ሕንጸተ ቤታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም

እመቤታችን በዐረገች በ4ዓመት ጳውሎስና በርናባስ ፊልጵስዩስ ገብተው አስተማሩ፤ ሕዝቡም አምነው ተጠመቁ እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሒዱ አሏቸው የለመድነውን ከከለከላችሁንማ መካነ ጸሎት ስጡን አሏቸው፡፡ እንዲህ ብንላቸው እንዲህ አሉን ብለው ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስ ላኩ አልቦ ‹‹ዘትገብሩ ወኢምንተኒ ዘእንበለ ትእዛዙ ወምክሩ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ›› ያለጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባም እናንተም ጸልዩ እኛም እንጸልያለን ብለው ላኩባቸው፡፡ ሱባዔ ሲጨርሱ በዚህ ዕለት ጌታ በሩቅም በቅርብም ያሉ ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ዮሐንስ ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን ብሎ ጠየቀ ጌታም በእናቴ ስም ጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው አለው፡፡

 

Read more: ሕንጸተ ቤታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል

መላእክት የሚለው ቃል መልእክተኞች' ተላላኪዎች' የእግዚአብሔር ይቅርታ ወደ ሰው የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ' የእግዚአብሔር ልዩ ወዳጆች ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ አለቆች ገዥዎች ወይም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ማለት ይሆናል፡፡

ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ እግዚአብሔር' እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?›› ማለት ነው፡፡ ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል /ዳን.10፥13' 2፥1/ ውስጥ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክም ለበርካታ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ሌላ በብሉይ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍት በኪዳነ አብርሃም ውስጥ ተጠቅሶም ይገኛል፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› /ዳን.12፥1/ በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› /ዳን. 10፥13/ በማለት ያስረዳል፡፡ በዚህ ቃል ላይ ከዋንኞቹ አለቆች አንዱ የሚለውን በመያዝ ሚካኤል ብቻ የመላእክት አለቃ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን የሌሎች አለቅነት የተወሰነ ወይም ዝቅተኛ ሲሆን በአንድ ነገድ ላይ በአንድ የመላእክት ከተማ ላይ ነው፡፡ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት ግን በመላእክት ሁሉ ላይ ከሆነ ከሌሎቹ ይለያል፡፡ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ እንደተገለጸው ሰባት ሊቃነ መላእክት ቢኖሩም አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

Read more: ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine