯቸው ከድርስና ከአንብር በስተቀር ዋናዎቹ የቅዱስ ያሬድ ብቻ ሲዘረዘሩ፡-

 1. ይዘት ( . ) ፡- በአይሁድ ጭፍሮች ለመያዙ
 2. ሂደት ( )፡- ታስሮ ለመጎተቱ
 3. ጭረት (  )፡- ለግርፋቱ ሰንበር
 4. ድፋት  (┌┐)፡- አክሊል ሾኽ ለመድፋቱ
 5. ደረት  (└┘)፡- ሲሰቅሉት በመስቀሉ ላይ አንጋለው ከደረቱ ላይ ቆመው እየረገጡት ለመቸንከሩ
 6. ርክርክ ( )፡- ለደሙ ነጠብጣብ አወራረድና ለችንካሮች ምልክት
 7. ቁርጥ ( )፡-  በጦር ተወግቶ  ፈጽሞ መሞቱ ለመታወቁ
 8. ቅንአት ( )፡-  በቅንአት አይሁድ ለመግደላቸው

ከላይ የተጠቀሱት ምልክትና መስታወሻዎች ሲሆኑ 8 መሆናቸው 8ቱ ማኅበረ አይሁድ ተባብረውና ተማክረው በብዙ መከራ ለመግደላቸው ምሳሌ ነው፡፡

እነርሱም ፡- 1. ጸሐፍት ፈሪሳውያን                       

            2. ሰዱቃውያን

            3. ረበናት /አይሁድ መምህራን/

            4. መገብተ ምኵራብ /የምኵራብ ሹማምንቶች/

            5. ሊቀ ካህናት

            6. መላሕቅተ ሕዝብ /የሕዝብ ሽማግላች/

            7. ኃጥአን

            8. መጸብኃን ቀራጮች ናቸው፡፡

በሊቃውንት የተጨመሩ ምልክቶች፡-

9.  አንብር (  )

10.  ድርስ ( ስ )

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የማኅበር ጸሎት ሲደርስ በጣዕመ ዜማ ወይም መዝሙር ማመስገንና መጸለይ የተለመደና የተወደደ ሥርዓት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ሲከናወን ለምስጋናውና ለጸሎቱ ማጎልመሻ ሆነው የሚቀርቡት ንዋይተ ቅድሳትና የጸሎት ቅደም ተከተል ሁሉ በቂ ምክንያትና ምሳሌ ያለው ሆኖ መገኘቱ እኛን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ በጣም ያኮራናል፡፡

ይህንንም ለመረዳት በጸሎተ ቅዳሴና በማኅሌት ምስጋና መዝሙር በሚቆምበት ጊዜ የሚፈጸመውን ከልብ መመልከትና ማገናዘብ ይገባል፡፡

ማኅሌት

ማኅሌት ማለት ኃለየ፣ ዘፈነ፣ ዘመረ፣ አመሰገነ ካለው የግእዝ ቃል የወጣ ሆኖ የምስጋና መዝሙር ለእግዚአብሔር ማቅረብ ማለት ነው፡፡

የዚህም ይዘትና አፈፃፀም በአጠቃላይ አቋቋም ይባላል፡፡ አቋቋም ማለት የመቆም ሥርዓት ማለት ሲሆን የበለጠ ሲብራራ ማኅሌቱ ተቁሞ ካህናቱ የሚያገለግሉበት ጊዜ የአገልግሎት ሥርዓት የዜማውን ስልት የሚገልፅ ነው፡፡ በዚህም ውስጥ በበዓላት ቀን ማኅሌቱ የሚገለጥባቸው መንገዶች አሉ እነዚህም፡-

1.   መቃኘት

2.   መቀበል

3.   መምራት

4.   መመራት

5.   ዝማሜ

6.   ቁም /ንዑስ መርግድ/

7.   ዐቢይ መርግድ

8.   ጽፋት /ከአመላለስ መልስ ወረብ ጋር/

9.   ድርብ ጽፋት

10. የጭብጨባ ጽፋት ናቸው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትም ለምን ዐሥር ሆኑ ቢባልም ዳዊት‹‹ወበመዝሙር ዘዐሠርቱ አውታሪሁ እዜምር ለከ›› ማለት ‹‹ዐሥር አውታር ባለው በገናም እዘምርልሃለሁ›› ያለውን መሠረት በማድረግ አይሁድ ጌታን ለመያዝ ይሁዳን አመልካች አድርገው ለመፈለጋቸው ምሳሌ ነው፡፡ መዝ. 143፥9

እነዚህም ግሩም የሆነ ምሳሌና ታሪካዊ ትርጉም አሏቸው፡፡

 1. መቃኘት፡- ቃለ እግዚአብሔርን መምራት እንዲያስታውሱትና በአንድ ቃል እንዲዘምሩ ማድረግ፡፡
 2. መቀበል፡- የተቃኘውን ቃለ እግዚአብሔርን ተቀብሎ በማስተካከል መዘመር ነው፡፡ ትርጉሙ ግን የአይሁድ ጭፍሮች ጌታን ከይሁዳ ተረክበው ፈቃዳቸውን ለመፈጸማቸው ምሳሌ ነው፡፡
 3. መምራት፡-ቃለ እግዚአብሔርን ከመሪው ተቀብሎ ማሰማት ነው፡፡ ይህም፡-

ሀ. የአይሁድ ጭፍሮች በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጌታን ይዘው መጀመሪያ ከሌዊ ካህናቱ ሐና ፊት ለማቅረባቸው ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ. 18፥13

ለ. ከግራ ቀኝ የመሪውን ቃል ማንሳታቸው ጌታን  በየተራ ተቀብለው የፈረዱበት የቀያፋ፣ የጲላጦስ የሄሮድስ ምሳሌ ነው፡፡ ሉቃ. 23፥7  ዮሐ. 18፥24

ሐ. በመጨረሻ ቃለ እግዚአብሔርን ተመልሶ በመሪው በእርሱ ማለቁ ነገረ መስቀሉ በሊቀ ካህናቱ ሐና ተፈጽሟልና በዚያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፡፡

 1. ዝማሜ፡- ዘንግ ከመቋሚያው ጋር ግራና ቀኝ መዘመርና ቀና ብሎ መቋሚያውን ከዜማው ጋር አስማምቶ በመሬት ላይ መጣልና መደለቅ ነው፡፡ ምሳሌው ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐና ወደ ቀያፋ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ መመላለሱን በቀራንዮ መስቀሉን ለማመልከት ነው፡፡ደግሞም ‹‹መኑ ኰርዓከ ተነበየ ለነ›› እያሉ በዘንግ እራስ እራሱን  ደብድበውታልና ኩርዓተ ርዕሱን ለማስታወስ ነው፡፡ ማቴ. 26፥66-68
 2. ቁም /ንዑስ መርግድ/ ፡- በወርኀ ጾም ሽብሸባ /ዝማሜውን በዘንግ ከጨረሱ በጽናጽልና በከበሮ ብቻ በንዑስ ዓመታት ረጋ አድርጎ መዘመር ነው፡፡/
 3. ዐቢይ መርግድ፡- ቁሙን ዜማ በከበሮው ለቀቅ አድርጎ በልዩ ዜማ የሚዘመር ነው፡፡ይህ ዜማ በከበሮ አመታት በጽናጽሉም አጣጣልና አወራረድ የተለየ መልክ አለው የአካልን ንቅናቄ ጭምር የሚያስከትል ነው፡፡ ይህም አይሁድ በሕጋቸው 40 ሲገርፉት ረጋ ብለው ከጀመሩ በኋላ ግርፋቱን በማክበድ ተሳሳትህ መልስ እያሉ 6666 ጊዜ እንደገረፉት ለማስታወስ ነው፡፡
 4. ጽፋት

ሀ. ከአመላለስ /መልስ ወረብ/ ጋር ቃለ እግዚአብሔርን እያፋጠኑ በጽናጽልና በከበሮ መዘመር ነው፡፡ ምሳሌውም ጽፋት ማለት በጥፊ መምታት ማለት ነው፡፡ ጌታ በጥፊ መመታቱን ለማሰብ ነው፡፡

ለ. ወረብ ወይም ለዘብ ባለ አመላለስ የተመረገደውን ቀለም ዐረፍተ ነገር በመጨመር ወይም በመለወጥ መልሶ የተባለውን ዜማ በመሰብሰብ መወረብና በታላቅ ስሜት ተመስጦ በልዩ ከበሮ አመታትና ጭብጨባ መዘመር ነው፡፡

ሐ. ድርብ መርግድ፡- በተለይ በክብረ በዓላት ቀን ወረብ ሲወረብ በርጋታ ተጀምሮ የነበረውን በማድመቅ በዐቢይ መርግድ ላይ የነበረውን አመታትና ሽብሸባ ወይም ዕርግጫ ጠበቅ አድርጎ በመዘመር ማደራረብ ነው፡፡ ምሳሌውም ጌታን ደጋግመው እንደገረፉትና እንደደበደቡት ማስታወስ ነው፡፡ ግራ ቀኝ ሆነው ማስረገጣቸውም አይሁድ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው 340 ጊዜ ረግጠውታል እንደዚያም አድርገውታልና ነው፡፡ከዚህም በላይ በክርስቶስ ስቃይና መከራ ስቅላትና ሞት ጠላት ዲያብሎስ ተረገጠ ለማለት ነው፡፡

 1.  ድርብ ጽፋት፡- በጽናጽሉ አጣጣልና በዜማው ቃና /ጉሮሮው/ ከተራው ጽፋት ባይለይም በከበሮው አመታት ለየት አድርጎ መዘመር ነው፡፡ ምሳሌውም አይሁድ ጌታን ደጋግመው በጥፊ እንደመቱት እንደገፉት ለማስታወስ ነው፡፡
 2. የጭብጨባ ጽፋት፡- ጽፋት ከተራው ጽፋትና ከድርብ ጽፋት ጋር በጉሮሮው በአጣጣሉ በመጠኑ ዘለግ አድርጎ በጽናጽል ፈንታ እያጨበጨቡ በከበሮው መዘመር ነው፡፡ ምሳሌውም ከላይ በጉሮሮ ዝማሬ በ8ኛና በ9ኛ ተራ ቁጥር ላይ እንደተገለጸው ነው፡፡

ያሬዳዊ ዝማሬ የሚቀርብባቸው ንዋየ ቅዱሳት

ይህንን ከልብ ከተረዳህ ለያሬዳዊ ዜማ ማጎልመሻ የሚሆኑት ንዋየ ቅዱሳትን ሁኔታዎች ሁሉ ከየት እንደመጡና ለምን እንዳስፈለጉ እንመለከታለን፡፡

 1. ካህናት እግዚአብሔርን በማኅሌት ሲያመሰግኑት ለመሣሪያነትና ለመደገፊያነት አድርገው መቋሚያ ይይዛሉ፡፡ ይህንን መቋሚያ በመጀመሪያ አባ እንጦንስ የሠሩት ሲሆን ምሳሌውም እግዚአብሔር ለአዳም የሰጠው የትእምርተ መስቀል ተስፋ ነው፡፡ስለሆነም አባ እንጦንስም ቅዱስ ያሬድም በምስጋና ጸሎት ጊዜ ይህንን እንዲያዝ አደረጉ ይህም ልብ-ወለድ ሳይሆን ሙሴ እስራኤልን ሕዝብ ባሕረ ኤርትራን ባሻገረ ጊዜ ተአምራት ያደረገው በዚህ ትእምርተ መስቀል ነው፡፡ ይህንን ትእምርተ መስቀል ተሸክሞ በእስራኤል መካከል ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ›› በማለት አመስግኗል ብለው በሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሆነ ሁሉ ትእምርተ መስቀል መያዝ ግዴታው ነው፡፡ ቢቸግረው እንኳ አፈር ቢኖር መስቀል ስሎ ድንጋይ ቢሆንም በምራቁ አመሳቅሎ እንዲጸልይ ያዛል በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችንም መቋሚያ መያዝ የክርስቶስን መከራ ለማሰብ ነው፡፡ ስለሆነም በጎጃም ክፍለሀገር መሬት ዋሁ በምትባል ሥፍራ የነበሩ መምህር አጽቀ ድንግል የሚባሉ የዐፄ ልብነ ድንግል ወንድም መቋሚያ መያዝ የክርስቶስ መከራ ማሰብ መሆኑን በተደረፉት ቁጥር እንዲወጋቸውና የክርስቶስን መከራውን እንዲያስታውሱ 15 እሾህ የፈሰሰበት መቋሚያ ነበራቸው፡፡ ይህንንም አርአያ በማድረግ በሸዋ ክፍለ ሀገር በወንዝ ከነበሩ መነኮሳት ይሠሩት ነበር እየተባለ ይተረክ ነበር፡፡ የክርስቶስን መከራ በማሰብ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ እንዲድንበት አምነው ስሙን ተአምኖ ብለውታል፡፡
 1. እስራኤል ባሕረ ኤርትራን በየብስ ሲሻገሩ የሙሴ እኅት ማርያም ከበሮ ይዛ ከእስራኤል መካከል በመግባት ታመሰግን ነበር አሁንም በካህናቱ መካከል አንዱ መቋሚያ ሌላው ከበሮ እየመታ ማመስገናቸው ስለዚህ ነው፡፡ የከበሮው ግራና ቀኝ መመታት ግን ለመዝሙር ውበትን ለመስጠት ሆኖ ዋና መልዕክቱ ግን አይሁድ ጌታን በቀራንዮ በቃሪያ ጥፊና በአይበሉባ ግራና ቀኝ አስረው እንደመቱት ለማሰብ ነው፡፡

 1. በቤተክርስቲያናችን እንደሚታየው መዘምራኑ /ካህናቱ በቀኝ እጃቸው ጽናጽል ይይዛሉ፡፡ ይህም በቀድሞው ዘመን ግብፃውያን እግዚአብሔርን  ያመሰግኑበት ነበርና ነው፡፡

ይህም ምሳሌ አለው ላዩ ቀስተ ደመና ይመስላል እንዴት ቢሉ ‹‹ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ፤ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም፡፡››ዘፍ. 9፥11-20 ብሎ ስለአሳየ ነው፡፡ አራት ዘንጎች አሉት የአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ምሳሌዎች ቅጠሎቹ የፍጥረተ ዓለም ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በአራቱ ባሕርያት የተፈጠሩ ሰዎችን፣ እንሰሳትንም አላጠፋም ሲል ለኖኅ ቃል ኪዳን ገብቷልና ካህናትም በጽናጽል ሲያመሰግኑ ኪዳነ ኖኅን አስብና በኃጢአታችን ብዛት አታጥፋን ብለው ማሰባቸው ነው፡፡

ደግሞም ጽናጽል ያዕቆብ በሎዛ ያየው መሰላል አምሳል ነው፡፡ ግራና ቀኝ ያሉትን ዘንጎች ወይም ጋድሞሽ የመውጨ መውረጃው ምልክቶች ናቸው፡፡ በዚህም የተንጠለጠሉት ቅጠሎች ይወጡ ይወርዱ የነበሩት መላእክት አምሳል ናቸው፡፡

ድምፃቸው የምስጋናቸው ድምፅ መታሰቢያ ነው ደግሞም በቀኝና በግራ የቆሙት የብሉያትና የሐዲሳት የሁለቱ ዐበይት ሕግጋት፣ ገጽታዎች የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ የሁለቱ ቃላት በእነዚህ የተንጠለጠሉት በሌሎች ቃላት /መጽሐፍ/ አስረውታል፡፡ በሽብሸባ ጊዜ መቋሚያና ጽናጽል ይዘው ወደ ኋላና ወደ ፊት ወደ ግራና ወደ ቀኝ ማለታቸው መስቀልያ ነውና ማማተብን ያመለክታል፡፡ ማማተብ መጀመሪያ አይደለምን ቢሉ በተናገሩ ቁጥር ማማተብ እንደሚገባ ተወስኖአል ነገር ግን ካህናት በቤተክርቲያን ለማገልገል በቆሙ ጊዜ መቋሚያና ጽናጽል ሲይዙ የክርስቶስን መስቀል መሸከም ማሰብ ይገባቸዋል፡፡ ደግሞም ጌታችን ክብር ይግባውና መስቀሉን ተሸክሞ ሲሄድ አይሁድ ወገቡን በገመድ አስረው ገመዱን በአራት ወገን አትርፈው ወደ ፊት ያሉት ጎትተው ያዳፉታል ይወነጅሉታል የኋለኞቹም ጎትተው ያዳፉታል በቀንም በግራም እየወዘወዙ ያደክሙት ነበር፡፡ ለዚህም መታሰቢያ እንዲሆን የኢትዮጵያ ቤተክስቲያን ካህናት ከወገባቸው ቀሸመራ አስረው ወደ ኋላ ተርፎ ለነበረው ገመድ መታሰቢያ እንዲሆን ቅዱን ወደኋላ ያተርፋሉ ወደ ፊትም ተርፎ ለነበረው ቀሸመሪውን ወደ ፊት ያስተርፋሉ፡፡ ወደ ቀኝና ግራ ተርፎ ለነበረው ገመድ በ2 ወገን ሸማቸውን አትርፈው አንዱን ወገን አትርፈው በጎናቸው በኩል ያተርፉታል፡፡ ከዚህም በኋላ ደፋ ቀና እያሉ  በዜማ ያመሰግናሉ ጌታ ደፋ ቀና ማለቱን ለማሰብ ደፋ ቀና እያሉ ወደ ቀኝና ወደ ግራ መወንጀሉን ደፋ ቀና እያሉ ወዲያና ወዲህ ትዕምርተ መስቀል /ኪዳን/ የሆነ ጽናጽላቸውን ይዘው ለአክሊለ ሾህ መታሰቢያ ምሳሌ የሆነ ጥምጣማቸውን ጠምጥመው ሲያገለግሉ ይታያሉ፡፡ በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ይህን ትተው ለጌጥና ለታይታ የሚያደርጉ ቢኖሩ ከትዕቢት ይቆጠራልና መጠንቀቅ ይሻል፡፡

 1. አሁንም ጌታችን በዕለተ ዓርብ ከሊቆስጠራ እስከ ቀራንዮ ድረስ እጅግ ከባድ መስቀሉን ተሸክሞ ሲጓዝ ከድካሙ የተነሳ መስቀሉን አንዳንድ ጊዜ ከመሬት ያሳርፈው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ካህናትም ይህንን ለማሰብ አንዳንድ ጊዜ መቋሚያቸውን እንደ ማማተብ አድርገው ከትከሻቸው አውርደው በመሬት ያሳርፋሉ፡፡

ደግሞም በዕለተ ዓርብ መድኃኒታችን ከመስቀሉ ክብደት የተነሳ ፈጽሞ በደከመው ጊዜ ያሰብነውን /የፈለግነውን/ ነገር ከአሰብነው ሥፍራ አድርሰን ሳንፈጽምበት ይሞትብናል ብለው መስቀሉን ለስምኦን አሸክመው ባዶውን እያጣደፉ ይነዱት ነበር፡፡ ለዚህም መታሰቢያ ካህናት የጀመሩትን ዜማ በፍጥነት ይናገሩታል መልሰውም ይጀምሩታል ትእምርተ መስቀል የሆነ መቋሚያቸውን ከትከሻቸው ላይ አውርደው ለሌላ ሰው ይሰጡታል፡፡ ቃለ እግዚአብሔሩን /ዜማውንም/ ወዲያና ወዲህ እያሉ እየተመላለሱ በመዘመር በእጃቸው ያጨበጭባሉ ይህም ለደስታም ሆነ ለሀዘን ወይም ለመከራ ምልክት ይሆናል፡፡ ሕዝ. 11፥11-17

ካህናቱ እያጨበጨቡ መዘመራቸው ለምንድን ነው? ቢሉ መድኃኒታችን ባፀኑበት መከራ እጅግ ተገርሞና አዝኖ ወንጌላዊው ቅዱስ ሊቃስ በምዕራፍ 23፥31 እንደገለጸው ‹‹በዘዕፀ ርጡብ ከመዝ ዘገብሩ አፎኑ ይከውን በክብስ›› ማለት በእርጥብ እንጨት /መለኮት በተዋሐደው ሥጋ/ ይህንን ጸዋትወ መከራ ከአበዙ በደረቅ እንጨት /በሩቅ ብእሲ ተራ ሰውማ/ እንዴት ያደርጉበት ይሆን ብሎ እጁን በእጁ እንደመታውና እንደጸፋው ለማሰብ ነው፡፡

 1. መድኃኒታችን የተቀበለውን መከራ ከልብ ተመልክተው የእስራኤል ሴቶች እጅግ አዝነው ያለቅሱ ነበር፡፡ ጌታችን አታልቅሱ ብሎ አፅናናቸው በዚህን ጊዜ ሰሎሜ የምትባል አንዲት ሴት የድካሙን ጽናት የላቡን ብዛት አይታ ለላቡ መጥረጊያ በእጇ ያለውን መሐረብ ሰጠችው፡፡ ጌታችንም በመሐረቡ የፊቱን ላብ በጠረገበት ጊዜ መልኩ በመሐረቡ ላይ ተስሎ ተገኘ ይህም ሁኔታ ለዘለዓለም ለመልኩ መታሰቢያ ሆኖ ይኖራል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ካህናት በአገልግሎታቸው ጊዜ በጣታቸው መሐረብ ይይዛሉ፡፡ ከዚህም ጋር ከላይ እንደገለጽነው መድኃኒታችን መስቀል ተሸክሞ ሲንገላታ እየተከተሉ የሚደረግበትን ግፍ እያዩ ያለቀሱለት ለነበሩ ሴቶች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ምዕመናን ሴቶችም በቤተክርስቲያን ለጌታም ሆነ ለእመቤታችን በዓል እየተገኙ እልል ይላሉ፡፡ ለምን ቢሉ ይህ ቃል በዘመናቸው ለደስታም ሆነ ለሐዘን ያገለግል ስለነበርና በዚያን ጊዜ የነበሩት ሴቶች ያሉት ይህንኑ ቃል ስለሆነ ነው፡፡

አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለሕያው

 እግዚአብሔር ክብር ምስጋና

ይግባው አሜን

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine