ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን

ኆኅተ ብርሃን ማለት የብርሃን መውጫ ማለት ነው፡፡የቦ/ኆ/ቅ/ማ ቤ/ክን የተመሠረተችው ታህሳስ 16 ቀን 1996 ዓ.ም ነው፡፡በጊዜው የነበሩት ዲያቆናት፣ካህናትና የአካባቢው ምዕመናን ቤተክርስቲያኗን ለማቆም ያዩት ፈተና ከባድ ነበር፡፡አካባቢው በመናፍቃን የተከበበ በመሆኑ ቦታው መዋዕለ ንዋይን ለማፍሰስ ወይም ለዘመናዊ ኢንቨስትመንት የተመቸ በመሆኑ ቤተክርስቲያኗን ለማቋቋም በመንፈስ ቅድስ አነሳሽነት ለታጠቁት ሰዎች ሁኔታው ከባድ ነበር፡፡ሆኖም መድሀኔዓለም የዐለም መድሃኒት የሆነው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ይህችን ቦታ በእናቱ በቅድስተ ቅዱሳን፣በንፅህተ ንፁሃን በድንግል ማርያም መታሰቢያነት ቤቱን ሊሰራባት አዝዟልና ክርስቶስን ሀይል አድርገው ለተነሱት ሁሉ ምድራዊ ፈተና ሊያቆማቸው አልቻለም፡፡በመሆኑም ቀኑን የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው፣ሌሊቱን ድምፅ ሳያሰሙ ቆርቆሮን በሽቦ እየበሱ አስረው፣በፖሊስ ተከበው፣በእስር ቤት ሰንብተውና ሌሎች ፈተናዎችን በፅናት ተጎንጭተው በትንሽ መቃኞ ያቆሟት የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክን ዛሬ የወደፊት ህንጻዋ የመሰረት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ህንጻው እስኪጠናቀቅ ድረስ በቤተክርስቲያኗ የሚገኙት የእመቤታችን የቅ/ድ/ማርያምና የቅድስት ሥላሴ ታቦት የሚገኙት በጊዜያዊነት ከተሠራው ቆርቆሮ በቆርቆሮ በሆነ መጠነኛ ህንፃ ቤ/ክን ውስጥ ነው፡፡

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine