የጥምቀት በዓል አከባበርና ሃይማኖታዊ ትርጉም

 ክርስትና በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ34 ዓ.ም. ነው፡፡ሐዋ.8፤26-34 ከዚያም በአብረሃና አጽብሃ ዘመነ መንግሥት የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነ፡፡ ለዚህም ከነገሥታቱ ባሻገር አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ጉልህ አስተዋጽኦን አድርገዋል፡፡

ከዚያም በኃላ በ481 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ተሰዓቱ ቅዱሳን የገዳም ሥርዓትን በመመሥረትና ትምህርተ ሃይማኖትን በማስፋፋት ከፍተኛ ሚናን ተጫውተዋል፡፡እነዚህ ቅዱሳን በነበሩበት ዘመን ኢትዮጵያውያኑ ቅዱስ ያሬድና ዐፄ ገብረ መስቀል ቅዱሳኑን ረድተዋል፡፡ ለሃይማኖቱ መስፋፋት የራሳቸውንም እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የቅዱስ ያሬድ የዜማና የመጻሕፍት ድርሰት ነው፡፡

Read more: የጥምቀት በዓል አከባበርና ሃይማኖታዊ ትርጉም

በዓለ ጥምቀት ሥርዓቱና ትውፊታዊ አከባበሩ 2004

በሕሊና በለጠ

     የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ከምታከብራቸው በዓላት መካከል የጥምቀት በዓል ከዋነኞቹ ተርታ የሚመደብና ሥርዓቱና አከባበሩም ለብዙ ዘመናት ብሔራዊ በመሆን የቆየ ነው፡፡ የጥምቀት በዓል አከባበሩ ጥንታዊ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን አይሁድ ከኢአማንያን ወገን የሆነ ሰው ወደ እምነታቸው ሲቀላቀል እንዲገረዝና በውኃ እንዲታጠብ ወይም እንዲጠመቅ ያደርጉ ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳንም አማናዊት ጥምቀት ከመመሥረቷ በፊት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ "እኔስ ለንስሓ በውኃ አጠምቃችኋለሁ ጫማውን እሸከም ዘንድ ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል" ማቴ 3÷11 ብሎ እንደተናገረው ሕዝቡን ለንስሓ በሚሆንና ለአማናዊት ጥምቀት የሚያዘጋጅ ጥምቀት ያጠምቅ ነበር፡፡

Read more: በዓለ ጥምቀት ሥርዓቱና ትውፊታዊ አከባበሩ 2004

የቅድስት ሥላሴ መዝሙራት (ጥር 7) 2004

የቅድስት ሥላሴ መዝሙራት (ጥር 7)

  1. ነአምን በአብ

ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ /2ጊዜ/

ወነአምን /4ጊዜ/ ነአምን በመንፈስ ቅዱስ /2ጊዜ/

 

ትርጉም፡-

እናምናለን በአብ እናምናለን በወልድ /2ጊዜ/

እናምናለን /4ጊዜ/ እናምናለን በመንፈስ ቅዱስ /2ጊዜ/

Read more: የቅድስት ሥላሴ መዝሙራት (ጥር 7) 2004

በዓለ ቅድስት ሥላሴ (ጥር 7) 2004

በዓለ ቅድስት ሥላሴ (ጥር 7)

በሰ//ቤቱ ትምህርት ክፍል

ሥላሴ የሚለው ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦስት ሦስትነት ማለት ሲሆን በያዘው ምሥጢር ግን አንድም ሦስትም /አንድነት ሦስትነት/ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ሦስትነታቸው በስም በአካል በግብር፤ አንድነታቸው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ ነው፡፡

  

  

1.   የሥላሴ ሦስትነት

ሀ. የስም ሦስትነት ፡- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ‹‹እንግዲህ አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ . . .›› ማቴ. 28፥19

      ለ. የአካል ሦስትነት፡- ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አለው፡፡ (ሃይማኖተ አበው) አካል ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለው ነው፡፡ ገጽ ማለት ደግሞ ፊት ነው፡፡ መልክም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለ ነው፡፡ አካልም እንዳላቸው ሲያጠይቅ ነቢዩ ዳዊት ‹‹የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው፡፡›› መዝ. 33፥15 ‹‹እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም›› መዝ. 118፥73 ኢሳይያስም ‹‹እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፡- ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት ›› ብሏል ኢሳ. 66፥1 ለአብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ስር ዘፍ.18፥1-4 ለዮሐንስ በዮርዳኖስ ተገልጸዋል ማቴ. 3፥16-17

      ሐ. የግብር ሦስትነት፡- የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው፡፡ አብ ቢወልድ ቢያሠርጽ እንጅ እንደ ወልድ አይወለድም እንደመንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ ወልድም ቢወለድ እንጂ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ መንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ መንፈስ ቅዱስም ቢሠርጽ እንጅ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ ወልድ አይወለድም፡፡ አብን ወላዲ አሥራጺ ወልድን ተወላዲ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ስላልን የሚበላለጡ አይደሉም አንድ ናቸው፡፡ ጌታ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹እኔ እና አብ አንድ ነን›› ብሏል፡፡ ዮሐ. 10፥30  አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ኢይልህቅ አብ እም ወልዱ ወልድኒ ኢይልህቅ እምመንፈስ ቅዱስ ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢይንዕስ እምወልድ ወወልድኒ ኢይንዕስ እምአቡሁ›› ብሏል፡፡ ይህ ማለት ሦስት አምላክ ማለት አይደለም፡፡ አንድ አምላክ ይባላሉ አንጂ፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም‹‹ወመለኮትሰ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ›› ብሏል፡፡

Read more: በዓለ ቅድስት ሥላሴ (ጥር 7) 2004

ጾመ ገሃድ/ጋድ

© ሕሊና ዘኆኅተብርሃን

ሰሞኑን ብዙ የክታበ ገጽ / ፌስቡክ / ወዳጆቼ የገሃድ ጾምን፣ ልደትንና ጥምቀትን የተመለከቱ የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ጥያቄዎችን በተደጋጋሚጠይቀውኛል፡፡ በክታበ ገጽ ብቻ ሳይሆን በስልክም በአካልም ከብዙዎች ጋር ተወያይተናል፡፡ በየዓመቱ በዚህ ወቅት ተመሳሳይ ጥያቄዎችበተደጋጋሚ የሚነሡ መሆናቸው ልማድ እየሆነም መጥቷል፡፡ ስለሆነም ለብዙ ወዳጆቼ ቃል እንደገባሁት በጉዳዩ ላይ መጻሕፍትን በማገላበጥይህችን ጽሑፍ አዘጋጅቻለሁ፡፡ ( የተጠቀምኋቸውን መጻሕፍት በግርጌ ማስታወሻ ጠቁሜአለሁ፡፡ )

ጥያቄ፡ - የልደት በዓል የገሃድ ጾም አለውን ? ልደት ረቡዕ በመዋሉ ይጾማልን ?

መልስ፡ - እንደሥርዐተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ማንኛውም ክርስቲያን ሊጾማቸውየሚገቡ የአዋጅ አጽዋማት 7 ናቸው፡፡ እነዚህም ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ፍልሰታ፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ገሃድ፣ ጾመ ነነዌእና ጾመ ድኅነት ( የዓርብና ረቡዕ ጾም ) ናቸው፡፡ የገሃድ ጾም ከ 7 ቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው ማለት ነው፡፡

Read more: ጾመ ገሃድ/ጋድ

Page 9 of 20

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine