ዕረፍታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም (ጥር 21)

ማርያም ማለት መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው፡፡ ምዕመናንን እየመራች ወደ መንግስተ ሰማያት ታስገባለችና፡፡ አንድም ፍጽምት ማለት ነው፡፡ በሥጋም በልቦናም ንጽሕት ናትና፡፡ ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው፡፡ ከፍጡራን በላይ ናትና፡፡ ‹‹ማር›› በምድር ‹‹ያም›› በሰማይ ናት፡፡ ማር በምድር ተወዳዳሪ የሌለው ምግብ ነው፡፡ ያም በሰማይ ቅዱሳን የሚመገቡት በብሔረ ሕያዋን በብሔረ ብፁዓን ያሉ ቅዱሳን የሚመገቡት ጣፋጭ ምግብ ነው፡፡ የእመቤታችን ርህራሄዋ በምድርም በሰማይም ሁሉ ጣፋጭ ነውና ማርያም ተባለች፡፡እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ 64 ዓመት ኖራ ጥር 21 እሑድ ቀን ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ ቢላት ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜ፣ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው፡፡ በሲኦል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእኚህ ቤዛ ይሆናቸዋል አላት፡፡ እመቤታችንም እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋንም ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጓት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገውም ይዘዋት ወደ ጌቴሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው ልጅዋን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ፤ አሁን ደግሞ እሷን ዐረገች ተነሣች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን ኑ የማርያምን ሥጋ እናቃጥል ብለው ተነሡ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ የአልጋውን ሸንኮር ቢይዘው የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀላው፡፡ በድያለሁ ማረኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘንበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት አለችው፡፡ ቢመልሰውም ድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ ገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡ድንግል እመቤት ንጹሕት ምሕረትለሁሉ ምታዝን ርኅርኅት እናት የአምላክ እናት ሁና እንደምን ትሙት፡፡ድንግል በሥጋዋ ሞትን ስትቀምሰው ሲዘምሩ ዋሉ ነፍሳት ተደስተው በሞቷ ቤዛነት ለዘለዓለም ድነው፡፡የእመቤቴ ነፍሷን ጌታ ሲያሳርጋትመላእክት ከሰማይ ከምድር ሐዋርያት መጡ እየዘመሩ በጥዑም ማኅሌት ለሰሚ እስኪመስል የደረሰ ምጽአት እመቤቴ ማርያም አማልደሽ ከልጅሽ እድሜን ለንስሓ ስጭኝ እባክሽ አንቺኑ ነውና ተስፋ ያረግሁሽ ቅዱስ ያሬድ የእናታችን የእመቤታችን ቅድስት ማርያም ልመናዋ ምልጃዋ ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይኑር፡፡ በሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በዓለ ቅድስት ሥላሴ (ጥር 7) 2004

በዓለ ቅድስት ሥላሴ (ጥር 7)

በሰ//ቤቱ ትምህርት ክፍል

ሥላሴ የሚለው ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦስት ሦስትነት ማለት ሲሆን በያዘው ምሥጢር ግን አንድም ሦስትም /አንድነት ሦስትነት/ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ሦስትነታቸው በስም በአካል በግብር፤ አንድነታቸው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ ነው፡፡

  

  

1.   የሥላሴ ሦስትነት

ሀ. የስም ሦስትነት ፡- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ‹‹እንግዲህ አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ . . .›› ማቴ. 28፥19

      ለ. የአካል ሦስትነት፡- ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አለው፡፡ (ሃይማኖተ አበው) አካል ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለው ነው፡፡ ገጽ ማለት ደግሞ ፊት ነው፡፡ መልክም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለ ነው፡፡ አካልም እንዳላቸው ሲያጠይቅ ነቢዩ ዳዊት ‹‹የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው፡፡›› መዝ. 33፥15 ‹‹እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም›› መዝ. 118፥73 ኢሳይያስም ‹‹እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፡- ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት ›› ብሏል ኢሳ. 66፥1 ለአብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ስር ዘፍ.18፥1-4 ለዮሐንስ በዮርዳኖስ ተገልጸዋል ማቴ. 3፥16-17

      ሐ. የግብር ሦስትነት፡- የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው፡፡ አብ ቢወልድ ቢያሠርጽ እንጅ እንደ ወልድ አይወለድም እንደመንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ ወልድም ቢወለድ እንጂ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ መንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ መንፈስ ቅዱስም ቢሠርጽ እንጅ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ ወልድ አይወለድም፡፡ አብን ወላዲ አሥራጺ ወልድን ተወላዲ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ስላልን የሚበላለጡ አይደሉም አንድ ናቸው፡፡ ጌታ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹እኔ እና አብ አንድ ነን›› ብሏል፡፡ ዮሐ. 10፥30  አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ኢይልህቅ አብ እም ወልዱ ወልድኒ ኢይልህቅ እምመንፈስ ቅዱስ ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢይንዕስ እምወልድ ወወልድኒ ኢይንዕስ እምአቡሁ›› ብሏል፡፡ ይህ ማለት ሦስት አምላክ ማለት አይደለም፡፡ አንድ አምላክ ይባላሉ አንጂ፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም‹‹ወመለኮትሰ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ›› ብሏል፡፡

Read more: በዓለ ቅድስት ሥላሴ (ጥር 7) 2004

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine