ሐምሌ 19 - ቅዱስ ገብርኤል

ይህች ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣን እና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ቀን የሚታሰብበት ነው፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፡፡

ዘመነ ሰማዕታት አምልኮተ ጣዖት በተስፋፋበት፣ አምልኮተ እግዚአብሔር በጠፋበት ዘመን መምለኬ ጣዖት የነበረ የሀገሩ ገዥ እለ እስክንድሮስ በክርስቲያኖች ላይ ስደትን ስላወጀ፣ ቅድስት ኢየሉጣ የሦስት ዓመት ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ወደ ሌላ ሀገር ተሰደደች፡፡ ጌታ በወንጌል ‹‹በአንዲቱ ከተማ መከራ ሲያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ›› (ማቴ. 0፡፳3) ያለውን በማሰብ ተሰዳ ሳለች፣ የአላዊው መኰንን ወታደሮች ተከታትለው ደርሰው ለጣዖት ስገጂ ፈጣሪሽን ካጂ ቢሏት፣ የዚህን ምሥጢር የሚያውቅ የሦስት ዓመት ሕፃን አለ፤ እሱን ጠይቁት አለቻቸው፡፡

 ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› (መዝ. ፻፴305)፡፡ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ፈራች፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው፡፡ ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን ‹‹እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ›› አላት፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም ‹‹ልጄ የነፍስ አባት

Read more: ሐምሌ 19 - ቅዱስ ገብርኤል

ጴጥሮስ ወጳውሎስ (ሐምሌ 5


 ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ

ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19

ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣን ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ አንተ እንድመጣ አሰናብተኝ ብሎ በባሕር ላይ ሲሄድ በመሞከሩ ማቴ. 6፥45፣ ፈጣንነቱ ጌታ ደቀመዛሙርቱን በቂሣርያ ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ጠይቋቸው ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ፈጥኖ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ  ክርስቶስ ነህ ብሎ በመመለሱ ማቴ. 16፥16 ቁጡነቱም አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቶጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ በመቁረጡ ዮሐ. 18፥10 ላይ ያስረዳል፡፡ መዋዕለ ስብከቱ 50 ዓመት ነው፡፡ /ገድ ሐዋ፣ ዜና ሐዋ/

Read more: ጴጥሮስ ወጳውሎስ (ሐምሌ 5

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine