እኛ


=> እኛ ሰው ሰራሽ ሆኖ መአዛ የሌለውን፣ ፍሬ የማያፈራውንና አበባ መሰሉን ሳይሆን፣ እግዚአብሔር የፈጠረውን፣ ያለመለመውንና አብቦ መልካም መኣዘ የተሰጠውን የተፈጥሮ አበባን እንሁን፡፡ ያን ጊዜ ዝንቦች ሳይሆኑ ንቦች ማርን ለማዘጋጀት ይቀስሙናል፡፡ በሃይማኖት ብቻ ያይደለ በምግባር እናብብ፡፡ ያዕ. 2፥14

=> እኛ ለታላላቆቻችን በመታዘዝ አክብሮትን፣ ለእኩዮቻችን በመታዘዝ ፍቅርን፣ ለታላላቆቻችን በመታዘዝ ትሕትናን እናስተምር፡፡

=> እኛ ብርን በመነዘርን ጊዜ ለምንወደው ዘሬ የእኛን ተካፍሎ ነገ ውለታን ለሚመልስ ብቻ ሳይሆን ላጡ ለነጡ ‹‹ለእናንተ ለሚያንሱ›› ለተባለላቸው እንደ እኛ ሲሆኑ አቅመ ደካማ ለሆኑ እናካፍል፡፡ ዋጋችን በሰማይ ይጠብቀናል፡፡ ‹‹ለሚወዷችሁ ይህን ብታደርጉ ምን ብልጫ አላችሁ›› ያለውን ዘወትር እናስብ፡፡ ማቴ. 5፥46

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine