ግጥሞች

አደራ አለብኝ

ብርሃ ይሆናል ስል

ቢውጠኝ ጨለማ

ለምለም መስክ ስፈልግ

ቢገጥመኝ ባድማ

ፍቅር አንድነት ስሻ

መለያየት ሆኖ

ሰላሜን ብቀማ

ለሌላም አይደለም

ቅድስት ተዋህዶ!

ላንቺ ነው ለእማማ

ጴጥሮስ የቁልቁሊት

ለእምነቱ ተሰቅሎ

ደግሞም እስጢፋኖስ

በድንጋይ ተወግሮ

ሳትነዋወጪ እንዳለሽ ጠብቀው

አንቺን ያስረከቡኝ

እኔስ አልተውሽም

አደራ አለብኝ

 

መ/ርት፡- ጸደቀወርቅ አስራት

ምንጭ ፡- ስምዐ ጽድቅ

                                                                  

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine