ግጥሞች

ገባሁ ወደ ገነት

ለሌባ ዋስ የለው

ለቀማኛ ዘመድ

ከጓደኛዬ ጋር

ተቀበልን የሞት ፍርድ

ተገልጾ ሲታየኝ

በደሉና ጽድቁ

የጸጸትን እንባ

ዓይኖቼ አፈለቁ

ለካስ ከሞት አገር

ሕይወትም ይገኛል

የዕድሜ ልክን ኃጢአት

ንስሐ ይጠራል

ዕንባዬን አብሶ

የተስፋ ቃል ሰጠኝ

ዳግም እንዳልጠፋ

በደሙ አተመኝ

ቁልፉን ተረክቤ

ከሕይወት ባለቤት

አዳምን ቀድሜ

ገባሁ ወደ ገነት

                  

ከሙሉነሽ 

 ምንጭ፡-  ሐመር 9ኛ ዓመት ቁጥር 1

       መጋቢት/ሚያዝያ 1993 ዓ.ም

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine