ዘመነ አስተርእዮ - የሰንበት ትምህርት ቤቱ መልእክት

St. Maryበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቀን ቀመር መሠረት ከታህሳስ 29 ጀምሮ ያለውን ወቅት ዘመነ አስተርዮ ይባላል፡፡ የመገለጥ ዘመን እንደማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ ኃጢአት በመስራቱ ምክንያት እግዚአብሔርን የመሰለ ጌታ ገነትን ያህል ቦታ አጥቶ ነበር፡፡ ይህ ብቻ አልነበረም አዳም በኃጢአቱ ምክንያት ጸጋው ተገፏል ባሕሪውም ጎስቁሏል ለ7 ዓመት በግልጥ ሲሰማ የነበረውን የአምላኩን ድምፅ እንኳ በኃጢአት ምክንያት መስማት ፈርቶ ‹‹በገነት ድምፅ ሰማሁ ዕራቁቴንም  ስለሆንኩ ፈራሁ ተሸሸግሁም›› ዘፍ. 3፥1 እንዳለ ታዲያ ይህ ያለንበት ወቅት እርቅ የተጀመረበት' ሰው እና መላእክት በአንድ ቋንቋ የዘመሩበት' የእዳ ደብዳቤ የተደመሰሰበት' የሦስትነትን የአንድነትን ምሥጢር በግልጥ የታወቀበት' የነቢያት ትንቢታቸው ተስፋቸው የተፈጸመበት ወቅት ስለሆነ ቤተክርስቲያናችን የመገለጥ ዘመን ትለዋለች፡፡

በዚህ ዘመን ብሉይን ወደ ሐዲስ ዘመነ ፍዳውን ወደ ዘመነ ምሕረት የሚቀይር አንድ ጌታ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በኅቱም ድንግልና ያለ አባት በፍጹም ትሕትና ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነሳ፡፡ ዘመን የማይቆጠርለት የዘመናት ጌታ እንዲቆጠርለት የማይወሰነው ጌታ ይጨበጥ ይዳሰስ ዘንድ ግድ ሆነ ግድ እንዲሆን ያደረገው እውነተኛ አምላክ ለሰው ልጅ የነበረው ፍቅር ነው፡፡ ‹‹እንዲሁ ወደድኳችሁ›› እንዳለ ‹‹ፍቅር ስሃቦ ለወልድ እመንበሩ›› ብሎ ሊቁ እንደተናገረው በፍጹም ካሳ ከፋይነት ያ ቃል እግዚአብሔር የነበረ ‹‹ቃል ሥጋ ሆነ፤ ጸጋና መንፈስን ተሞልቶ በኛ አደረ›› ዮሐ. 1፥14 ይህንን እውነተኛ ጌታ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዓለም ከስጦታዎች ሁሉ በላይ  የሆነውን ሕፃን አበረከተች፡፡ ‹‹ድንግሊቱ ሔዋን የእባብን ቃል ሰምታ አለመታዘዝንና ሞትን ፀነሰች ወንድሙን የሚገድለውን የሞትን ልጅ ገዳይ ቃየልን ወለደች ድንግል ማርያም ግን የብርሃናዊውን መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን ቃል ብስራት ሰምታ ታዛዥ ሆነችና ሕይወት ክርስቶስን ፀነሰች ለሕዝብም የሚሞተውን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወለደች ›› ሰማዕቱ ቅዱስ ዮስጢኖስ እንደተናገረው እውነተኛ የሕይወት መብልን ክርስቶስን ወለደችልን የመጀመሪያይቱ የማክሰኞ ምድር ያለምንም ዘር ለሥጋ የሚሆነውን አዝዕርቱን እፅዋቱን ፍራፍሬውን ስትሰጥ አማናዊት የሆነች የማክሰኖ ምድር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ያለ ወንድ ዘር የሥጋንም የነፍስንም ምግብ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ወለደች፡፡ ‹‹ለዚህ ድንቅ ነገር ምሥጢር አንክሮ ይገባል ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው›› ሃይማኖተ አበው ይህ ያለንበት ወቅት የፍቅር መጀመሪያው የጥል ግርግዳ የመፍረሻው ዋዜማ ነበር፡፡ ለዚህ ነው መገለጥ የሚባለው እውነተኛ ፍቅር የተገለጠበት ስለሆነ በብሉይ ተሰውሮ የነበረው የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር ተገልጧል፡፡ ይህም በባሕረ ዮርዳኖስ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው በማዕከለ ዮርዳኖስ በመለኮት የእዳ ደብዳቤውን ሲፍቅልን ከሰማይ አባት አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው እሱን ስሙት ሲል መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ሲያርፍ ይህ ድንቅ ምሥጢር በድንቅ ስለታየ ዘመነ አስተርዮ ተብሏል፡፡ እንግዲህ የልደትም ሆነ የጥምቀት በዓል በተለይ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ለየት ያለ እይታ አለው ለምን ቢሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ባሕላዊ የአከባበር ወጉ ጥልቅና ከልብ የማይጠፋ ትውስታ ያለው ነው፡፡ ‹‹ፍቅር እግዚአብሔር ነው፡፡›› 1ዮሐ. 4፥8 ይህ ፍቅር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ባገኘንበት በዚህ ወቅት በዓሉን በመተሳሰብና በመረዳዳት በእውነተኛ ፍቅር ልናከብር ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ‹‹በዓላችሁን ጠላሁት›› አሞ. 5፥21 ብሎ እንደወቀሰን እንደተናገረን የኛም በዓል አከባበር እግዚአብሔርን እንዳያስቀይም ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

ወሩ ወርሃ ጥር ሲሆን ለዚች ለቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤታችን እግዚአብሔር የተገለጠበት ወቅት ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም፡፡ ምክንያቱም በተለያየ ኃጢአት ሥራ ላይ የነበሩትን ይሰበስብ ዘንድ ምንም ባልነበረበት ቦታ ልጆቼ ብሎ ይጠራን ዘንዳ እግዚአብሔር ወደደና የዛሬ 7 ዓመት ጥር 23/ 1996 ዓ.ም ሰንበት ትምህርት ቤታችን በአባቶች ቡራኬ በሜዳ ላይ ተመሠረተ፡፡ እግዚአብሔር ሲገለጥ በአማረና በተዋበ ቦታ አልነበረም ይልቁንም በማይመቸው በከብቶች በረት ውስጥ ተገለጠ ለዚች ቤትም ሲገለጥ ፀሐይና ዝናብ መከለያ በሌለው በዛ ሽታው በከረፋ በአውላላ ሜዳ ላይ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በተለይ በአካባቢው ለምንኖር ምዕመናን በግልጥ ፍቅሩን ያየንበት ዕለት ነበረች፡፡ ዛሬ ሰንበት ትምህርት ቤቱ እግዚአብሔርን ኃይል አድርጎ እመብርሃንን አማላጅ አድርጎ ለቤተክርስቲያንና ለሀገር የሚጠቅም ሥራ ለመሥራት ትልቅ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ አሁን ሰንበት ትምህርት ቤቱ ጊዜያዊ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲኖረው የተለያዩ በዓላት ማክበሪያ ይሆን ዘንድ የአገልግሎት ልብስ አሰፍቶ አገልግሎቱን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት እየሞከረ ይገኛል በተለይም ዳግም ቤተክርስቲያንን ወደ ፊት ለማራመድ ይረዳ ዘንድ የአምስት ዓመት ስልታዊ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በነዚህም ጊዜያት ወጥ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት ከሕፃናት እስከ ወጣቶች በመንደፍ ማስተማር የቻለ ሲሆን በየጊዜው ለሚነሱ አጽራረ ቤተክርስቲያን ምላሽ የሚሰጡ መርሃግብርችን በማዘጋጀት የአካባቢ ልጆች በመንፈሳዊም በዘመናዊም የበሰሉ ይኖኑ ዘንድ በክረምት ከ5- 10 ክፍል ዘመናዊ ትምህርት በማስተማር ከሙስና የነፃ ትውልድ ለማፍራት ጥረት ያደርጋል 3 ዲያቆናትን 2 መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው የሚማሩ አባላትን በማፍራት አሁንም ሌሎችን ለማዘጋቸት የአብነት ትምህርትን በማቋቋም በተጨማሪም ከ15 ያላነሱ  ሰ/ት/ቤቱንና በአጥቢያ ያሉትን ግቢ ጉባኤያት ሊያስተምሩ የሚችሉ ተተኪ መምህራን በማፍራት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ድረ ገጽም የዚሁ አንድ ውጤት ነው፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር ለሰ/ቤታችን የተገለጠበት ወቅት ነው ያልነው ስለዚህ ሰ/ት/ቤቱ የተመሠረተበትን 7ኛ ዓመት ጥር 28 በዓውደ ምሕረት በ29 ደግሞ በአዳራሽ ብፁዓን አባቶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በብዙ ተጋድሎና በብዙ ፈተና ዘሬ እኛ እንድንማር የበኩላችሁን የተወጣችሁ ታላላቅ ወንድሞችና እህቶች ሁላችሁንም በያላችሁበት እመብርሃን ጸጋ በረከቱን ታድል እንላለን፡፡ ከአሁን በኋላ የተሻለ ሥራ መሥራት እንችል ዘንድ በተለይም ደግሞ ዛሬ ቤተክርስቲያንን ከፈተና ሕዝቡንም ከክፉ ነገሮች እንታደግ ዘንድ ሰ/ት/ቤቱ ለሁሉም ወጣቶች ኑ ቃለ እግዚአብሔርን በማሰማት እራሳችንንና ወገኖቻችንን እናድን ይላል፡፡ በመጨረሻም በየውጭ ሀገርና በየክፍለ ሀገር ላላችሁ አባሎቻችንና ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ እንኳን ለልደት' ለጥምቀት' ለቃና ዘገሊላ' አስተርዮ ማርያም እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤታችን 7ኛ ዓመት አደረሳችሁ እንላለን እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ ቤተክርስቲያናችንን ከፈተና ከመከራ ይሰውርልን፡፡

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine