ብሂለ አበው - 6

  • በሰው እጅ ያልተፈተለና ያልተሸመነ የደጋ ልብሳችን፣ የእርቃናችን መሸፈኛ፣ ጌጥ እና ክብራችን፣ ሊጡ አእምሮ የቦካበት አዲሱ እርሾ፣ አልጫውን ያጣፈጠ ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/

  • በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡

/ቅዱስ አውጉስጢን/

  • ሥጋን በንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለትና እንዲሁ  ነፍሱም በወጣትነት ወራት በደዌ ኃጢአት ትያዛለች፡፡ ትዕቢተኛነት፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት በጾታ መፈላለግንና ይህን በመሳሰሉ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርባታል የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋን ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል፡፡

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

  • ‹‹ሌሊት በህልም ከሴት ጋር የተገናኘህ /ዝሙት የፈጸምህ/ መስሎህ ዘር ቢወርድህ በመዓልት /በቀን/ አታስባት፡፡›› እንዲህ ማድረግህ ደግሞ በህልም የተመለከትከውን በእውን፣ እያሰብከው ደስታ ከማድረግ ይጠብቅሃል፡፡

/ከመጽሐፈ መነኩሳት/

  • ብፅዕት ማርያም፣ በእድሜ ትንሽ በመኖኗ ከሴቶች መካከል ተለይታ ቡርክት ለመሆን አልከለከላትም፡፡

/መጽሐፈ ፊልክስዮስ ክፍል 4 ተሰዕሎ 47/

  • በአፉ ከእግዚአብሔር በልቡ ከዓለም መነጋገሩ ከንጉሱ በፊት ቆሞ ሲነጋገር ዞሮ ከሌላ ቢጫወት ቅጣት እንደሚያገኘው እንዲሁም ልቡን ሳይጠቀልል የሚጸልይ ሰው አምላኩን የሚንቅ እና የሚያቃልል ስለሆነ ቅጣቱ እጅግ ያስፈራል፡፡

/ፍኖተ አእምሮ ገፅ 49/

  • ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡

/ማቴ. 10፥28/

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine