ግጥሞች

ጾም


ቁስለ ነፍስን

የምታደርቅ

ፈቃደ ሥጋን

የምታርቅ

የፈጣሪን

ደጅ መጥኛ

የፈቃዱ መገለጫ

መታመኛ

የሥጋን ፈረስ

መለጎሚያ

የጠላትን ጦር

መቃወሚያ

የንስሐ እኅቷ

የጸሎት እናቷ

የይቅርታ መንገድ

አቁራሪተ መአት

ከብራ ትመጣለች

የንጉሥ አዋጅ

ቀድሷታልና

አንዱ የአብ ልጅ

 

 

ከሱናማዊት    

ምንጭ፡-  ሐመር 9ኛ ዓመት ቁጥር 1

             መጋቢት/ሚያዝያ 1993 ዓ.ም

 

 

 

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine