ጸሎት /ለሕፃናት/

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ዛሬ ስለ ጸሎት ምንነት እን አደራረግ ዝግጅቱን በተመለከተ ትማራላችሁ፡፡ በደንብ ተከተሉኝ እሺ፡፡

ጸሎት “ጸለየ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ የቃሉ ፍችም አመሰገነ፣ ለመነ፣ ዘመረ ማለት ሲሆን ጸሎት ማለት ልመና ፣ ምስጋና ፣ ዝማሬ ይኸውም ከአምላክ ጋር መነጋገር ማለት ነው፡፡

ጸሎት የሚቀርበው ለእግዚአብሔር/ወደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ጌታችንም ”ለምኑ ይሰጣችኋል ፈልጉ ታገኛላችሁ ደጅ ምቱ ይከፈትላችኋል” ማቴ. 7፥7 በማለት መጸለይ እንደሚገባን አስተምሮናል፡፡

ጸሎት ጥቅም

ጸሎት ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ ለዚህ ትምህርት እንዲሁኑ ጥቂቶቹን እንደሚከተለው እንመለከታለን።-

-    እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቅመናል፡፡

-    በጸሎት በደላችንን ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር እንናዘዛለን(እንናገራለን) ይቅርታውንም እንለምናለን፡፡

-    ከእግዚአብሔር ዘንድ የፈለግነውንና የጎደለንን ለማግኘት ያስችለናል፡፡

-    መንፈሳዊ ኃይል እንድናገኝ ያስችለናል፡፡

እንግዲህ ጸሎት ይህን ያህል ጥቅም እንዳሉት ከተረዳን እንዴት መጸለይ እንደሚገባን እንደሚከተለው እንማማራለን፡፡

ጸሎት እደራረግ ሥርዓትና ዝግጅት

ልጆችዬ ጸሎት በቤተክርስቲያን በዘፈቀደ የሚከናወን ሳይሆን ራሱን የቻለ ሥርዓት ያለው ነው፡፡ ይህም ከመጸለያችን በፊት በቂ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ማድረግ የሚገባንን ዝግጅት ለመረዳት ያስችለን ዘንድ በሁለት ወገን ከፍለን እንመለከተዋለን፡፡ ከእነዚህም አንዱ ውጫዊ /አፍአዊ ዝግጅት/ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ ዝግጅት ነው፡፡ በዛሬው ትምህርታችን ውጫዊ /አፍአዊ ዝግጅቶች/ ውስጥ የሚጠቃለሉትና ማድረግ የሚገባንን እንመለከታለን፡፡

Read more: ጸሎት /ለሕፃናት/

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን /ለሕፃናት/

በፍሬሕይወት ጸጋዬ ዘኆኅተ ብርሃን

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን /ለሕፃናት/

ልጆችዬ እንደምን ሰነበታችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን አላችሁ ጐበዞች ልጆችዬ ዛሬ በቤተክርስቲያን ሊኖረን ስለሚገባ ሥርዓት እጽፍላችኋለሁ በማስተዋል ተከታተሉኝ እሺ፡፡

ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት ነች ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ ስለዋጃትም ቅድስት ነች፡፡ ስለዚህ ልዩና የክብር ቦታ ናት፡፡ ልጆች እኛም ልናከብራት ይገባል፡፡

በቤተክርስቲያን ካህናትንም ልናከብር ይገባል፡፡ ምክንያቱም ክብር የሚገባትን የእግዚአብሔርን ቤት አገልጋዮች ስለሆኑ ማለት ነው፡፡

ልጆችዬ እግዚአብሔር በቤተመቅደሱ አለ በቅዳሴ ሰዓትም ቅዱሳንና መላእክት ከእኛ ጋር ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ ዝግጅታችን ምን መምሰል አለበት? በቤተመቅደስ ውስጥም ምን እንድናደርግ ይጠበቅብናል? የሚሉትን ነጥቦች በቅደም ተከተለ እንደሚከተለው እናያለን፡፡

Read more: ሥርዓተ ቤተክርስቲያን /ለሕፃናት/

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine