ትንሣኤ

    ‹‹ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም፡፡›› /ሉቃ. ፳45/

 

  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ልበ አምላክ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹እግዚአብሔር ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ተነሣ›› ብሎ እንደተናገረው በኃይሉና በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፡፡ የጌታችን ትንሣኤ ለክርስቲያኖች ታላቅ ክብራችን ነው እኛን ወዶ ስለኛ ሞትን ድል በመንሳት ለኛ አርአያ ሆኗል፡፡

 

Tensae

      በሳምንቱ መጀመሪያ መግደላዊት ማርያም ሽቱ ይዛ ወደ ጌታዋ መቃብር ስትሄድ ድንጋዩ ተፈንቅሎ አየችው እየሮጠችም ለሐዋርያት ማኅበር ተናገረች እነ ጴጥሮስም ወደ መቃብሩ መጥተው ተመለከቱ ነገር ግን ገና የመጽሐፉን ቃል አላወቁም ነበርና ተመልሰው ወደ ቤታቸው ሄዱ፡፡ ማርያም ግን በውጭ ቆማ የጌታዬን ሥጋ ወሰዱት ብላ ታለቅስ ነበር፡፡ ጌታም አጥብቃ  እንደፈለገችው ተመልክቶ ትንሣኤውን ከሁሉ መጀመሪያ ገለጸላት እርሷ ግን አትክልት ጠባቂ መስሏት ነበር፡፡ በስሟ ሲጠራት ግን ጌታዋ መሆኑን አወቀች እርሱ ግን አላመንሽኝምና አትንኪኝ አላት ነገር ግን ሄደሽ ለወንድሞቼ ትንሣኤዬን ንገሪ ብሎ ላካት፡፡

ከዚህ በኋላ ጌታችን ብዙ ጊዜ እየተገለጸ ታይቷል በመጽሐፍ ቅዱስ ከተመዘገቡት መሃል፡፡

  - ገና ጨለማ ሳለ ለማርያም መግደላዊት  /ዮሐ. ፳፥1-08/ /ማር. 069/

  - እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ከገሊላ ጀምሮ ለተከተሉት ሦስት ሴቶች /ማቴ. ፳81-0/ /1ቆሮ. 055/

  - በመሸ ጊዜ ለሐዋርያትና ከእነርሱ ጋር ለነበሩት  /ሉቃ. ፳4፥፴6-፵3/   /ዮሐ. ፳፥09-፳5/

  - በሳምንቱ ቅዱስ ቶማስ ባለበት ለሐዋርያት /ዳግማዊ ትንሣኤ/   /ዮሐ. ፳፥፳6-፳9/

  - ለሰባቱ ደቀመዛሙርት በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ         /ዮሐ. ፳11-04/

  - ለአምስት መቶ ሰው /1ቆሮ.056/

  - ለቅዱስ ያዕቆብ    /1ቆሮ.057/

  - በዐረገበት ዕለት ለሐዋርያት  /ሉቃ. ፳4፥፵4-፶3/   /ሐዋ. 16-01 /

            ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ

ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ያሉት ዕለታት በቤተክርስቲያናችን ስያሜና መታሰቢያነት አላቸው፡፡

- የትንሣኤ ማግሥት ሰኞ - ማዕዶት /ሽግግር/

- ማክሰኞ  -  ቶማስ

- ረቡዕ    -  አልዓዛር

- ሐሙስ   -  የአዳም ሐሙስ

- ዓርብ    -   ጸአት /ነፍሳት ከሲኦል የወጡበት መታሰቢያ/

- ቅዳሜ   -   ቅዱሳት አንስት

- እሑድ   -   ዳግም ትንሣኤ

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine