ኆኅተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ወደ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ጉዞ አዘጋጀች

በወለተ ትንሣኤ

‹‹መልካም ሥራ የክፉ ቀን ስንቅ ነው ››

በሰባተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት (ኒቆዲሞስ) የኆኀተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና የአካባቢው ምዕመናን  በሰንበት ትምህርት ቤቱ በጎ አድራጎት ክፍል አስተባባሪነት  እሑድ መጋቢት 20 ቀን ፣ 2007 ዓ.ም. በሕመም የተጎዱ ወገኖችን የመጠየቅ መርሐ ግብር ተከናውኗል ፡፡

Read more: ኆኅተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ወደ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ጉዞ አዘጋጀች

ስልታዊ ዕቅድን አስመረቀ

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ለ5 ዓመት (ከ2005ዓ.ም - 2009ዓ.ም) የሚሆን ስልታዊ ዕቅድን አባቶች ካህናት ፣ መምህራን እንዲሁም ከተለያየ ሰንበት ትምህርት ቤት የተጋበዙ አባላት በተገኙበት በደመቀ ስነስርዓት ታህሳስ 21 ቀን 2005 ዓ.ም በይፋ አስመረቀ፡፡    

መስከረም 1 እንቁጣጣሽ

መስከረም 1 እንቁጣጣሽ ቀን ምዕመኑ በመለገስ የሚያመጣውን የበግ፣ የፍየል እና የበሬ ቀዳ የደብሩ ካህናት እና የሰ/ት/ቤቱ አባላት በመተባበር መሰብሰባቸው ተገለጸ፡፡፡

የኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያናችን ሕንጻ መሰራት ከጀመረ የሰነባበተ ሲሆን በምዕመኑ ሐሳብ ለሕንጻ ማሰሪያ በበዓላት ሲሰበሰብ የነበረው የበግ የፍየል እና የበሬ ቆዳዎች በአለንበት በ2005 እንቁጣጣሽ ላይ እንዲሁ በካህናት እና በሰንበት ተማሪዎች አባላት ሲሰበሰብ እንደነበር ዘና ክፍላችን ገልጾልናል፡፡

በዘንድሮው ዓመት የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት የወሰዱ የሰ/ት/ቤት አባላት ሁሉም ደረጃቸው ጥሩ ውጤት እንዳመጡ ተገለጸ

በዘንድሮው ዓመት የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት የወሰዱ የሰ/ት/ቤት አባላት ሁሉም ደረጃቸው ጥሩ ውጤት እንዳመጡ ተገለጸ፡፡

    በዘንድሮው ዓመት የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ የሰ/ት/ቤታችን አባላት ሁሉም በደረጃቸው ጥሩ ውጤት እንዳመጡ ተገለጸ፡፡የብሔራዊ ፈተናን ከወሰዱት ተማሪዎች 90 ከመቶ የሚሆኑት አጥጋቢ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ያልሆኑት ተማሪዎችም ለትምህርት የሚሰጡት ትኩረት የሚያረካ መሆኑን የሰ/ት/ቤቱ የነጻ ሞያ አገልግሎት ዋና ክፍል ጠቁሙአል፤

      የሰንበት ትምህርት ቤታችን ነጻ ሞያ አገልግሎት ክፍል እንደገለጸው ሰ/ት/ቤቱ ባቀደው የረጅም ጊዜ ስልታዊ ዕቅድ መሠረት በመንፈሳዊና በዘመናዊ ትምህርት የበሰሉ አባላትን ማፍራት የሚለው የሰ/ት/ቤቱ ራዕይ ዋና ሐረግ በመሆኑ፤ ባለፉት ዓመታት እንደተለመደው በቀጣዩም ዓመት ከዚህ የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ተማሪዎቹ በርትተው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ተያያዥ ገጾች

Joomla templates by Joomlashine