ግጥሞች

ዝሙትን ፍራው

ዝሙትን ፍራው

ከኃጢአትን ሁሉ ከምትሰራው፤

እሳትን አዝንሟል ዝሙትን ፍራው::

በዳይ ነው ዝሙት በዕውቀትህ ዕወቀው፤

አቅምንም አድክሞ ያረክሳልና ሰው::

የዝሙትን ማጥፋት እይ በመሰረቱ፤

ፊት ጓጉቶ እየሰራ ኋላ በመጥላቱ፡፡

ልቡናህ በዝሙት በምኞት እንዳይጤስ፤

ዘፈንን አትስማ በዓይንህም አትይ ዳንስ፡፡

ለዝሙት ሥራ እንዳትገደድ፤

አባል መዳሰስ እጅህ አይልመድ፡፡

            ምንጭ ፡- ከጣፋጭ ጥበብ

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine