9ኛ ዓመት

እንኳን ለ9ኛ ዓመት የሰንበት ትምህርት ቤታችን የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

እነሆ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ይህን ታሪካዊ ቀን ሲያከብር በዚች ዕለት የተቀበላትን የቤተክርስቲያን ኃላፊነት በመዘከርና ወደ ፊቱም ከሰ/ት/ቤቱ ሆነ ከምእመናንና ከሌሎች ሰ/ት/ቤቶች ጭምር ምን እንደሚጠበቅባቸው በማስገንዘብ ጭምር ነው፡፡ ይህን የሰ/ት/ቤቱን እና የቤተክርስቲያኒቱን ልደት ስናከብር ይህ በዓል የሰ/ት/ቤቱ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ጭምር መሆኑን በማስታወስ ነው ዛሬ በዚች ቦታ ለማክበር ወዳችሁ ሽታችሁ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ከሰ/ት/ቤቱ በአካል ርቃችሁ የምትገኙ የሰ/ት/ቤቱ አባላት እና ይህ መልእክት የሚደርሳችሁ ምእመናን በሙሉ በተጨማሪም በሥራ ምክንያት ከአገር ወጥታችሁ በተለያዩ አገሮች የምትኖሩ፣ በዩኒቨርስቲና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ተበታትናችሁ ያላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች በሙሉ እንኳን ለሰ/ት/ቤቱ የዘጠነኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አደረሳችሁ፡፡

ይህች ታሪካዊ ቀን ለሰ/ት/ቤቱም ልጆች ሆነ ለአንባቢው ምዕመን ልዩ ቀን ናት እንደ እግዚአብሔር ቸርነትና እንደ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በተለያየ ስፍራ የምንገኝ ልጆቿን ስብስባ አንድ አድርጋ በመንፈሳዊ ሕይወት እንድንታነፅ በምግባር እንድንበለፅግ የተጠራንበት ዕለት ናት፡፡ ብዙዎቻችን በዚች እቤት እንድንኖርባት እና የነገዋን ቤተክርስቲያን ተረካቢዎች እንድንሆን አደራ የተቀበልንባት ቀን ብትኖር ይህች ዕለት ናት፡፡ ዛሬ እኛ የተቀበልነው ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን አደራም ጭምር ነው፡፡ ይህ አደራ ደግሞ ሰማያዊ አደራ ብቻ ሳይሆን ምድራዊ አደራ ጭምርም ነው፡፡ ዛሬ ከኛ ቤተክርስቲያን አለሁልሽ የሚላት በምግባሩና በሕይወቱ የሚመሰክርላትን ልጆች ትሻለች፤ ዛሬ ቤተክርስቲያን እሳቱን የሚያበርድላት ልጆችን  ትፈልጋለች፤ዛሬ ቤተክርስቲያን በሥነ ምግባር የታነፀ በሃይማኖት በመንፈሳዊ እውቀት የበለፀገ ክርስቲያን ትፈልጋለች፡፡ ለዚህ ሁሉ ሀላፊዎች ደግሞ አደራው የተሰጠው ለቅርብ ተጠሪዎች ለሰ/ት/ቤት ወጣቶችና እና በአገልግሎት ላይ ያሉ መሰል ሰ/ት/ቤቶች ጭምር ነው፡፡ ይህ አደራ ደግሞ በውስጧ ላለን ልጆቿ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ምዕመናንም ጭምር ነው፡፡ ስለሆነም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላችሁ የሰ/ት/ቤቶችን ምዕመናን በሙሉ በተሰጠን ጸጋ እግዚአብሔርን እንድናገለግለው ቤተክርስቲያናችን ተስፋፍታ ምዕመኖች ሁሉ የክርስቶስን ሥጋና ደም ተቀባዮች እንዲሆኑ ወንጌል ያልደረሰባቸው ሀገራት ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል እንዲደርሳቸው ሁላችንም ሃላፊነታችንን አንድንወጣ ሰ/ት/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ሰንበት ት/ቤቱ ራዕይም ነገ የቤተክርስቲያን ልጆች የቅድስት ቤተክርስቲያንን እምነት ሥርዓት ሀብት ለመጪው ትውልድ የሚያስረክብ በሃይማኖት በምግባር የታነፀ በዓላማዊና በመንፈሳዊ እውቀት የበሰሉ ክርስቲያን ሲኖር ማየት ነውና ራዕይዋ ጎኖ በመሆን ራዕዩን እንድናሳካ የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ጸጋና በረከት አይለየን፡፡ አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine