የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ በሰማዕታቱ ቤት

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ በገባው ቃልኪዳን መሠረት ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2007 ዓ.ም በሊቢያ መስዋዕትነትን የተቀበሉ ወንድሞቻችንን ለማዘከር እንዲሁም ያዘኑ ቤተሰቦቻቸውን ለማጽናናት የቦሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የገርጂ ቅድስ ጊዮርጊስ ፣ የጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፣ የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም በአንድነት በመሆን ከምሽቱ 12 ሰዓት በሰማዕታቱ ቤት በመገኘት የጸሎት የዝማሬ እንዲሁም ጧፍ የማብራት መርሃግብር በማዘጋጀት ሰማዕታቱን አዘክሯል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አሁንም ከሰማዕታቱ በረከት ያሳትፈን ፣ ያዘኑት ቤተሰቦቻቸውንም ያጽናናልን፡፡

የጸሎት መርሃ ግብር በሊቢያ ሰማዕትነትን ለተቀበሉ ወንድሞቻችን

ሰንበት ትምህርት ቤታችን በሊብያ የተሰዉ የቤተክርስቲያናችንን ሰማዕታትን የሚዘክር ልዩ የጸሎት መርሐግብር ሚያዚያ 17 ቀን 2007 ዓ.ም በማዘጋጀት ጸሎተ ምህላ፣ትምህርተ ወንጌል፣ መነባንብ፣ዝማሬ ፣ ሥነ-ጽሁፎች እንዲሁም ሌሎች መርሃግብራትን አከናውኗል፡፡ በእለቱም የደብሩ ካህናት አንዲሁም የአካባቢው ምእመናን በተገኙበት ጧፍ በማብራት ንፁሃን ወንድሞቻችን ሰማዕታቱን አዘክረናል፡፡

Page 6 of 20

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine