የጥምቀት በዓል አከባበርና ሃይማኖታዊ ትርጉም

 ክርስትና በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ34 ዓ.ም. ነው፡፡ሐዋ.8፤26-34 ከዚያም በአብረሃና አጽብሃ ዘመነ መንግሥት የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነ፡፡ ለዚህም ከነገሥታቱ ባሻገር አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ጉልህ አስተዋጽኦን አድርገዋል፡፡

ከዚያም በኃላ በ481 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ተሰዓቱ ቅዱሳን የገዳም ሥርዓትን በመመሥረትና ትምህርተ ሃይማኖትን በማስፋፋት ከፍተኛ ሚናን ተጫውተዋል፡፡እነዚህ ቅዱሳን በነበሩበት ዘመን ኢትዮጵያውያኑ ቅዱስ ያሬድና ዐፄ ገብረ መስቀል ቅዱሳኑን ረድተዋል፡፡ ለሃይማኖቱ መስፋፋት የራሳቸውንም እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የቅዱስ ያሬድ የዜማና የመጻሕፍት ድርሰት ነው፡፡

 

የጥምቀት በዓልን ታሪካዊ አከባበር ስናነሳ እንግዲህ ወደዚህ ዘመን መመለሳችን ግድ ነው፡፡ በበዓሉ ታቦታትን ከየማደሪያቸው የማውጣት ሥርዓት የተጀመረው በዚህ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ ንጉሡ በየደብሩ ይከበር የነበረውን በዓል ጌታ ወደ ዮርዳኖስ መሄዱን ለማስታወስ ታቦታቱ ከማደሪያቸው እንዲወጡና በዓሉ እንዲከበር ሥርዓትን ሠሩ፡፡ ይህ ሥርዓት እስከ ቅዱስ ላሊበላ እና ይኩኖአምላክ ዘመን ድረስ ቀጥሎ በአንድ አጥቢያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት እንዲያርፉ ሥርዓት ተሠራ፡፡ እስከዚህ ዘመን ድረስ ታቦት በጥር 11 ጠዋት ወጥቶ ማታ ይገባ ነበር፡፡ ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በኋላ ግን ታቦት በጥር 10 አመሻሹ ላይ ወጥቶ በጥር 11 ወደ ማደሪያው እንዲመለስ ሥርዓት ተሠራ፡፡ እስከ ዛሬም ድረስ ይህ ሥርዓት በትውፊት ተጠብቆ የጥምቀት በዓል በተለየ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡      የዘንድሮውም በዓል በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደተለመደው በዘንድሮውም የጌታችን የጥምቀት በዓል ወጣቶች ጥቅስ የተጻፈበት ቲ ሸርት በማድረግና ታቦታቱ የሚሄዱበትን መንገድ በማጽዳት እና ምንጣፍ በማነጠፍ እንዲሁም ሥርዓትን ከፖሊስ ጋር በመተባበር በማስከበር፣ ሰንበት ተማሪዎች እና ካህናትም በተለያዩ ዝማሬዎች ታቦቱን በማጀብ፣ ምዕመኑም በእልልታ በጭብጨባና በዝማሬው በመሳተፍ በዓሉን ደማቅ አድርገውታል፡፡ እኛም ከዚህ በመቀጠል የዚህን ታላቅ በዓል ሃይማኖታዊ ትርጉምና አመሠራረት እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡ ጥምቀት ሌሎች የቤተክርስቲያን ምሥጢራትን ለመፈጸም ከእግዚአብሔር ለመወለድ የሚፈጸም ሥርዓት በመሆኑ ማንኛውም ክርስቲያን የእግዚአብሔር ልጅ ሊሰኝ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ሲፈጽም ጥምቀትን ማስቀደም ይኖርበታል፡፡በብሉይ ኪዳን ጥምቀት በውሃ መታጠብ መጥለቅና መንጻት ነበር በብሉይ ኪዳን በዓል ሲከበር በዓሉን ለማክበር የሚሰበሰበው ሕዝብ በውሃ መረጨት ለበዓሉ ዝግጅት የሚፈለጉ ዕቃዎች ሁሉ በውኃ መንጻት ነበረባቸው፡፡ ዘሌ. 6 7 እንዲሁም ሰውን ወይም ዕቃን /ንዋያተ ቅድሳት/ ያረክሳሉ ተብለው የሚታመኑባቸው ነገሮች ነበሩ፡፡ እነኚህ በውሃ ካልታጠቡ ወደ ሰፈር መግባት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ የሞተ ሰው አስከሬን የነካ ሰው በሞተበት ድንኳን ውስጥ የገባ ሁሉ እንደርኩስ ስለሚቆጠር በውሃ መታጠብና መንጻት የተለመደ ሕግ ነበር፡፡ ዘኁ. 0908 መዝ. ፶፥፶1ከብሉይ ኪዳን ውጭ የነበረ ሰው የኦሪትን ዕምነት ሲቀበል ወደ አይሁድ ማኅበር ከመግባቱ በፊት መገረዝና መታጠብ ግድ ነበር፡፡ ወደ እነርሱም ዕምነት ሲገባ እንደተወለደ ሕፃን ይቆጠር ነበር፡፡ እርሱም ከኢግዙርነት መለየት ከመቃብር እንደመውጣት ነው ተብሎ ይታመን ነበር፡፡ዮሐንስ የንስሓ ጥምቀትን አጠመቀ ማር. 14 የዮሐንስ ጥምቀት ለክርስቶስ ጥምቀት የሚያዘጋጅ የክርስቶስን ጥምቀት ለመቀበልና በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ባለቤት ለመሆን የሚያበቃ ነበር፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ሁለት ነገሮችን ያመለክታል፡፡1.       ከኃጢአት ወደ ሥርየት፣ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔርመመለስን2.       ሥርየተ ኃጢአትን አግኝቶ ከማኅበረ ጻድቃን መቀላቀልንበብሉይ ኪዳን ይፈጽም የነበረው ጥምቀት በሐዲስ ኪዳን እንደሚፈጸመው ጥምቀት ምሥጢር አልነበረም፡፡ የብሉይ ኪዳን ጥምቀት የመንጻት ጥምቀት ነበር፡፡ ዮሐ. 2፥6በሐዲስ ኪዳን ጥምቀት ከቤተክርስቲያን ምሥጢራት ከማይደገሙት አንዱ ሲሆን ትርጉሙም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር በተጸለየበት ውሃ /ማየ ሕይወት፣ማየ ገቦ/ ውስጥ በስመ ሥላሴ 3 ጊዜ መጥለቅ፣መዘፈቅ፣ መነከር ማለት ነው፡፡ ይህ ምሥጢር ለቤተክርስቲያን ምሥጢራት በሙሉ መግቢያ በር ነው፡፡የጥምቀት አስፈላጊነት1.       ድኅነት እናገኛለን ማር 06062.       ከውሃና ከመንፈስ ዳግም እንወለዳለን ዮሐ.3 3፣ ቲቶ. 35 ኤፌ. 5፥፳63.       ከጌታችን ሞቱን በሚመስል ሞት እንሞታለን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ እንነሳለን ሮሜ. 63 ቆላ.2024.       የኃጢአት ሥርየት እናገኛለን፡፡ እምነት መሠረት ነው ፍጹም የሚሆነው ግን በጥምቀት ነው፡፡ ሐዋ. 206 ቆላ. 601 ሐዋ. 27 ‹‹ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን›› ጸሎተ ሃይማኖት5.       በጥምቀት አዲስ ሕይወት እናገኛለን ያደፈው ሰውነታችን ይታደሳል ይቀደሳል ሮሜ. 646.       በጥምቀት የቤተክርስቲያን አባል እንሆናለን፡፡ በዘመነ ኦሪት የእግዚአብሔር ሕዝብ ለመሆን መገረዝ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነበር፡፡ በዘመነ ሐዲስም ጥምቀት በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ከቅድስት ቤተክርስቲያን የሚገኝ ጸጋ ተካፋይ ያደርገዋል፡፡ ቆላ. 201 በብሉይ ኪዳን ለጥምቀት የተደረጉ ምሳሌዎች1.       እስራኤል ቀይ ባህርን መሻገራቸው በደመና ማለፋቸው በደመናና በባህር ተጠመቁ ይላል፡፡ ዘጸ. 042 ፤ ዕብ. 0192.       ስምንቱ ነፍሳት የጸኑባት የኖህ መርከብ /የጥምቀት ምሳሌ ናት/ 1ጴጥ. 3፥፳ ፤ ዘፍ. 603 - 23.       ግዝረት የቃልኪዳን ምልክት ነው፡፡ ቆላ. 201 ዘፍ. 0734.       አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከመልከ ጼዴቅ መገናኘቱ ዘፍ. 04፥፳5.       ሶርያዊው ንዕማን በዮርዳኖስ ውኃ ታጥቦ ከለምጽ መንጻቱ   2ነገ. 5066.       የመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት ማቴ. 31-01እነዚህ ለጥምቀት በመጠኑ የተወሰዱ ምሳሌዎች ሲሆኑ የብሉይ ኪዳን ጥምቀት ፍጹም ድኅነት የሚያሰጥ አልነበረም፡፡የጥምቀት አመሠራረት በሐዲስ ኪዳንጥምቀት ጌታችን በተግባር /ማቴ. 33-06/ በትምህርት /ዮሐ. 35/ በትዕዛዝ /ማቴ. ፳809/ መሥርቷታል፡፡ ነገር ግን በምሥጢረ ጥምቀት ሙሉ ጸጋ የተሰጠው በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ መውረድ ነው፡፡ የሐዋ.21-5ጌታችን መች ተጠመቀ?ከእመቤታችን በተወለደ በሠላሳ ዘመኑ በዘመነ ሉቃስ ጥር1 ቀን ማክሰኞ ሌሊት 10 ሰዓት ተጠመቀ፡፡ጌታችን ለምን ተጠመቀ?ሀ. ለትህትና፣ ለትምህርት፣ ለአርአያነት ዮሐ. 031-07ለ. በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ሊደመስስ ቆላ. 204ሐ. የሦስትነትን ምሥጢር ይገልጥልን ዘንድ ማቴ. 303መ. በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመባረክጌታችን አምላክ ሆኖ ሳለ ለምን በባርያው በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ? ለምንስ ወደ ዮሐንስ ሔዶ ተጠመቀ?1.       ወደ እዚህ ዓለም የመጣው በትህትና እንጂ በልዕልና አይደለምና እኛን ትህትናን ለማስተማር2.       ሥርዓት ሲደነገግልን ጌታ ዮሐንስን ና አጥምቀኝ ብሎት ቢሆን ዛሬም ነገሥታት መኳንንትና ባለጸጎች ካህናትን ኑ እና አጥምቁን ባሉ ነበርና፡፡ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን ወደ ካህናት ሄዶ መጠመቅ እንዳለበት ለማስተማርጌታችን በማን ስም ተጠመቀ?ጌታ ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለ ጊዜ ‹‹ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለው አንተን በማን ስም ላጥምቅህ?›› በአብ ስም እዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ በአንተም ሕልው ነው እንዲያ በማን ስም ላጥምቅህ? ብሎ ቢጠይቀው‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባህርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡ እንዳለውም አጥምቆታል፡፡ እጆቹን ዘርግቶ በራሱ ላይ አኖረበት ረቦ ነው አልጫነበትም መሥዋዕተ ኦሪት አለፈ ከእንግዲህ መሥዋዕት አንተ ነህ ሲል ነው፡፡ ዮሐንስ ጌታችንን ሲያጠምቅ ለምን እጁን አልጫነበትም?1.       ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል2.       መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል   

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine