ለመሆኑ ባልንጀራነት ምንድን ነው?

ለመሆኑ ባልንጀራነት ምንድን ነው?

ለእባብና ለሔዋን ፡- አንዱ ጉድጓድ ቆፋሪ ሌላው ምስጢር አባካኝ የሚሆኑበት ነው፡፡

ለኢያሱና ለካሌብ ፡- እየተመካከሩ እስከ መጨረሻው የሚጸኑበት፣ ከተስፋይቱ ምድር የሚደርሱበት ነው፡፡

ለሩትና ለኦርፋ ፡- አብረው ቢቆዩም በመጨረሻ ምርጫቸው የተለያዩበት ነው፡፡

ለዳዊትና ለዮናታን ፡- እየተሳሰቡ ቃልኪዳናቸውን በመጠበቅ የሚገልጹት ነው፡፡

ለአምኖንና ለኢዮናዳብ ፡- ክፉ ለመምከር የሚሰበሰቡት የክፉዎች ሸንጎ ነው፡፡

ለኢዮብና ለኤሊሁ ፡- የልባቸውን በመነጋገር ተወቃቅሰው ተማምረው ከጥፋት የሚመለሱበት ት/ቤት ነው፡፡

ለናትናኤልና ለፊሊጰስ ፡- አንዱ ያገኘውን መልካም ነገር ሌላውም እንዲያገኝ የሚተሳሰቡበት አደባባይ ነው፡፡

ለዳክረስና ጥጦስ ፡- በሕይወት ፍፃሜ ላይ የሚወሰን ቁርጥ ውሳኔ በመለያየት የሚደመደም ወዳጅነት ነው፡፡

 

ባልንጀራነት ለእርስዎ ምን ነበር?

አሁንስ ምንድን ነው?

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine