የንስሓ መዝሙራት

እንደበደሌማ

እንደበደሌማ ከሆነ ቅጣቴ

አያልቅም ተነግሮ ብዙ ነው ጥፋቴ

እንጃልኝ ፈራሁኝ አዬ ሰውነቴ/2/

      እመለሳለሁ እያልኩ ጠዋት ማታ

      ዘመኔን ጨረስኩ ሳስብ ሳመነታ

      ምን እመልስ ይሆን የተጠራሁ ለታ/2/

በላዬ ሲያንዣብብ ሞት እጁን ዘርግቶ

ስጋዬን ሲውጠው መቃብር ተከፍቶ/

የነፍሴ ማረፊያ ወዴት ይሆን ከቶ/2/

      ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን

      አቤቱ ጌታ ሆይ እኔን ባሪያህን

      ይቅር በለኝና ልየው ፊትህን/2

Read more: የንስሓ መዝሙራት

ምኵራብ

 የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ምራብ ይባላል፡፡ ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት' የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢየሩሳሌም አይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሠሩ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ግን ብዙ ምኩራቦች ነበሩ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡

Read more: ምኵራብ

ምኵራብ

ምኵራብ ማለት ሰቀላ መሰል አዳራሽ ማለት ነው፡፡ አይሁድ ስግደትና መሥዋዕት በኢየሩሳሌም ባለው መቅደስ ብቻ ነው ብለው ቢያምኑም /ዮሐ. 4፥20/ በተበተኑበት ቦታ ምኵራብ ሠርተው ትምህርተ ኦሪትን እየተማሩ ሃይማኖታቸውን ያፀኑ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም በሮማውያን ቅኝ ግዛት ሥር ወደቀችና ጭቆናው ከጊዜ ወደ ጊዜ በተራው ሕዝብ ላይ እየበረታ ሄደ፡፡ በመሆኑም ይህ ጭቆና የኑሮውን ውድነት ከዕለት ወደ ዕለት ያባብሰው ጀመር፤ በዚህ ጊዜ ሁሉም እያንዳንዱ ለራሱ በሚመቸው መልኩ ገንዘብ የሚያገኝበትን መንገድ በመምረጡ ሕዝቡ የማይወጣው ከፍተኛ ጫና ወደቀበት፤ ግማሹ የቄሳርን የሥራ አመራር በመጠጋት በገበያ ይቀርጣል፣ ሌላው የሃይማኖትን ነጻነት ሽፋን በማድረግ ፖለቲከኞችን አሳምኖና ከቀረጥ ነጻ ትሆናላችሁ በማለት ሕዝቡን አባብሎ ገበያውን ወደ ቤተመቅደሱ አንደኛ ግቢ ውስጥና በየምኵራቦቹ ውስጥ እንዲሆን አስወስኖ በቤተመቅደስ ዙሪያ በተለያየ ምክንያት ዘረፋውን ያጧጡፋል፡፡ እንዲህ መሆኑም መንፈሳዊያን ፖለቲከኞችና የጥገኝነት ፖለቲካ አራማጆችን ችግሩ አንድም ቀን ነክቷቸው አያውቅም፡፡ ይህ በመሆኑም የደሀው ኅብረተሰብ ንብረት በካህናት እጅ በተለያየ ስልት ሙልጭ ብሎ ገባ እንጂ ሕዝቡ አሁንም ቢሆን ያወቀው፣ የተረዳው ነገር አልነበረም፡፡

Read more: ምኵራብ

ቅድስት

የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡ ‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህንን የመሰለ የሰንበት ቅድስናን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት 40 ቀን ጌታችን ጾም የሚጀምርበት ሳምንት ስለሆነም  ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡

የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ ዘጸ. 20፥8 ይህንን ቃለ እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሯል፡፡ ዕረፉባት ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ባሕሪ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍሰሐን ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡  በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት/በመማር/' ንስሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል' የተጣላ በማስታረቅ' ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሠረ በመጠየቅ' በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ .25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘለዓለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ. 56፥4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ. 15፥32-36

Read more: ቅድስት

ዐቢይ ጾም

እንኳን ታላቅ በረከትና ጸጋ ለምናገኝበት ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ለጾመው ለዐቢይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ፡፡ በበዓላት እንኳን አደረሳችሁ እንደምንባባለው ሁሉ በጾም መግቢያ ላይም እንኳን ለወርኃ ጾም አደረሳችሁ መባባል ይገባል፡፡ የጾም ወቅት የሚናፍቅ መሆን አለበት ምክንያቱም ጾም ፈቃደ ነፍስ ፈቃደ ሥጋን የምትገዛበት ከልዑል እግዚአብሔር የምንገናኝበት በረከት የምንቀበልበት ልዩ ወቅት ስለሆነ ነው፡፡ከአጽዋማት ሁሉ ታላቅ መሆኑን ስሙም ጭምር የሚጠቁመው ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከተጠመቀ በኋላ በገዳም ገብቶ 40 ቀንና 40 ሌሊት የጾመው ጾም ሲሆን በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፡፡ ማቴ. ፬ ከቁጥር ፩ ጀምሮ፡፡

Read more: ዐቢይ ጾም

Page 4 of 20

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine