መስከረም 26 ጽንሰቱ ለዮሐንስ መጥምቅ

Normal 0 false false false EN-US X-NONE X-NONE /* Style Definitions */ table.MsoNormalTable {mso-style-name:"Table Normal"; mso-tstyle-rowband-size:0; mso-tstyle-colband-size:0; mso-style-noshow:yes; mso-style-priority:99; mso-style-qformat:yes; mso-style-parent:""; mso-padding-alt:0in 5.4pt 0in 5.4pt; mso-para-margin-top:0in; mso-para-margin-right:0in; mso-para-margin-bottom:10.0pt; mso-para-margin-left:0in; line-height:115%; mso-pagination:widow-orphan; font-size:11.0pt; font-family:"Calibri","sans-serif"; mso-ascii-font-family:Calibri; mso-ascii-theme-font:minor-latin; mso-fareast-font-family:"Times New Roman"; mso-fareast-theme-font:minor-fareast; mso-hansi-font-family:Calibri; mso-hansi-theme-font:minor-latin;}

           አባቱ ዘካርያስ እናቱ ኤልሳቤጥ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው ብዙ ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ገብርኤል ጸሎትህ ተሰምቶልሀል አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወለዳለህች ስሙን ዮሐንስ ትለዋለህ ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፣ የወይን ጠጅም አይጠጣም በጌታም ፊት ታላቅ ይሆናል አለው፡፡ አሁንም እኔም ልምላሜ ሙቀት ተለይቶኛል ሚስቴም ልማደ አንስት አልፎባታል ይህ የምትለው እንደምን ይሆንልኛል? አለው፡፡ አኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፡፡ ይህ የነገርኩህን አላመንክምና እስኪፈጸም ደረስ ድዳ ትሆናለህ ብሎት ዐረገ፡፡ እንዳለውም በዚህ ዕለት ዮሐንስ ተጸንሷል፡፡ ሉቃ 1፣15፣25   

                                                                                          ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መስከረም 21፡ ብዙኃነ ማርያም

በደሳለኝ አላምሬ ዘኆኅተ ብርሃን

 

       ይህ በዓል መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው የአርዮስ የምነፍቅና ትምህርት የእስክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ እለእሰስክንድሮስ አውግዞት በዚህ ምክንያት በጉባኤ እንዲደረግ የሮሙ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነቂያ ጉባኤ ይሁን ብሎ አዋጅ አስነግሮ በዚህ ዕለት ሃይማኖት ዶግማ አስቀምጠውልናል ፡፡

      ሁለተኛው መስቀልን ይመለከታል፡፡ ዐፄ ዳዊት ከግብጽ ጌታችን የተሰቀለበት ቀኝ እጁ ያረፈበት ዕፀ መስቀል የገባበትና ኢትዮጵያን እየዞረ ከባረከ በኃላ ዐፄ ዘርዕ ያዕቆብ በታዘዙት መሠረት ማለትም ‹‹መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ›› በዚህ ትእዛዝ መሠረት ግሸን ደብረ ከርቤ አስምጠውታል፡፡ ይህን በማስመልከት ከመስቀሉ በረከት ረድኤት ከቃል ኪዳኑ ተካፋይ ለመሆን መስከረም 21 ቀን ወደ ግሸን ጉዞ ደደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine