ግጥሞች

በአታ ለእግዝእትነ ማርያም

ድንግል ስትገባ ወደ አምላኳ ቤት

ገና ልጅ ነበረች የሦስት ዓመት፡፡

አባት ዘካርያስ ሊቀ ካህናት

ምን ልመግባት ነው እያለ ሲያትት

ሕዝቡም ተሰብስበው ሲመክሩ አንድነት

መልአኩ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት

ሰማያዊ ኅብስት ይዞ መጣላት

ሰማያዊ ጽዋም አቀረበላት፡፡

ድንግል በንጽሕና በመቅደስ ሳለች

ምድራዊውን ምግብ አልተመገበች፡፡

ደግሞም የጐበኟት ወደ መቅደስ ገብተው

ወራዙት አይደሉም መላእክት ናቸው፡፡

                  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

 

  ምንጭ፡- መዝገበ ታሪክ /ከመምህር ኅሩይ ኤርምያስ/

                  ክፍል 1 ገጽ - 86

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine