ግጥሞች

እንማጸናለን ገና


በማይፈርስ መሰረት በማይሰነጠቅ ዓለት    

በማይነቃነቅ ግንብ በማይሰበር እንደ ብረት

በዛ በጸና ኪዳኑ ስለኛ በፈሰሰው ደም 

የቆመው የአባታችን ቤት ዛሬም አለ አልወደቀም 

ምኞት የሚወድቅ መስሏቸው ብዙ ድንጋይ ወርውረዋል  

የሚያቃጥሉት ሲመስላቸው እሳት ጭረው ለኩሰዋል

ግን መሰረቱ የጸና ነው የጠፋ ቢመስላቸው                  

እውነት መመንመኗ እንጂ አለመጥፋቷ አልታያቸውም

አባቶቻችን እንዳቆዩት በጽኑ እምነት ተጋድለው                   

ስለ ክርስቶስ ሲሉ መስዋዕት መሆንን መርጠው

እንደነሱ ጽናት ሁሉ እኛም እንጸናለን ገና

ከኛ ጋር አብሮ ያለው ክርስቶስ አምላክ ነውና

የተዋሕዶ በር አይዘጋም ታላቁን መቅደስ አንለቅም

መሰረቱ የጸና ነው የጸና ደግሞ አይወድቅም

                                                 

 

ከሊዲያ

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine