እግዚአብሔርን መፍራት

 •  የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ /ምሳ. 1፥7/
 •  እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ /ምሳ. 8፥13/
 •  እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ /ምሳ. 14፥27/
 •  እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው፤ /ምሳ. 15፥33/
 •  እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል /ምሳ. 19፥23/
 •  እግዚአብሔርን የሚፈራ ከሁሉ ይወጣልና… ፡፡ /መክ. 7፥18/
 •  እግዚአብሔርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ፡፡ /መክ. 12፥13/
 •  እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍጻሜው ያምራል /ሲራ. 1፥13/
 •  የጥበብ ዘውዷ እግዚአብሔርን መፍራት ነው /ሲራ. 1፥18/
 •  እግዚአብሔርን መፍራት አትዘንጋ፡፡ /ሲራ. 1፥27/
 •  እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ለሕጉ ይገዛል /ሲራ. 35፥14/
 •  እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው መከራ አያገኘውም /ሲራ. 36፥1/
 •  እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን /2ኛ ዜና. 19፥7/
 •  እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ /መዝ. 24፥14/
 •  እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ትንንሾችንና ትልልቆችን ይባርካል፡፡ /መዝ. 113፥21/

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine