ግጥሞች

ታቦተ ጽዮን

አምላክ ክብሩን ቢገልጽ በታቦቱ አድሮ

እንደማገዶ እንጨት ዳጐንን ሰባብሮ

ክብር ሰጡ ለታቦት አሕዛብ በአንክሮ፡፡

ጽዮንን ከዳጐን ቢያስቀምጧት አብረው

ዳጎንን ወደ ምድር አውርዳ ጣለችው

ጣዖት ከታቦት ጋር ኅብረት ስለሌለው፡፡

ታቦተ ጽዮንን ንቀው ያቃለሉ

አይቆሙም በሕይወት ከምድር ይጠፋሉ፡፡

እንኳን ያቃለሏት ደፍረው ያዩአት ሁሉ

በእባጭ ተመቱ መቃብር ተጣሉ፡፡

ታቦትን ሲያከብር ዳዊትን የናቀች

የእርሱ ሚስት ሜልኮል ንግሥት የነበረች

መካን ሆነች እንጅ መቼ ተጠቀመች

ስለዚህ እናክብር ታቦትን አምነን

የልዑል ማደሪያ ቅዱስ መሆኑን፡፡

                  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

   ምንጭ፡- መዝገበ ታሪክ /ከመምህር ኅሩይ ኤርምያስ/

                  ክፍል 1 ገጽ - 77

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine